Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 109 Online
Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 109 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መዝሙረ ዳዊት and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
መዝሙረ ዳዊት 109
ምዕራፍ 109
1. አምላክ ሆይ፥ ምሥጋናዬን ዝም አትበል፥
2. የኃጢአተኛ አፍና የተንኰለኛ አፍ በላዬ ተላቅቀውብኛልና፤ በሽንገላ አንደበትም በላዬ ተናገሩ፤
3. በጥል ቃል ከበቡኝ፥ በከንቱም ተሰለፉብኝ።
4. በወደድኋቸው ፋንታ አጣሉኝ፥ እኔ ግን እጸልያለሁ።
5. በመልካም ፋንታ ክፉን በወደድኋቸውም ፋንታ ጠላትነትን መለሱልኝ።
6. በላዩ ኃጢአተኛን ሹም፤ ሰይጣንም በቀኙ ይቁም።
7. በተምዋገተም ጊዜ ተረትቶ ይውጣ፤ ጸሎቱም ኃጢአት ትሁንበት።
8. ዘመኖቹም ጥቂት ይሁኑ፤ ሹመቱንም ሌላ ይውሰድ።
9. ልጆቹም ድሀ አደግ ይሁኑ፥ ሚስቱም መበለት ትሁን።
10. ልጆቹም ተናውጠው ይቅበዝበዙ ይለምኑም፥ ከስፍራቸውም ይባረሩ።
11. ባለዕዳም ያለውን ሁሉ ይበርብረው፥ እንግዶችም ድካሙን ሁሉ ይበዝብዙት።
12. የሚያግዘውንም አያግኝ። ለድሀ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር።
13. ልጆቹ ይጥፉ፤ በአንድ ትውልድ ስሙ ይደምሰስ።
14. የአባቶቹ ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት ትታሰብ፤ የእናቱም ኃጢአት አትደምሰስ።
15. በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ ይኑሩ፤ መታሰቢያቸው ከምድር ይጥፋ።
16. ምሕረትን ያደርግ ዘንድ አላሰበምና ችግረኛንና ምስኪንን ልቡ የተሰበረውንም ሰው ይገድል ዘንድ አሳደደ።
17. መርገምን ወደደ ወደ እርሱም መጣች፤ በረከትንም አልመረጠም ከእርሱም ራቀች።
18. መርገምን እንደ ልብስ ለበሳት፥ እንደ ውኃም ወደ አንጀቱ፥ እንደ ቅባትም ወደ አጥንቱ ገባች።
19. እንደሚለብሰው ልብስ። ሁልጊዜም እንደሚታጠቀው ትጥቅ ይሁነው።
20. ይህ ሥራ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሚያጣሉኝ በነፍሴም ላይ ክፉን በሚናገሩ ነው።
21. አንተ ግን አቤቱ ጌታዬ፥ ስለ ስምህ ምሕረትህን በእኔ ላይ አድርግ፤ ምሕረትህ መልካም ናትና አድነኝ።
22. እኔ ችግረኛ ምስኪንም ነኝና፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ።
23. እንዳለፈ ጥላ አለቅሁ፥ እንደ አንበጣም እረገፍሁ።
24. ጕልበቶቼ በጾም ደከሙ፤ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ።
25. እኔም በእነርሱ ዘንድ ለነውር ሆንሁ፤ ባዩኝ ጊዜ ራሳቸውን ነቀነቁ።
26. አቤቱ አምላኬ፥ እርዳኝ፥ እንደ ምሕረትህም አድነኝ።
27. አቤቱ፥ እጅህ ይህች እንደ ሆነች፥ አንተም ይህችን እንዳደረግህ ይወቁ።
28. እነርሱ ይራገማሉ አንተ ግን ባርክ፤ በእኔ ላይ የሚነሡ ይፈሩ፥ ባሪያህ ግን ደስ ይበለው።
29. የሚያጣሉኝ እፍረትን ይልበሱ፤ እፍረታቸውን እንደ መጐናጸፊያ ይልበሱአት።
30. እግዚአብሔርን በአፌ እጅግ አመሰግነዋለሁ። በብዙዎችም መካከል አከብረዋለሁ፤
31. ነፍሱን ከሚያሳድዱአት ያድን ዘንድ በድሀ ቀኝ ቆሞአልና።
About መዝሙረ ዳዊት Chapter 109
Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 109 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: መዝሙረ ዳዊት
Chapter: 109
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መዝሙረ ዳዊት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading መዝሙረ ዳዊት Chapter 109 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is መዝሙረ ዳዊት Chapter 109?
መዝሙረ ዳዊት Chapter 109 is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete መዝሙረ ዳዊት Chapter 109 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from መዝሙረ ዳዊት
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 112
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 59
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 55
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 1
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 147
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 134
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 122
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- ኤርምያስ Chapter 42
- ኢሳይያስ Chapter 33
- 1 ሳሙኤል Chapter 16
- ሕዝቅኤል Chapter 27
- ዳንኤል Chapter 1
- 1 ሳሙኤል Chapter 25
- ኤርምያስ Chapter 4