መዝሙረ ዳዊት Chapter 147

For English

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 147 Online

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 147 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መዝሙረ ዳዊት and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

መዝሙረ ዳዊት 147

ምዕራፍ 147

1. እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ መዝሙር መልካም ነውና። ለአምላካችን ምስጋና ያማረ ነው።

2. እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይሠራል፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ይሰበስባል።

3. ልባቸውን የቈሰሉትን ይፈውሳል፥ ሕማማቸውንም ይጠግናል።

4. የከዋክብትንም ብዛት ይቈጥራል፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።

5. ጌታችን ታላቅ ነው፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ ለጥበቡም ቍጥር የለውም።

6. እግዚአብሔር የዋሃንን ያነሣል፥ ኃጢአተኞችን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋርዳል።

7. ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፥ ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ፤

8. ሰማዩን በደመናት ይሸፍናል ለምድርም ዝናብን ያዘጋጃል፤ ሣርን በተራሮች ላይ ያበቅላል፤ ለምለሙንም ለሰው ልጆች ጥቅም።

9. ለሚጠሩት ለቍራዎች ጫጩቶች ለእንስሶችም ምግባቸውን ይሰጣል።

10. የፈረስን ኃይል አይወድድም፥ በሰውም ጭን አይደሰትም።

11. እግዚአብሔር በሚፈሩት፥ በምሕረቱም በሚታመኑት ይደሰታል።

12. ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኚ፥

13. ጽዮንም ሆይ፥ ለአምላክሽ እልል በዪ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥ ልጆችንም በውስጥሽ ባርኮአልና።

14. በወሰንሽም ሰላምን አደረገ፥ የስንዴንም ስብ አጠገበሽ።

15. ነገሩን ወደ ምድር ይሰድዳል፥ ቃሉም እጅግ ፈጥኖ ይሮጣል።

16. አመዳዩን እንደ ባዘቶ ይሰጣል፤ ጉሙን እንደ አመድ ይበትነዋል፤

17. በረዶውን እንደ ፍርፋሪ ያወርዳል፤ በበረዶውስ ፊት ማን ይቆማል?

18. ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፥ ውኆችንም ያፈስሳል።

19. ቃሉን ለያዕቆብ፥ ሥርዓቱንና ፍርዱን ለእስራኤል ይናገራል።

20. ለሌሎች አሕዛብ ሁሉ እንዲህ አላደረገም፥ ፍርዱንም አልገለጠላቸውም። ሃሌ ሉያ።

About መዝሙረ ዳዊት Chapter 147

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 147 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: መዝሙረ ዳዊት
Chapter: 147
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መዝሙረ ዳዊት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading መዝሙረ ዳዊት Chapter 147 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is መዝሙረ ዳዊት Chapter 147?

መዝሙረ ዳዊት Chapter 147 is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete መዝሙረ ዳዊት Chapter 147 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from መዝሙረ ዳዊት

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 112
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 55
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 59
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 24
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 1
  6. መዝሙረ ዳዊት Chapter 148
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 134

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 114
  2. ሕዝቅኤል Chapter 34
  3. ዘኍልቍ Chapter 7
  4. 1 ዜና መዋዕል Chapter 19
  5. ዘካርያስ Chapter 9
  6. ኢሳይያስ Chapter 10
  7. 2 ዜና መዋዕል Chapter 15

Related Chapters & Readings

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 90
  2. ዘጸአት Chapter 32
  3. 1 ዮሐንስ Chapter 3
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 19
  5. ምሳሌ Chapter 17
  6. ዘዳግም Chapter 17
  7. 1 ጴጥሮስ Chapter 2
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *