ማርቆስ Chapter 16

For English

Read ማርቆስ Chapter 16 Online

Read ማርቆስ Chapter 16 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ማርቆስ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ማርቆስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ማርቆስ 16

ምዕራፍ 16

1. ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም የያዕቆብም እናት ማርያም ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቱ ገዙ።

2. ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን እጅግ በማለዳ ፀሐይ ከወጣ በኋላ ወደ መቃብር መጡ።

3. እርስ በርሳቸውም። ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል? ይባባሉ ነበር፤

4. ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርና፤ አሻቅበውም አይተው ድንጋዩ ተንከባሎ እንደ ነበር ተመለከቱ።

5. ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጎናጸፈ ጎልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ።

6. እርሱ ግን። አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ።

7. ነገር ግን ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ለጴጥሮስም። ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፤ እንደ ነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው አላቸው።

8. መንቀጥቀጥና መደንገጥ ይዞአቸው ነበርና ወጥተው ከመቃብር ሸሹ፤ ይፈሩ ነበርና ለማንም አንዳች አልነገሩም። እነርሱም ያዘዛቸውን ሁሉ ለጴጥሮስና ከእርሱ ጋር ላሉት በአጭሩ ተናገሩ። ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ራሱ ለዘላለም ድኅነት የሆነውን የማይለወጠውን ቅዱስ ወንጌል ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያው ድረስ በእጃቸው ላከው።

9. ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜ፥ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ።

10. እርስዋ ሄዳ ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው፤

11. እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርስዋም እንደ ታያት ሲሰሙ አላመኑም።

12. ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ለሁለቱ ወደ ባላገር ሲሄዱ በመንገድ በሌላ መልክ ተገለጠ፤

13. እነርሱም ሄደው ለሌሎቹ አወሩ፤ እነዚያንም ደግሞ አላመኑአቸውም።

14. ኋላም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለአሥራ አንዱ ተገለጠ፥ ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውንና የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ።

15. እንዲህም አላቸው። ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።

16. ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።

17. ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥

18. የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ።

19. ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።

20. እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።

About ማርቆስ Chapter 16

Read ማርቆስ Chapter 16 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ማርቆስ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ማርቆስ
Chapter: 16
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ማርቆስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ማርቆስ Chapter 16 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ማርቆስ Chapter 16?

ማርቆስ Chapter 16 is part of the Book of ማርቆስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ማርቆስ Chapter 16 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ማርቆስ

  1. ማርቆስ Chapter 10
  2. ማርቆስ Chapter 8
  3. ማርቆስ Chapter 1
  4. ማርቆስ Chapter 2
  5. ማርቆስ Chapter 15
  6. ማርቆስ Chapter 14
  7. ማርቆስ Chapter 7

Explore More from አዲስ ኪዳን

  1. ዮሐንስ Chapter 4
  2. የሐዋርያት ሥራ Chapter 6
  3. ቲቶ Chapter 1
  4. 2 ተሰሎንቄ Chapter 2
  5. ኤፌሶን Chapter 6
  6. 2 ቆሮንቶስ Chapter 8
  7. ማርቆስ Chapter 11

Related Chapters & Readings

  1. ዘሌዋውያን Chapter 27
  2. ዕንባቆም Chapter 2
  3. ዘሌዋውያን Chapter 5
  4. ኢያሱ Chapter 1
  5. ዘፍጥረት Chapter 46
  6. ምሳሌ Chapter 11
  7. ዮሐንስ Chapter 4
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *