መዝሙረ ዳዊት Chapter 89

For English

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 89 Online

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 89 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መዝሙረ ዳዊት and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

A+ A A-

መዝሙረ ዳዊት 89

ምዕራፍ 89

1. አቤቱ፥ ምሕረትህን ለዘላለም እዘምራለሁ፥ እውነትህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ።

2. እንዲህ ብለሃልና። ምሕረት ለዘላለም ይመሠረታል፥ እውነትህም በሰማይ ይጸናል።

3. ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ፥ ለባሪያዬም ለዳዊት ማልሁ።

4. ዘርህን ለዘላለም አዘጋጃለሁ፥ ዙፋንህንም ለልጅ ልጅ እመሠርታለሁ።

5. አቤቱ፥ ሰማያት ተኣምራትህን እውነትህንም ደግሞ በቅዱሳን ማኅበር ያመሰግናሉ።

6. እግዚአብሔርን በሰማይ የሚተካከለው ማን ነው? ከአማልክትስ ልጆች እግዚአብሔርን ማን ይመስለዋል?

7. በቅዱሳን ምክር እግዚአብሔር ክቡር ነው፤ በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው።

8. አቤቱ የሠራዊት አምላክ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? አቤቱ፥ አንተ ብርቱ ነህ፥ እውነትህም ይከብብሃል።

9. የባሕርን ኃይል አንተ ትገዛለህ፥ የሞገዱንም መናወጥ አንተ ዝም ታሰኘዋለህ።

10. አንተ ረዓብን እንደ ተገደለ አዋረድኸው፥ በኃይልህም ክንድ ጠላቶችህን በተንሃቸው።

11. ሰማያት የአንተ ናቸው፥ ምድርም የአንተ ናት፤ ዓለምንና ሞላውም አንተ መሠረትህ።

12. ሰሜንና ደቡብን አንተ ፈጠርህ፤ ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል።

13. ክንድህ ከኃይልህ ጋር ነው፤ እጅህ በረታች ቀኝህም ከፍ ከፍ አለች።

14. የዙፋንህ መሠረት ጽድቅና ፍርድ ነው፤ ምሕረትና እውነት በፊትህ ይሄዳሉ።

15. እልልታ የሚያውቅ ሕዝብ ምስጉን ነው፤ አቤቱ፥ በፊትህ ብርሃን ይሄዳሉ።

16. በስምህ ቀኑን ሁሉ ደስ ይላቸዋል፥ በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ፤

17. የኃይላቸው ትምክሕት አንተ ነህና፥ በሞገስህም ቀንዳችን ከፍ ከፍ ይላልና።

18. ረድኤታችን ከእግዚአብሔር ከንጉሣችንም ከእስራኤል ቅዱስ ነውና።

19. በዚያ ጊዜ ለልጆችህ በራእይ ተናገርህ እንዲህም አልህ። ረድኤቴን በኃይል ላይ አኖርሁ፤ ከሕዝቤ የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግሁ።

20. ባሪያዬን ዳዊትን አገኘሁት፥ ቅዱስ ዘይትም ቀባሁት።

21. እጄም ትረዳዋለች፥ ክንዴም ታጸናዋለች።

22. ጠላት በእርሱ ላይ አይጠቀምም፥ የዓመፃ ልጅም መከራ አይጨምርበትም።

23. ጠላቶቹን ከፊቱ አጠፋለሁ፥ የሚጠሉትንም አዋርዳቸዋለሁ።

24. እውነቴና ምሕረቴም ከእርሱ ጋር ነው፥ በስሜም ቀንዱ ከፍ ከፍ ይላል።

25. እጁን በባሕር ላይ ቀኙንም በወንዞች ላይ አኖራለሁ።

26. እርሱ። አባቴ አንተ ነህ፥ አምላኬ የመድኃኒቴም መጠጊያ ይላል።

27. እኔም ደግሞ በኵሬ አደርገዋለሁ፥ ከምድር ነገሥታትም ከፍ ይላል።

28. ለዘላለምም ምሕረቴን ለእርሱ እጠብቃለሁ፥ ኪዳኔም በእርሱ ዘንድ የታመነ ነው።

29. ዘሩንም ለዓለምና ለዘላለም፥ ዙፋኑንም እንደ ሰማይ ዘመን አደርጋለሁ።

30. ልጆቹ ግን ሕጌን ቢተዉ፥ በፍርዴም ባይሄዱ፤

31. ሥርዓቴንም ቢያረክሱ፥ ትእዛዜንም ባይጠብቁ፤

32. ኃጢአታቸውን በበትር፥ በደላቸውንም በመቅሠፍት እጐበኛታለሁ።

33. ምሕረቴን ግን ከእርሱ አላርቅም፥ በእውነቴም አልበድልም፤

34. ኪዳኔንም አላረክስም፥ ከከንፈሬም የወጣውን አልለውጥም።

35. ዳዊትን እንዳልዋሸው አንድ ጊዜ በቅዱስነቴ ማልሁ።

36. ዘሩ ለዘላለም፥ ዙፋኑም በፊቴ እንደ ፀሐይ ይኖራል።

37. ለዘላለም እንደ ጨረቃ ይጸናል፤ ምስክርነቱ በሰማይ የታመን ነው።

38. አንተ ግን ናቅኸው ጣልኸውም፥ የቀባኸውንም ጣልኸው።

39. የባሪያህንም ኪዳን አፈረስህ፥ መቅደሱንም በምድር አረከስህ።

40. ቅጥሩን ሁሉ ጣልህ፥ አምባዎቹንም አጠፋህ።

41. መንገድ አላፊም ሁሉ ተናጠቀው፥ ለጎረቤቶቹም ስድብ ሆነ።

42. የጠላቶቹንም ቀኝ ከፍ ከፍ አደረግህ፥ ጠላቶቹንም ሁሉ ደስ አሰኘህ።

43. የሰይፉንም ረድኤት መለስህ፥ በሰልፍም ውስጥ አልደገፍኸውም።

44. ከንጽሕናውም ሻርኸው፥ ዙፋኑንም በምድር ጣልህ።

45. የዙፋኑንም ዘመን አሳነስህ፥ በእፍረትም ሸፈንኸው።

46. አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘላለም ፊትህን ትመልሳለህ? እስከ መቼስ ቍጣህ እንደ እሳት ይነድዳል?

47. ችሎታዬ ምን እንደ ሆነ አስብ፤ በውኑ የሰውን ልጅ ሁሉ ለከንቱ ፈጠርኸውን?

48. ሕያው ሆኖ የሚኖር፥ ሞትንስ የማያይ ማን ነው? ነፍሱንስ ከሲኦል እጅ የሚያድን ማን ነው?

49. ለዳዊት በእውነት የማልህ፥ አቤቱ፥ የቀድሞ ምሕረትህ ወዴት ነው?

50. አቤቱ፥ የባሪያዎችህን ስድብ፥ በብብቴ ብዙ አሕዛብን የተቀበልሁትን፥

51. አቤቱ፥ ጠላቶችህን የሰደቡትን የቀባኸውን ዘመን የሰደቡትን አስብ።

52. እግዚአብሔር ለዘላለም ይባረክ። ይሁን ይሁን።

About መዝሙረ ዳዊት Chapter 89

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 89 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: መዝሙረ ዳዊት
Chapter: 89
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መዝሙረ ዳዊት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading መዝሙረ ዳዊት Chapter 89 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is መዝሙረ ዳዊት Chapter 89?

መዝሙረ ዳዊት Chapter 89 is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete መዝሙረ ዳዊት Chapter 89 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from መዝሙረ ዳዊት

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 112
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 59
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 55
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 147
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 122
  6. መዝሙረ ዳዊት Chapter 120
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 1

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 15
  2. ኢያሱ Chapter 24
  3. ነህምያ Chapter 10
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 79
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 22
  6. 1 ዜና መዋዕል Chapter 11
  7. መሳፍንት Chapter 5

Related Chapters & Readings

  1. ዕብራውያን Chapter 13
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 127
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 58
  4. 1 ነገሥት Chapter 4
  5. ሆሴዕ Chapter 5
  6. 2 ዜና መዋዕል Chapter 35
  7. ኢሳይያስ Chapter 13
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *