Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 49 Online
Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 49 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መዝሙረ ዳዊት and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
መዝሙረ ዳዊት 49
ምዕራፍ 49
1. አሕዛብ ሁላችሁ፥ ይህን ስሙ፤ በዓለም የምትኖሩትም ሁላችሁ፥ አድምጡ፤
2. ዝቅተኞችና ከፍተኞች፥ ባለጠጎችና ድሆች በአንድነት።
3. አፌ ጥበብን ይናገራል፥ የልቤም አሳብ ማስተዋልን።
4. ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፥ በበገናም ምሥጢሬን እገልጣለሁ።
5. ኃጢአት ተረከዜን በከበበኝ ጊዜ በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ?
6. በኃይላቸው የሚታመኑ፥ በባለጠግነታቸውም ብዛት የሚመኩ፤
7. ወንድም ወንድሙን አያድንም፥ ሰውም አያድንም፤ ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም፥
8. –
9. ለዘላለም እንዲኖር፥ ጥፋትንም እንዳያይ፤ የነፍሳቸው ለውጥ ከብሮአልና፥ ለዘላለምም ቀርቶአልና።
10. ብልሃተኞች እንዲሞቱ፥ ሰነፎችችና ደንቆሮች በአንድነት እንዲጠፉ፥ ገንዘባቸውንም ለሌሎች እንዲተዉ አይቶአል።
11. በልባቸውም ቤታቸው ለዘላለም የሚኖር፥ ማደሪያቸውም ለልጆች ልጅ የሚሆን ይመስላቸዋል፤ በየአገራቸውም ስማቸው ይጠራል።
12. ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም፤ እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ።
13. ይህች መንገዳቸው መሰናክላቸው ናት፥ ከእነርሱም በኋላ የሚመጡ በአፋቸው እሺ ይላሉ።
14. እንደ በጎች ወደ ሲኦል የሚሄዱ ናቸው፥ እረኛቸውም ሞት ነው፤ ቅኖችንም በማለዳ ይገዙአቸዋል፥ ውበታቸውም ከመኖሪያቸው ተለይታ በሲኦል ታረጃለች።
15. ነገር ግን እግዚአብሔር ይቀበለኛልና ነፍሴን ከሲኦል እጅ ይቤዣታል።
16. የሰው ባለጠግነት የቤቱም ክብር በበዛ ጊዜ አትፍራ፥
17. በሞተ ጊዜ ከእርሱ ጋር ምንም አይወስድምና፥ ክብሩም ከእርሱ በኋላ አይወርድምና።
18. በሕይወቱ ሳለ ነፍሱን ባርኮአልና ለሰውነቱ መልካም ብታደርግለት ያመሰግንሃል።
19. ሆኖም ወደ አባቶቹ ትውልድ ይወርዳል፤ ለዘላለም ብርሃንን አያይም።
20. አእምሮ የሌለው ክቡር ሰው እንደሚጠፋ እንስሶች መሰለ።
About መዝሙረ ዳዊት Chapter 49
Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 49 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: መዝሙረ ዳዊት
Chapter: 49
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መዝሙረ ዳዊት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading መዝሙረ ዳዊት Chapter 49 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is መዝሙረ ዳዊት Chapter 49?
መዝሙረ ዳዊት Chapter 49 is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete መዝሙረ ዳዊት Chapter 49 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from መዝሙረ ዳዊት
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 112
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 55
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 59
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 1
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 147
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 122
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 120
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- 2 ሳሙኤል Chapter 4
- 1 ዜና መዋዕል Chapter 4
- መኃልየ መኃልይ Chapter 7
- ዕዝራ Chapter 1
- ዘሌዋውያን Chapter 19
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 46
- ዮናስ Chapter 3