መዝሙረ ዳዊት Chapter 69

For English

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 69 Online

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 69 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መዝሙረ ዳዊት and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

መዝሙረ ዳዊት 69

ምዕራፍ 69

1. አቤቱ፥ ውኃ እስከ ነፍሴ ደርሶብኛልና አድነኝ።

2. በጥልቅ ረግረግ ጠለቅሁ መቋሚያም የለኝም። ወደ ጥልቅ ባሕር ገባሁ ማዕበልም አሰጠመኝ።

3. በጩኸት ደከምሁ ጕሮሮዬም ሰለለ፤ አምላኬን ስጠብቅ ዓይኖቼ ፈዘዙ።

4. በከንቱ የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጕር በዙ፤ በዓመፅ ያሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ በረቱ፤ በዚያን ጊዜ ያልቀማሁትን መለስሁ።

5. አቤቱ፥ አንተ ስንፍናዬን ታውቃለህ፥ ኃጢአቴም ከአንተ አልተሰወረም።

6. አቤቱ የሠራዊት አምላክ፥ ተስፋ የሚያደርጉህ በእኔ አይፈሩ፤ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ የሚሹህ በእኔ አይነወሩ።

7. ስለ አንተ ስድብን ታግሻለሁና፥ እፍረትም ፊቴን ሸፍናለችና።

8. ለወንድሞቼ እንደ ሌላ፥ ለእናቴ ልጆችም እንደ እንግዳ ሆንሁባቸው፥

9. የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፥ የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና።

10. ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፥ ለስድብም ሆነብኝ።

11. ማቅ ለበስሁ ምሳሌም ሆንሁላቸው።

12. በደጅ የሚቀመጡ በእኔ ይጫወታሉ፤ ወይን የሚጠጡ እኔን ይዘፍናሉ።

13. አቤቱ፥ በመልካሙ ጊዜ ጸሎቴ ወደ አንተ ነው፤ አቤቱ፥ በምሕረትህ ብዛት በማዳንህም እውነት አድምጠኝ።

14. እንዳይውጠኝ ከረግረግ አውጣኝ፤ ከሚጠሉኝና ከጥልቅ ውኃ አስጥለኝ።

15. የውኃው ማዕበል አያስጥመኝ፥ ጥልቁም አይዋጠኝ፥ ጕድጓድም አፉን በእኔ ላይ አይዝጋ።

16. አቤቱ፥ ምሕረትህ መልካም ናትና ስማኝ። እንደ ርኅራኄህም ብዛት ወደ እኔ ተመልከት፤

17. ከባሪያህም ፊትህን አትሰውር፤ ተጨንቄአለሁና ፈጥነህ አድምጠኝ።

18. ነፍሴን ተመልክተህ ተቤዣት፤ ስለ ጠላቶቼም አድነኝ።

19. አንተ ስድቤን እፍረቴንም ነውሬንም ታውቃለህ፤ የሚያስጨንቁኝ ሁሉ በፊትህ ናቸው።

20. ነፍሴ ስድብንና ኃሣርን ታገሠች፤ አስተዛዛኝም ተመኘሁ አላገኘሁም። የሚያጽናናኝም አጣሁ።

21. ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፥ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ።

22. ማዕዳቸው በፊታቸው ለወጥመድ ለፍዳ ለዕንቅፋት ትሁንባቸው፤

23. ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፥ ጀርባቸውም ዘወትር ይጕበጥ።

24. መዓትህን በላያቸው አፍስስ፥ የቍጣህ መቅሠፍትም ያግኛቸው።

25. ማደሪያቸው በረሃ ትሁን፥ በድንኳኖቻቸውም የሚቀመጥ አይገኝ፤

26. አንተ የቀሠፍኸውን እነርሱ አሳድደዋልና፥ በቍስሌም ላይ ጥዝጣዜ ጨመሩብኝ።

27. በኃጢአታቸው ላይ ኃጢአትን ጨምርባቸው፥ በጽድቅህም አይግቡ።

28. ከሕያዋን መጽሐፍ ይደምሰሱ፥ ከጻድቃንም ጋር አይጻፉ።

29. እኔ ችግረኛና ቍስለኛ ነኝ፤ አቤቱ፥ የፊትህ መድኃኒት ይቀበለኝ።

30. የእግዚአብሔርን ስም በዝማሬ አመሰግናለሁ፥ በምስጋናም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።

31. ቀንድና ጥፍር ካበቀለ ከእምቦሳ ይልቅ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል።

32. ችግረኞች ያያሉ ደስ ይላቸዋል፤ እግዚአብሔርን ፈልጉ ሕያዋንም ሁኑ።

33. እግዚአብሔር ችግረኞችን ሰምቶአልና፥ እስረኞቹንም አልናቀምና።

34. ሰማይና ምድር ባሕርም በእርስዋም የሚንቀሳቀስ ሁሉ ያመሰግኑታል።

35. እግዚአብሔር ጽዮንን ያድናታልና፥ የይሁዳንም ከተሞች ይሠራልና፤ በዚያም ይቀመጣሉ ይወርሱአትማል።

36. የባሪያዎቹ ዘር ይኖሩባታል። ስሙንም የሚወድዱ በዚያ ይቀመጣሉ።

About መዝሙረ ዳዊት Chapter 69

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 69 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: መዝሙረ ዳዊት
Chapter: 69
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መዝሙረ ዳዊት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading መዝሙረ ዳዊት Chapter 69 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is መዝሙረ ዳዊት Chapter 69?

መዝሙረ ዳዊት Chapter 69 is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete መዝሙረ ዳዊት Chapter 69 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from መዝሙረ ዳዊት

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 112
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 55
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 147
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 59
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 48
  6. መዝሙረ ዳዊት Chapter 24
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 1

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 90
  2. 2 ዜና መዋዕል Chapter 3
  3. 2 ዜና መዋዕል Chapter 8
  4. 2 ሳሙኤል Chapter 7
  5. ሚክያስ Chapter 1
  6. ዘፍጥረት Chapter 2
  7. 2 ዜና መዋዕል Chapter 24

Related Chapters & Readings

  1. ምሳሌ Chapter 21
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 61
  3. 1 ሳሙኤል Chapter 28
  4. አስቴር Chapter 6
  5. 2 ቆሮንቶስ Chapter 8
  6. ዕብራውያን Chapter 2
  7. ነህምያ Chapter 5
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *