መዝሙረ ዳዊት Chapter 104

For English

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 104 Online

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 104 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መዝሙረ ዳዊት and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

መዝሙረ ዳዊት 104

ምዕራፍ 104

1. ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፤ ክብርንና ግርማን ለበስህ።

2. ብርሃንን እንደ ልብስ ለበስህ፤ ሰማይንም እንደ መጋረጃ ዘረጋህ፤

3. እልፍኙን በውኃ የሚሠራ፥ ሰረገላውን ደመና የሚያደርግ፥ በነፋስ ክንፍም የሚሄድ፥

4. መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል።

5. ለዘላለም እንዳትናወጥ ምድርን በመሠረትዋ ላይ መሠረታት።

6. በጥልቅ እንደ ልብስ ከደንሃት፥ በተራሮችም ላይ ውኆች ይቆማሉ።

7. ከዘለፋህም ይሸሻሉ፥ ከነጐድጓድህም ድምፅ ይደነግጣሉ፤

8. ወደ ተራሮች ይወጣሉ፥ ወደ ቈላዎች ወዳዘጋጀህላቸው ስፍራ ይወርዳሉ፤

9. እንዳያልፉትም ድንበር አደረግህላቸው ምድርን ይከድኑ ዘንድ እንዳይመለሱ።

10. ምንጮችን ወደ ቈላዎች ይልካል፤ በተራሮች መካከል ውኆች ያልፋሉ፤

11. የዱር አራዊትን ሁሉ ያጠጣሉ፥ የበረሃ አህያዎችም ጥማታቸውን ይረካሉ።

12. የሰማይም ወፎች በእነርሱ ዘንድ ያድራሉ፥ በድንጋዩ ስንጥቅ መካከልም ይጮኻሉ።

13. ተራሮችን ከላይ የሚያጠጣቸው፤ ከሥራህ ፍሬ ምድር ትጠግባለች።

14. እንጀራን ከምድር ያወጣ ዘንድ ለምለሙን ለሰው ልጆች ጥቅም፥ ሣርንም ለእንስሳ ያበቅላል።

15. ወይን የሰውን ልብ ደስ ያሰኛል፥ ዘይትም ፊትን ያበራል፥ እህልም የሰውን ጕልበት ያጠነክራል።

16. የእግዚአብሔር ዛፎች እርሱም የተከላቸው የሊባኖስ ዝግባዎች ይጠግባሉ።

17. በዚያም ወፎች ይዋለዳሉ፥ የሽመላ ቤትም የእነርሱ ጎረቤት ነው።

18. ረጃጅም ተራራዎች ለዋላዎች፥ ድንጋዮችም ለእሽኮኮች መሸሻ ናቸው።

19. ጨረቃን ለጊዜዎች አደረገ፤ ፀሐይም መግቢያውን ያውቃል።

20. ጨለማ ታደርጋለህ ሌሊትም ይሆናል፤ በእርሱም የዱር አራዊት ሁሉ ይወጡበታል።

21. የአንበሳ ግልገሎች ለመንጠቅ ይጮኻሉ፥ ከእግዚአብሔርም ምግባቸውን ይሻሉ።

22. ፀሐይ ስትወጣ ይሰበሰባሉ በየዋሻቸውም ይተኛሉ።

23. ሰው ወደ ተግባሩ፥ እስኪመሽም ድረስ ወደ ሥራው ይወጣል።

24. አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ብዙ ነው፤ ሁሉን በጥበብ አደረግህ፥ ምድርም ከፍጥረትህ ተሞላች።

25. ይህች ባሕር ታላቅና ሰፊ ናት፤ በዚያ ስፍራ ቍጥር የሌለው ተንቀሳቃሽ፥ ታላላቆችና ታናናሾች እንስሶች አሉ።

26. በዚያ ጊዜ መርከቦች ይሄዳሉ፥ በዚያም ላይ የፈጠርኸው ዘንዶ ይጫወትበታል።

27. ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸው ዘንድ እነዚህ ሁሉ አንተን ተስፋ ያደርጋሉ።

28. በሰጠሃቸውም ጊዜ ይሰበስባሉ፤ እጅህን ትከፍታለህ፥ ከመልካም ነገርም ይጠግባሉ።

29. ፊትህን ስትሰውር ይደነግጣሉ፤ ነፍሳቸውን ታወጣለህ ይሞታሉም፥ ወደ አፈራቸውም ይመለሳሉ።

30. መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉም፥ የምድርንም ፊት ታድሳለህ።

31. የእግዚአብሔር ክብር ለዘላለም ይሁን፤ እግዚአብሔር በሥራው ደስ ይለዋል።

32. ምድርን ያያል እንድትንቀጠቀጥም ያደርጋል፤ ተራሮችን ይዳስሳል ይጤሳሉም።

33. በሕይወቴ ሳለሁ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፥ ለአምላኬም በምኖርበት ዘመን ሁሉ እዘምራለሁ።

34. ቃሌ ለእርሱ ይጣፍጠው፥ እኔም በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል።

35. ኅጥኣን ከምድር ይጥፉ፤ ዓመፀኞች እንግዲህ አይገኙ። ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ። ሃሌ ሉያ።

About መዝሙረ ዳዊት Chapter 104

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 104 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: መዝሙረ ዳዊት
Chapter: 104
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መዝሙረ ዳዊት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading መዝሙረ ዳዊት Chapter 104 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is መዝሙረ ዳዊት Chapter 104?

መዝሙረ ዳዊት Chapter 104 is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete መዝሙረ ዳዊት Chapter 104 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from መዝሙረ ዳዊት

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 59
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 55
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 134
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 48
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 37
  6. መዝሙረ ዳዊት Chapter 137
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 122

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ዳንኤል Chapter 4
  2. ኢዮብ Chapter 40
  3. ዘፍጥረት Chapter 11
  4. ዘፍጥረት Chapter 25
  5. 2 ሳሙኤል Chapter 19
  6. 2 ዜና መዋዕል Chapter 23
  7. ዳንኤል Chapter 3

Related Chapters & Readings

  1. ዘዳግም Chapter 28
  2. ኢሳይያስ Chapter 56
  3. ኤርምያስ Chapter 30
  4. ዮሐንስ Chapter 2
  5. 1 ዜና መዋዕል Chapter 27
  6. መዝሙረ ዳዊት Chapter 53
  7. ምሳሌ Chapter 5
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *