መዝሙረ ዳዊት Chapter 38

For English

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 38 Online

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 38 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መዝሙረ ዳዊት and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

መዝሙረ ዳዊት 38

ምዕራፍ 38

1. አቤቱ፥ በቍጣህ አትቅሠፈኝ፥ በመዓትህም አትገሥጸኝ።

2. ፍላጾችህ ወግተውኛልና፥ እጅህንም አክብደህብኛልና።

3. ከቍጣህ የተነሣ ለሥጋዬ ጤና የለውም፤ ከኃጢአቴም የተነሣ ለአጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።

4. ኃጢአቴ በራሴ ላይ ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ እንደ ከባድ ሸክምም በላዬ ከብዶአልና።

5. ከስንፍናዬ የተነሣ ቍስሌ ሸተተ በሰበሰም፤

6. እጅግ ጐሰቈልሁ ተዋረድሁም፥ ሁልጊዜም በትካዜ እመላለሳለሁ።

7. ነፍሴ ስድብን ተሞልታለችና፥ ለሥጋዬም ጤና የላትምና።

8. ታመምሁ፤ እጅግም ተቸገርሁ፥ ከልቤ ውዝዋዜም የተነሣ ጮኽሁ።

9. አቤቱ፥ ፈቃዴ ሁሉ በፊትህ ነው፥ ጭንቀቴም ከአንተ አይሰወርም።

10. ልቤ ደነገጠብኝ፥ ኃይሌም ተወችኝ፥ የዓይኖቼም ብርሃን ፈዘዘ።

11. ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ከቍስሌ ገለል ብለው ቆሙ፥ ዘመዶቼም ርቀው ቆሙ።

12. ነፍሴንም የሚሹአት በረቱብኝ፥ መከራዬንም የሚፈልጉ ከንቱን ተናገሩ፥ ሁልጊዜም በሽንገላ ይመክራሉ።

13. እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቆሮ አፉንም እንደማይከፍት ዲዳ ሆንሁ።

14. እንደማይሰማ ሰው በአፉም ተግሣጽ እንደሌለው ሰው ሆንሁ።

15. አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና፤ አቤቱ አምላኬ፥ አንተ ትሰማኛለህ።

16. ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ እንዳይላቸው ብያለሁና፥ እግሮቼም ቢሰናከሉ ራሳቸውን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ ያደርጋሉ።

17. እኔስ ወደ ማንከስ ቀርቤአለሁና፥ ቍስሌም ሁልጊዜም በፊቴ ነውና።

18. በደሌን እናገራለሁና፥ ስለ ኃጢአቴም እተክዛለሁ።

19. ጠላቶቼ ሕያዋን ናቸው ይበረቱብኝማል፥ በጠማማነትም የሚጠሉኝ በዙ።

20. ጽድቅን ስለ ተከተልሁ፥ በበጎ ፋንታ ክፉን የሚመልሱልኝ ይጠሉኛል።

21. አቤቱ፥ አንተ አትጣለኝ፤ አምላኬ፥ ከኔ አትራቅ።

22. አቤቱ መድኃኒቴ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።

About መዝሙረ ዳዊት Chapter 38

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 38 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: መዝሙረ ዳዊት
Chapter: 38
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መዝሙረ ዳዊት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading መዝሙረ ዳዊት Chapter 38 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is መዝሙረ ዳዊት Chapter 38?

መዝሙረ ዳዊት Chapter 38 is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete መዝሙረ ዳዊት Chapter 38 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from መዝሙረ ዳዊት

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 112
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 59
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 55
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 147
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 122
  6. መዝሙረ ዳዊት Chapter 120
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 1

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ሕዝቅኤል Chapter 44
  2. ዘጸአት Chapter 15
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 60
  4. ዘሌዋውያን Chapter 12
  5. መኃልየ መኃልይ Chapter 8
  6. ዘዳግም Chapter 32
  7. ሶፎንያስ Chapter 1

Related Chapters & Readings

  1. ዘኍልቍ Chapter 1
  2. መሳፍንት Chapter 10
  3. ዘሌዋውያን Chapter 15
  4. 2 ነገሥት Chapter 7
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 20
  6. ማቴዎስ Chapter 17
  7. 2 ዜና መዋዕል Chapter 28
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *