Read መኃልየ መኃልይ Chapter 7 Online
Read መኃልየ መኃልይ Chapter 7 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መኃልየ መኃልይ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መኃልየ መኃልይ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
መኃልየ መኃልይ 7
ምዕራፍ 7
1. አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ። በሱላማጢስ ምን ታያላችሁ? እርስዋ እንደ መሃናይም ዘፈን ናት።
2. ፤ አንቺ የመኰንን ልጅ ሆይ፥ እግሮችሽ በጫማ ውስጥ እንዴት ውቦች ናቸው! ዳሌዎችሽስ በአንጥረኛ እጅ እንደ ተሠሩ እንደ ዕንቍዎች ይመስላሉ።
3. ፤ እንብርትሽ የወይን ጠጅ እንደማይጐድልበት እንደ ተነጠጠ ጽዋ ነው፤ ሆድሽ እንደ ስንዴ ክምር፥ በአበባም እንደ ታጠረ ነው።
4. ፤ ሁለቱ ጡቶችሽ እንደ ሁለቱ መንታ እንደ ሚዳቋ ግለገሎች ናቸው።
5. ፤ አንገትሽ እንደ ዝሆን ጥርስ ግንብ ነው፤ ዓይኖችሽ በሐሴቦን ውስጥ በባትረቢ በር አጠገብ እንደ ውኃ ኵሬዎች ናቸው፤ አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አፋዛዥ እንደሚመለከት እንደ ሊባኖስ ግንብ ነው።
6. ፤ ራስሽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ በላይሽ ነው፤ የራስሽም ጠጕር እንደ ሐምራዊ ሐር ነው፤ ንጉሡ በሹርባው ታስሮአል።
7. ፤ ወዳጄ ሆይ፥ እንዴት የተዋብሽ ነሽ! እንዴትስ ደስ ታሰኛለሽ!
8. ፤ ይህ ቁመትሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፥ ጡቶችሽም የወይን ዘለላ ይመስላሉ።
9. ፤ ወደ ዘንባባው ዛፍ እወጣለሁ ጫፎችዋንም እይዛለሁ አልሁ፤ ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ የአፍንጫሽም ሽቱ እንደ እንኮይ ናቸው።
10. ፤ ጕሮሮሽ ለወዳጄ እየጣፈጠ እንደሚገባ፥ የተኙትን ከንፈሮች ይናገሩ ዘንድ እንደሚያደርግ፥ እንደ ማለፊያ የወይን ጠጅ ነው።
11. ፤ እኔ የውዴ ነኝ፥ የእርሱም ምኞት ወደ እኔ ነው።
12. ፤ ውዴ ሆይ፥ ና፥ ወደ መስክ እንውጣ በመንደሮችም እንደር።
13. ፤ ወደ ወይኑ ቦታ ማልደን እንሂድ፤ ወይኑ አብቦ አበባውም ፍሬ አንዠርግጎ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ እንይ፤ በዚያ ውዴን እሰጥሃለሁ። [14]፤ ትርንጎዎች መዓዛን ሰጡ፤ መልካሞች ፍሬዎች ሁሉ፥ አሮጌው ከአዲሱ ጋር፥ በደጃችን አሉ፤ ውዴ ሆይ፥ ሁሉን ለአንተ ጠበቅሁልህ።
About መኃልየ መኃልይ Chapter 7
Read መኃልየ መኃልይ Chapter 7 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መኃልየ መኃልይ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: መኃልየ መኃልይ
Chapter: 7
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መኃልየ መኃልይ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading መኃልየ መኃልይ Chapter 7 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is መኃልየ መኃልይ Chapter 7?
መኃልየ መኃልይ Chapter 7 is part of the Book of መኃልየ መኃልይ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete መኃልየ መኃልይ Chapter 7 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from መኃልየ-መኃልይ
- መኃልየ መኃልይ Chapter 2
- መኃልየ መኃልይ Chapter 6
- መኃልየ መኃልይ Chapter 8
- መኃልየ መኃልይ Chapter 1
- መኃልየ መኃልይ Chapter 4
- መኃልየ መኃልይ Chapter 3
- መኃልየ መኃልይ Chapter 5
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- ዘጸአት Chapter 5
- 1 ሳሙኤል Chapter 23
- ዮናስ Chapter 1
- ኢያሱ Chapter 16
- ሶፎንያስ Chapter 3
- 2 ሳሙኤል Chapter 4
- ኢሳይያስ Chapter 2