Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 139 Online
Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 139 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መዝሙረ ዳዊት and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
መዝሙረ ዳዊት 139
ምዕራፍ 139
1. አቤቱ፥ መረመርኸኝ፥ አወቅኸኝም።
2. አንተ መቀመጤንና መነሣቴን አወቅህ፤ አሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ።
3. ፍለጋዬንና ዕረፍቴን አንተ መረመርህ፤ መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ አወቅህ፥
4. የዓመፃ ቃል በአንደበቴ እንደሌለ።
5. አቤቱ፥ አንተ እነሆ የቀድሞውንና የኋላውን አወቅህ፤ አንተ ፈጠርኸኝ፥ እጅህንም በላዬ አደረግህ።
6. እውቀትህ ከእኔ ይልቅ ተደነቀች፤ በረታች፥ ወደ እርስዋም ለመድረስ አልችልም።
7. ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?
8. ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ። ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ።
9. እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥
10. በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች።
11. በውኑ ጨለማ ትሸፍነኛለች ብል፥ ሌሊት በዙሪያዬ ብርሃን ትሆናለች፤
12. ጨለማ በአንተ ዘንድ አይጨልምምና፥ ሌሊትም እንደ ቀን ታበራለችና፤ እንደ ጨለማዋ እንዲሁ ብርሃንዋ ነው።
13. አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን ፈጥረሃልና፥ በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል።
14. ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።
15. እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፥ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም።
16. ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ።
17. አቤቱ፥ አሳቦችህ በእኔ ዘንድ እንደ ምን እጅግ የተከበሩ ናቸው! ቍጥራቸውም እንደ ምን በዛ!
18. ብቈጥራቸው ከአሸዋ ይልቅ ይበዛሉ፤ ተነሣሁም፥ እኔም ገና ከአንተ ጋር ነኝ።
19. አቤቱ፥ አንተ ኃጢአተኞችን የምትገድል ከሆንህስ፥ የደም ሰዎች ሆይ፥ ከእኔ ፈቀቅ በሉ።
20. በክፋት ይናገሩብሃልና፤ ጠላቶችህም በከንቱ ያምፁብሃል።
21. አቤቱ፥ የሚጠሉህን እኔ የጠላሁ አይደለሁምን? ስለ ጠላቶችህም አልተሰቀቅሁምን?
22. ፍጹም ጥል ጠላኋቸው፥ ጠላቶችም ሆኑኝ።
23. አቤቱ፥ መርምረኝ ልቤንም እወቅ፤ ፍተነኝ መንገዴንም እወቅ፤
24. በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ፤ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ።
About መዝሙረ ዳዊት Chapter 139
Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 139 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: መዝሙረ ዳዊት
Chapter: 139
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መዝሙረ ዳዊት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading መዝሙረ ዳዊት Chapter 139 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is መዝሙረ ዳዊት Chapter 139?
መዝሙረ ዳዊት Chapter 139 is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete መዝሙረ ዳዊት Chapter 139 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from መዝሙረ ዳዊት
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 112
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 59
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 55
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 120
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 1
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 147
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 134
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 114
- ዘኍልቍ Chapter 21
- ዘዳግም Chapter 26
- 2 ዜና መዋዕል Chapter 5
- ዘፍጥረት Chapter 25
- አሞጽ Chapter 6
- ኢሳይያስ Chapter 13