መዝሙረ ዳዊት Chapter 119

For English

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 119 Online

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 119 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መዝሙረ ዳዊት and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

መዝሙረ ዳዊት 119

ምዕራፍ 119

1. በመንገዳቸው ንጹሐን የሆኑ፥ በእግዚአብሔርም ሕግ የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።

2. ምስክሩን የሚፈልጉ፥ በፍጹም ልብ የሚሹት ምስጉኖች ናቸው፤

3. ዓመፅንም አያደርጉም፥ በመንገዶቹም ይሄዳሉ።

4. ትእዛዛትህን እጅግ እንጠብቅ ዘንድ አንተ አዘዝህ።

5. ሥርዓትህን ለመጠበቅ፤ መንገዶቼ ይቀኑ ዘንድ እወድድ ነበር።

6. ትእዛዝህን ሁሉ ስመለከት በዚያን ጊዜ አላፍርም።

7. አቤቱ፥ የጽድቅህን ፍርድ ስማር በቅን ልብ አመሰግንሃለሁ።

8. ሥርዓትህን እጠብቃለሁ፤ በፍጹም አትጣለኝ። ቤት

9. ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው።

10. በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ።

11. አንተ እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።

12. አቤቱ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፤ ሥርዓትህን አስተምረኝ።

13. የአፍህን ፍርድ ሁሉ በከንፈሬ ነገርሁ።

14. እንደ ብልጥግና ሁሉ በምስክርህ መንገድ ደስ አለኝ።

15. ትእዛዝህን አሰላስላለሁ፥ መንገድህንም እፈልጋለሁ።

16. በትእዛዝህ ደስ ይለኛል፤ ቃልህንም አልረሳም። ጋሜል

17. ለባሪያህ መልካም አድርግ ሕያው እንድሆን፥ ቃልህንም እንድጠብቅ።

18. ዓይኖቼን ክፈት፥ ከሕግህም ተኣምራትህን አያለሁ።

19. እኔ በምድር እንግዳ ነኝ፤ ትእዛዛትህን ከእኔ አትሰውር።

20. ነፍሴ ሁልጊዜ ፍርድህን እጅግ ናፈቀች።

21. ከትእዛዛትህ የሳቱትን ትዕቢተኞችንና ርጉማንን ዘለፍህ።

22. ምስክርህን ፈልጌአለሁና። ስድብንና ነውርን ከእኔ አርቅ።

23. አለቆች ደግሞ ተቀምጠው እኔን አሙኝ፤ ባሪያህ ግን ሕግህን ያሰላስል ነበር።

24. ምስክርህም ተድላዬ ነው፥ ሥርዓትህም መካሪዬ ነው። ዳሌጥ

25. ነፍሴ ወደ ምድር ተጠጋች፤ እንደ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።

26. መንገድህን ነገርሁ ሰማኸኝም፤ ሥርዓትህን አስተምረኝ።

27. የሥርዓትህን መንገድ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ተኣምራትህንም አሰላስላለሁ።

28. ከኀዘን የተነሣ ነፍሴ አንቀላፋች፤ በቃልህ አጠንክረኝ።

29. የዓመፅን መንገድ ከእኔ አርቅ፥ በሕግህም ማረኝ፤

30. የእውነትህን መንገድ መረጥሁ፥ ፍርድህንም አልረሳሁም።

31. አቤቱ፥ ምስክርህን ተጠጋሁ፤ አታሳፍረኝ።

32. ልቤን ባሰፋኸው ጊዜ፥ በትእዛዝህ መንገድ ሮጥሁ። ሄ

33. አቤቱ፥ የሥርዓትህን መንገድ አስተምረኝ፥ ሁልጊዜም እፈልገዋለሁ።

34. እንዳስተውል አድርገኝ፥ ሕግህንም እፈልጋለሁ፤ በፍጹም ልቤም እጠብቀዋለሁ።

35. እርስዋን ወድጃለሁና የትእዛዝህን መንገድ ምራኝ።

36. ልቤን ወደ ምስክርህ አዘንብል፥ ወደ ስስትም አይሁን።

37. ከንቱ ነገርን እንዳያዩ ዓይኖቼን መልስ፤ በመንገድህ ሕያው አድርገኝ።

38. እንዲፈራህ ባሪያህን በቃልህ አጽና።

39. ፍርድህ መልካም ናትና የተጠራጠርሁትን ስድብ ከእኔ አርቅ።

40. እነሆ፥ ትእዛዝህን ናፈቅሁ፤ በጽድቅህ ሕያው አድርገኝ ዋው

41. አቤቱ፥ እንደ ቃልህ፥ ምሕረትህና መድኃኒትህ ይምጡልኝ።

42. በቃልህ ታምኛለሁና ለሚሰድቡኝ በነገር እመልስላቸዋለሁ።

43. በፍርድህም ታምኛለሁና የእውነትን ቃል ከአፌ ፈጽመህ አታርቅ።

44. ለዘላለም ዓለም ሁልጊዜ ሕግህን እጠብቃለሁ።

45. ትእዛዛትህንም ፈልጌአለሁና አስፍቼ እሄዳለሁ።

46. በነገሥታት ፊት ምስክርህን እናገራለሁ፥ አላፍርምም፤

47. እጅግም በወደድኋቸው በትእዛዛትህ ደስ ይለኛል።

48. እጆቼንም ወደ ወደድኋቸው ወደ ትእዛዛትህ አነሣለሁ፤ ሥርዓትህንም አሰላስላሁ። ዛይ

49. ለባሪያህ ተስፋ ያስደረግኸውን ቃልህን አስብ።

50. ቃልህ ሕያው አድርጎኛልና ይህች በመከራዬ ደስ አሰኘችኝ።

51. ትዕቢተኞች እጅግ ዐመፁ፤ እኔ ግን ከሕግህ አልራቅሁም።

52. ከጥንት የነበረውን ፍርድህን አሰብሁ፥ አቤቱ፥ ተጽናናሁም።

53. ሕግህን ከተዉ ከኃጢአተኞች የተነሣ ኅዘን ያዘኝ።

54. በእንግድነቴ አገር ሥርዓትህ መዝሙር ሆነችኝ።

55. አቤቱ፥ በሌሊት ስምህን አሰብሁ፥ ሕግህንም ጠበቅሁ።

56. ትእዛዛትህንም ፈልጌአለሁና፤ ይህች ሆነችልኝ። ሔት

57. እግዚአብሔር ክፍሌ ነው፤ ሕግህን እጠብቃለሁ አልሁ።

58. በፍጹም ልቤ ወደ ፊትህ ተማለልሁ፤ እንደ ቃልህ ማረኝ።

59. ስለ መንገዶችህ አሰብሁ፥ እግሬንም ወደ ምስክሮችህ መለስሁ።

60. ትእዛዝህን ለመጠበቅ ጨከንሁ አልዘገየሁምም።

61. የኃጥኣን ገመዶች ተተበተቡብኝ፤ ሕግህን ግን አልረሳሁም።

62. ስለ ጽድቅህ ፍርድ፥ በእኩለ ሌሊት አመሰግንህ ዘንድ እነሣለሁ።

63. እኔ ለሚፈሩህ ሁሉ፥ ትእዛዝህንም ለሚጠብቁ ባልንጀራ ነኝ።

64. አቤቱ፥ ምሕረትህ በምድር ሁሉ ሞላች፤ ሥርዓትህን አስተምረኝ። ጤት

65. አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ለባሪያህ መልካም አደረግህ።

66. በትእዛዛትህ ታምኛለሁና መልካም ምክርና እውቀትን አስተምረኝ።

67. እኔ ሳልጨነቅ ሳትሁ፤ አሁን ግን ቃልህን ጠበቅሁ።

68. አቤቱ፥ አንተ ቸር ነህ፥ በቸርነትህም ሥርዓትህን አስተምረኝ።

69. የትዕቢተኞች ዓመፅ በላዬ በዛ፤ እኔ ግን በፍጹም ልቤ ትእዛዛትህን እፈልጋለሁ።

70. ልባቸው እንደ ወተት ረጋ፤ እኔ ግን በሕግህ ደስ ይለኛል።

71. ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።

72. ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል። ዮድ

73. እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ትእዛዛትህንም እማራለሁ።

74. በቃልህ ታምኛለሁና የሚፈሩህ እኔን አይተው ደስ ይላቸዋል።

75. አቤቱ፥ ፍርድህ ጽድቅ እንደ ሆነች፥ በእውነትህም እንዳስቸገርኸኝ አወቅሁ።

76. ምሕረትህ ለመጽናናቴ ትሁነኝ፥ እንደ ቃልህም ለባሪያህ ይሁነው።

77. ሕግህ ተድላዬ ናትና ቸርነትህ ትምጣልኝ፥ በሕይወትም ልኑር።

78. ትዕቢተኞች በዓመፅ ጠምመውብኛልና ይፈሩ፤ እኔ ግን በትእዛዝህ እጫወታለሁ።

79. የሚፈሩህና ምስክሮችህን የሚያውቁ ወደ እኔ ይመለሱ።

80. እንዳላፍር ልቤ በሥርዓትህ የቀና ይሁን። ካፍ

81. ነፍሴ መድኃኒትህን ናፈቀች፤ በቃልህም ታመንሁ።

82. መቼ ታጽናናኛለህ እያልሁ ዓይኖቼ ስለ ቃልህ ፈዘዙ።

83. በጢስ እንዳለ አቁማዳ ሆኛለሁና፤ ሥርዓትህን ግን አልረሳሁም።

84. የባሪያህ ዘመኖች ስንት ናቸው? በሚያሳድዱኝስ ላይ መቼ ትፈርድልኛለህ?

85. ኃጢአተኞች ጨዋታን ነገሩኝ፥ አቤቱ፥ እንደ ሕግህ ግን አይደለም።

86. ትእዛዛትህ ሁሉ እውነት ናቸው፤ በዓመፅ አሳድደውኛል፤ እርዳኝ።

87. ከምድር ሊያጠፉኝ ጥቂት ቀርቶአቸው ነበር፤ እኔ ግን ትእዛዛትህን አልተውሁም።

88. እንደ ምሕረትህ ሕያው አድርገኝ፤ የአፍህንም ምስክር እጠብቃለሁ። ላሜድ

89. አቤቱ፥ ቃልህ በሰማይ ለዘላለም ይኖራል።

90. እውነትህ ለልጅ ልጅ ናት፤ ምድርን መሠረትሃት እርስዋም ትኖራለች።

91. ሁሉም ባሪያዎችህ ናቸውና ቀኑ በትእዛዝህ ይኖራል።

92. ሕግህ ተድላዬ ባይሆን፥ ቀድሞ በጐስቍልናዬ በጠፋሁ ነበር።

93. በእርሱ ሕያው አድርገኸኛልና ፍርድህን ለዘላለም አልረሳም።

94. እኔ የአንተ ነኝ፤ ፍርድህን ፈልጌአልሁና አድነኝ።

95. ኃጢአተኞች ያጠፉኝ ዘንድ ጠበቁኝ፤ ምስክርህን ግን መረመርሁ።

96. የሥራህን ሁሉ ፍጻሜ አየሁ፤ ትእዛዝህ ግን እጅግ ሰፊ ነው። ሜም

97. አቤቱ፥ ሕግህን እንደ ምን እጅግ ወደድሁ! ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታዬ ነው።

98. ለዘላለም ለእኔ ነውና ትእዛዝህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ።

99. ምስክርህ ትዝታዬ ነውና ካስተማሩኝ ሁሉ ይልቅ አስተዋልሁ።

100. ትእዛዝህን ፈልጌአለሁና ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋልሁ።

101. ቃልህን እጠብቅ ዘንድ ከክፉ መንገድ ሁሉ እግሬን ከለከልሁ።

102. አስተምረኸኛልና ከፍርድህ አልራቅሁም።

103. ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ።

104. ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ። ኖን

105. ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።

106. የጽድቅህን ፍርድ እጠብቅ ዘንድ ማልሁ፥ አጸናሁም።

107. እጅግ ተቸገርሁ፤ አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።

108. አቤቱ፥ ከአፌ የሚወጣውን ቃል ውደድ፥ ፍርድህንም አስተምረኝ።

109. ነፍሴ ሁልጊዜ በእጅህ ውስጥ ናት፤ ሕግህን ግን አልረሳሁም።

110. ኃጢአተኞች ወጥመድን ዘረጉብኝ፤ ከትእዛዝህ ግን አልሳትሁም።

111. የልቤ ደስታ ነውና ምስክርህን ለዘላለም ወረስሁ።

112. ለዘላለም ለፍጻሜውም ትእዛዝህን አደርግ ዘንድ ልቤን አዘነበልሁ። ሳምኬት

113. ዓመፀኞችን ጠላሁ፥ ሕግህን ግን ወደድሁ።

114. አንተ ረዳቴና መጠጊያዬ ነህ፥ በቃልህም ተማመንሁ።

115. እናንተ ኃጢአተኞች፥ ከእኔ ራቁ፥ የአምላኬንም ትእዛዝ ልፈልግ።

116. እንደ ቃልህ ደግፈኝ፥ ሕያውም እሆናለሁ። ከተስፋዬም አልፈር።

117. እርዳኝ እድናለሁም፥ ሁልጊዜም ሥርዓትህን እመረምራለሁ።

118. ምኞታቸው ዓመፃ ነውና ከሥርዓትህ የሚርቁትን ሁሉ አጐሳቈልሃቸው።

119. የምድርን ኃጢአተኞች ሁሉ እንደ ርኵሰት አጠፋሃቸው፤ ስለዚህ ምስክርህን ወደድሁ።

120. ሥጋዬ አንተን ከመፍራት የተነሣ ደንገጠ፤ ከፍርድህ የተነሣ ፈርቻለሁ። ዔ

121. ፍርድንና ጽድቅን ሠራሁ፤ ለሚያስጨንቁኝ አሳልፈህ አትስጠኝ።

122. ባሪያህን በመልካም ጠብቀው፤ ትዕቢተኞችም አይጋፉኝ።

123. ዓይኖቼ ለማዳንህ፥ ለጽድቅህም ቃል ፈዘዙ።

124. ለባሪያህ እንደ ምሕረትህ አድርግ፥ ሥርዓትህንም አስተምረኝ።

125. እኔ ባሪያህ ነኝ፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ምስክርህንም አውቃለሁ።

126. ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ ነው፥ ሕግህንም ሻሩት።

127. ስለዚህ ከወርቅና ከዕንቍ ይልቅ ትእዛዝህን ወደድሁ።

128. ስለዚህ ወደ ትእዛዝህ ሁሉ አቀናሁ፥ የዓመፅንም መንገድ ሁሉ ጠላሁ። ፌ

129. ምስክሮችህ ድንቆች ናቸው፤ ስለዚህ ነፍሴ ፈለገቻቸው።

130. የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።

131. አፌን ከፈትሁ፥ አለከለክሁም፤ ወደ ትእዛዝህ ናፍቄአለሁና።

132. ስምህን ለሚወድዱ እንድምታደርገው ፍርድ፥ ወደ እኔ ተመልከተ ማረኝም።

133. አካሄድን እንደ ቃልህ አቅና፤ ኃጢአትም ሁሉ አይግዛኝ።

134. ከሰው ግፍ አድነኝ፤ ትእዛዝህንም እጠብቃለሁ።

135. በባሪያህ ላይ ፊትህን አብራ፥ ሥርዓትህንም አሰተምረኝ።

136. ሕግህን አልጠበቅሁምና የውኃ ፈሳሽ ከዓይኖቼ ፈሰሰ። ጻዴ

137. አቤቱ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፥ ፍርድህም ቅን ነው።

138. ምስክርህን በጽድቅ አዘዝህ፥ እጅግም ቅን ነው።

139. ጠላቶቼ ቃልህን ረስተዋልና የቤትህ ቅንዓት አቀለጠኝ።

140. ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው፥ ባሪያህም ወደደው።

141. እኔ ታናሽና የተናቅሁ ነኝ፤ ትእዛዛትህን ግን አልረሳሁም።

142. ጽድቅህ የዘላለም ጽድቅ ነው፥ ቃልህም እውነት ነው።

143. መከራና ችግር አገኙኝ፤ ትእዛዛትህ ግን ተድላዬ ናቸው።

144. ምስክርህ ለዘላለም ጽድቅ ነው፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ በሕይወትም አኑረኝ። ቆፍ

145. በፍጹም ልቤ ጮኽሁ፥ አቤቱ፥ ስማኝ፤ ሥርዓትህን እፈልጋለሁ።

146. ወደ አንተ ጮኽሁ፤ አድነኝ፥ ምስክርህንም እጠብቃለሁ።

147. ማለዳ ጮኽሁ፤ ቃልህንም ተስፋ አድርጌአለሁ።

148. ቃልህን አስብ ዘንድ ዓይኖቼ ለመማለድ ቀደሙ።

149. አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ ድምፄን ስማ፤ እንደ ፍርድህ ሕያው አድርገኝ።

150. በዓመፃ የሚያሳድዱኝ ቀረቡ፥ ከሕግህም ራቁ።

151. አቤቱ፥ አንተ ቅርብ ነህ፥ መንገዶችህም ሁሉ ቅኖች ናቸው።

152. ከዘላለም እንደ መሠረትኸው ከቀድሞ ጀምሮ ከምስክርህ የተነሣ አወቅሁ። ሬስ

153. ሕግህን አልረሳሁምና ችግሬን ተመልከት አድነኝም።

154. ፍርዴን ፍረድ አድነኝም፤ ስለ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።

155. መድኃኒት ከኅጥኣን ሩቅ ነው፥ ሥርዓትህን አልፈለጉምና።

156. አቤቱ፥ ቸርነትህ እጅግ ብዙ ነው፤ እንደ ፍርድህ ሕያው አድርገኝ።

157. ያሳደዱኝና ያስጨነቁኝ ብዙዎች ናቸው፤ ከምስክር ግን ፈቀቅ አላልሁም።

158. ቃልህን አልጠበቁምና ሰነፎችን አይቼ አዘንሁ።

159. ትእዛዝህን እንደ ወደድሁ ተመልከት፤ አቤቱ፥ በምሕረትህ ሕያው አድርገኝ።

160. የቃልህ መጀመሪያ እውነት ነው፥ የጽድቅህንም ፍርድ ሁሉ ለዘላለም ነው። ሳን

161. ገዢዎች በከንቱ አሳደዱኝ፤ ከቃልህ የተነሣ ግን ልቤ ደነገጠብኝ።

162. ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ።

163. ዓመፃን ጠላሁ ተጸየፍሁም፤ ሕግን ግን ወደድሁ።

164. ስለ ጽድቅህ ፍርድ ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንሃለሁ።

165. ሕግህን ለሚወድዱ ብዙ ሰላም ነው፥ ዕንቅፋትም የለባቸውም።

166. አቤቱ፥ ማዳንህን ተስፋ አደርግሁ፥ ትእዛዛትህንም ጠበቅሁ።

167. ነፍሴ ምስክርህን ጠበቀች እጅግም ወደደችው።

168. መንገዶቼ ሁሉ በፊትህ ናቸውና ትእዛዝህንና ምስክርህን ጠበቅሁ። ታው

169. አቤቱ፥ ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትቅረብ፤ እንደ ቃልህም አስተዋይ አድርገኝ።

170. ልመናዬ ወደ ፊትህ ትድረስ፤ እንደ ቃልህ አድነኝ።

171. ሥርዓትህን አስተምረኸኛልና ከንፈሮቼ ምስጋናን አወጡ።

172. ትእዛዛትህ ሁሉ ጽድቅ ናቸውና አንደበቴ ቃልህን ተናገረ።

173. ትእዛዛትህን መርጫለሁና እጅህ የሚያድነኝ ይሁን።

174. አቤቱ፥ ማዳንህን ናፈቅሁ፤ ሕግህም ተድላዬ ነው።

175. ነፍሴ ትኑርልኝ ታመሰግንህማለች፥ ፍርድህም ይርዳኝ።

176. እንደ ጠፉ በግ ተቅበዘበዝሁ፤ ትእዛዛትህን አልረሳሁምና ባሪያህን ፈልገው።

About መዝሙረ ዳዊት Chapter 119

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 119 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: መዝሙረ ዳዊት
Chapter: 119
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መዝሙረ ዳዊት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading መዝሙረ ዳዊት Chapter 119 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is መዝሙረ ዳዊት Chapter 119?

መዝሙረ ዳዊት Chapter 119 is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete መዝሙረ ዳዊት Chapter 119 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from መዝሙረ ዳዊት

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 112
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 59
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 55
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 120
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 1
  6. መዝሙረ ዳዊት Chapter 147
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 134

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ዘኍልቍ Chapter 12
  2. ዘኍልቍ Chapter 26
  3. ኢዮብ Chapter 1
  4. ዘዳግም Chapter 16
  5. ኢሳይያስ Chapter 5
  6. ዘጸአት Chapter 17
  7. አሞጽ Chapter 3

Related Chapters & Readings

  1. ሉቃስ Chapter 21
  2. ነህምያ Chapter 4
  3. ዘዳግም Chapter 5
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 90
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 141
  6. ኤርምያስ Chapter 4
  7. የሐዋርያት ሥራ Chapter 22
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *