2 ዜና መዋዕል Chapter 5

For English

Read 2 ዜና መዋዕል Chapter 5 Online

Read 2 ዜና መዋዕል Chapter 5 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ዜና መዋዕል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 2 ዜና መዋዕል and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

2 ዜና መዋዕል 5

ምዕራፍ 5

1. እንዲሁም ሰሎሞን ስለ እግዚአብሔር ቤት የሠራው ሥራ ሁሉ ተጨረሰ። አባቱም ዳዊት የቀደሰውን የብርና የወርቅ ዕቃ ሁሉ ሰሎሞን አምጥቶ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በነበረው ግምጃ ቤት አኖረው።

2. ፤ በዚያን ጊዜም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያወጡ ዘንድ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆች ሁሉ የእስራኤልንም ልጆች አባቶች ቤቶች መሳፍንት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።

3. ፤ የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ በሰባተኛው ወር በበዓሉ ጊዜ ጊዜ ወደ ንጉሡ ተከማቹ።

4. ፤ የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ፥ ሌዋውያንም ታቦቱን አነሡ።

5. ፤ ታቦቱንም የመገናኛውንም ድንኳን በድኳኑም ውስጥ የነበረውን የተቀደሰውን ዕቃ ሁሉ አመጡ፤ እነዚህንም ሁሉ ካህናቱና ሌዋውያኑ አመጡ።

6. ፤ ንጉሡም ሰሎሞን ከእርሱም ጋር የተሰበሰቡ የእስራኤል ማኅበር ሁሉ በታቦቱ ፊት ሆነው ከብዛት የተነሣ የማይቈጠሩትንና የማይመጠኑትን በጎችና በሬዎች ይሠዉ ነበር።

7. ፤ ካህናቱም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤቱ አምጥተው በቅድስት ቅዱሳን ውስጥ ከኪሩቤል ክንፍ በታች በነበረው በስፍራው አኖሩት።

8. ፤ ኪሩቤልም በታቦቱ ስፍራ ላይ ክንፎቻቸውን ዘርግተው ነበር፥ ኪሩቤልም ታቦቱንና መሎጊያዎቹን በስተ ላዩ በኩል ይሸፍኑ ነበር።

9. ፤ መሎጊያዎቹም ረጃጅሞች ነበሩና በቅዱስተ ቅዱሳን ፊት ከመቅደሱ ውስጥ ጫፎቻቸው ይታዩ ነበር፤ ነገር ግን ከውጪ አይታዩም ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ እዚያ አሉ።

10. ፤ በታቦቱም ውስጥ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ፥ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ ሙሴ በኮሬብ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ ጽላቶች በቀር ምንም አልነበረበትም።

11. ፤ በዚያም የነበሩት ካህናት ሁሉ ተቀድሰው ነበር፥ በሰሞናቸውም አልተከፈሉም ነበር፤

12. ፤ መዘምራንም የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፥ አሳፍና ኤማን ኤዶታምም ልጆቻቸውም ወንድሞቻቸውም፥ ጥሩ በፍታ ለብሰው ጸናጽልና በገና መሰንቆም እየመቱ በመሠዊያው አጠገብ በመሥራቅ በኩል ቆመው ነበር፤ ከእነርሱም ጋር መቶ ሀያ ካህናት መለከት ይነፉ ነበር። ካህናቱም ከመቅደሱ በወጡ ጊዜ፥

13. ፤ መለከቱንም የሚነፉ መዘምራኑም በአንድነት ሆነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ። እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ እያሉ በአንድ ቃል ድምፃቸውን ወደ ላይ ከፍ አድገው በመለከትና በጸናጽል በዜማም ዕቃ ሁሉ እግዚአብሔርን ባመሰገኑ ጊዜ፥ ደመናው የእግዚአብሔርን ቤት ሞላው።

14. ፤ የእግዚአብሔርም ክብር የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶት ነበርና ካህናቱ ከደመናው የተነሣ መቆምና ማገልገል አልተቻላቸውም።

About 2 ዜና መዋዕል Chapter 5

Read 2 ዜና መዋዕል Chapter 5 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ዜና መዋዕል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 2 ዜና መዋዕል
Chapter: 5
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 2 ዜና መዋዕል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 2 ዜና መዋዕል Chapter 5 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 2 ዜና መዋዕል Chapter 5?

2 ዜና መዋዕል Chapter 5 is part of the Book of 2 ዜና መዋዕል in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 2 ዜና መዋዕል Chapter 5 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 2 ዜና-መዋዕል

  1. 2 ዜና መዋዕል Chapter 36
  2. 2 ዜና መዋዕል Chapter 19
  3. 2 ዜና መዋዕል Chapter 16
  4. 2 ዜና መዋዕል Chapter 14
  5. 2 ዜና መዋዕል Chapter 34
  6. 2 ዜና መዋዕል Chapter 26
  7. 2 ዜና መዋዕል Chapter 24

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. መሳፍንት Chapter 3
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 131
  3. ሕዝቅኤል Chapter 33
  4. 2 ዜና መዋዕል Chapter 26
  5. ምሳሌ Chapter 22
  6. ኢዮብ Chapter 12
  7. 2 ሳሙኤል Chapter 17

Related Chapters & Readings

  1. 1 ዜና መዋዕል Chapter 24
  2. ኤርምያስ Chapter 20
  3. ኢሳይያስ Chapter 40
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 133
  5. 2 ዜና መዋዕል Chapter 8
  6. ሉቃስ Chapter 12
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 7
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *