መዝሙረ ዳዊት Chapter 105

For English

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 105 Online

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 105 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መዝሙረ ዳዊት and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

መዝሙረ ዳዊት 105

ምዕራፍ 105

1. እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ፥ ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ።

2. ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፥ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።

3. በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው።

4. እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።

6. ባሪያዎቹ የአብርሃም ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ የሠራትን ድንቅ አስቡ፥ ተአምራቱን የአፉንም ፍርድ።

7. እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱ በምድር ሁሉ ነው።

8. ቃል ኪዳኑን ለዘላለም፥ እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፥

9. ለአብርሃም ያደረገውን፥ ለይስሐቅም የማለውን፤

10. ለያዕቆብ ሥርዓት እንዲሆን ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን እንዲሆን አጸና።

11. እንዲህም አለ። ለአንተ የከነዓንን ምድር የርስታችሁን ገመድ እሰጣለሁ፤

12. ይህም የሆነው እነርሱ በቍጥር ጥቂቶች ሰዎች፥ እጅግ ጥቂቶችና ስደተኞች ሲሆኑ ነው።

13. ከሕዝብ ወደ ሕዝብ፥ ከመንግሥታትም ወደ ሌላ ሕዝብ አለፉ።

14.

15. የቀባኋቸውን አትዳስሱ፥ በነቢያቴም ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም፥ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።

16. በምድር ላይ ራብን ጠራ፥ የእህልን ኃይል ሁሉ ሰበረ።

17. በፊታቸው ሰውን ላከ፤ ዮሴፍ ለባርነት ተሸጠ።

18. እግሮቹም በእግር ብረት ደከሙ፥ እርሱም በብረት ውስጥ ገባ።

19. ቃሉ እስኪመጣለት ድረስ፥ የእግዚአብሔር ቃል ፈተነው።

20. ንጉሥ ላከ ፈታውም፥ የአሕዛብም አለቃ አስፈታው።

21. የቤቱ ጌታ፥ የጥሪቱ ሁሉ ገዢ አደረገው፥

22. አለቆቹን እንደ ፈቃዱ ይገሥጽ ዘንድ፥ ሽማግሌዎቹንም ጥበበኞች ያደርጋቸው ዘንድ።

23. እስራኤልም ወደ ግብጽ ገባ፥ ያዕቆብም በካም አገር ተቀመጠ።

24. ሕዝቡንም እጅግ አበዛ፥ ከጠላቶቻቸውም ይልቅ አበረታቸው።

25. ሕዝቡን ይጠሉ ዘንድ በባሪያዎቹም ላይ ይተነኰሉ ዘንድ ልባቸውን ለወጠ።

26. ባሪያውን ሙሴን የመረጠውንም አሮንን ላከ።

27. የተኣምራቱን ነገር በላያቸው ድንቁንም በካም አገር አደረገ።

28. ጨለማን ላከ ጨለመባቸውም፤ በቃሉም ዐመፁ።

29. ውኃቸውን ወደ ደም ለወጠ፥ ዓሦቻቸውንም ገደለ።

30. ምድራቸው የንጉሦቻቸውም ቤቶች በጓጕንቸር ሞሉ።

31. ተናገረ፥ የውሻ ዝንብ ትንኝም በዳርቻቸው መጡ።

32. ዝናባቸውን በረዶ አደረገው፥ እሳትም በምድራቸው ተቃጠለች።

33. ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ፥ የአገራቸውንም ዛፍ ሁሉ ሰበረ።

34. ተናገረ፥ አንበጣም ስፍር ቍጥር የሌለውም ኩብኩባ መጣ፥

35. የአገራቸውንም ለምለም ሁሉ በላ፥ የምድራቸውንም ፍሬ በላ።

36. የአገራቸውንም በኵር ሁሉ፥ የጕልበታቸውን መጀመሪያ ሁሉ መታ።

37. ከወርቅና ከብርም ጋር አወጣቸው፥ በወገናቸውም ውስጥ ደዌ አልነበረም።

38. ፈርተዋቸው ነበርና ግብጽ በመውጣታቸው ደስ አላት።

39. ደመናን ለመሸፈኛ ዘረጋባቸው፥ እሳትንም በሌሊት ያበራላቸው ዘንድ ዘረጋ።

40. ለመኑ፥ ድርጭትንም አመጣላቸው፥ የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው።

41. ዓለቱን ሰነጠቀ፥ ውኃውም ፈሰሰ፤ ወንዞች በበረሃ ሄዱ፤

42. ለባሪያው ለአብርሃም የነገረውን ቅዱስ ቃሉን አስቦአልና።

43. ሕዝቡንም በደስታ የተመረጡትንም በእልልታ አወጣ።

44. የአሕዛብንም አገሮች ሰጣቸው፥ የወገኖችንም ድካም ወረሱ፥

45. ሕጉን ይጠብቁ ዘንድ፥ ሥርዓቱንም ይፈልጉ ዘንድ። ሃሌ ሉያ

About መዝሙረ ዳዊት Chapter 105

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 105 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: መዝሙረ ዳዊት
Chapter: 105
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መዝሙረ ዳዊት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading መዝሙረ ዳዊት Chapter 105 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is መዝሙረ ዳዊት Chapter 105?

መዝሙረ ዳዊት Chapter 105 is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete መዝሙረ ዳዊት Chapter 105 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from መዝሙረ ዳዊት

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 112
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 59
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 55
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 120
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 1
  6. መዝሙረ ዳዊት Chapter 147
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 134

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ሕዝቅኤል Chapter 31
  2. ዳንኤል Chapter 11
  3. ኢዮብ Chapter 11
  4. ኤርምያስ Chapter 34
  5. 2 ሳሙኤል Chapter 18
  6. ዘኍልቍ Chapter 33
  7. ኤርምያስ Chapter 41

Related Chapters & Readings

  1. ዘጸአት Chapter 2
  2. ማርቆስ Chapter 4
  3. ዕብራውያን Chapter 6
  4. ኢሳይያስ Chapter 51
  5. ዘኍልቍ Chapter 5
  6. ኢዮብ Chapter 34
  7. ኢሳይያስ Chapter 19
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *