Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 106 Online
Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 106 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መዝሙረ ዳዊት and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
መዝሙረ ዳዊት 106
ምዕራፍ 106
1. ሃሌ ሉያ፤ ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ።
2. የእግዚአብሔርን ኃይል ሥራ ማን ይናገራል? ምስጋናውንስ ሁሉ ማን ያሰማል?
3. ፍርድን የሚጠብቁ፥ ጽድቅንም ሁልጊዜ የሚያደርጉ ምስጉኖች ናቸው።
4. አቤቱ፥ በሕዝብህ ሞገስ አስበን፥ በመድኃኒትህም ጐብኘን፤
5. የመረጥሃቸውን በጎነት እናይ ዘንድ፥ በሕዝብህም ደስታ ደስ ይለን ዘንድ፥ ከርስትህም ጋር እንጓደድ ዘንድ።
6. ከአባቶቻችን ጋር ኃጢአትን ሠራን፥ ዐመፅንም፥ በደልንም።
7. አባቶቻችን በግብጽ ሳሉ ተኣምራትህን አላስተዋሉም፥ የምሕረትህንም ብዛት አላሰቡም፤ በኤርትራ ባሕር ባለፉ ጊዜ ዐመፁብህ።
8. ኃይሉን ግን ለማስታወቅ። ስለ ስሙ አዳናቸው።
9. የኤርትራንም ባሕር ገሠጸ እርሱም ደረቀ፤ እንደ ምድረ በዳ በጥልቅ መራቸው።
10. ከሚጠሉአቸውም እጅ አዳናቸው፥ ከጠላትም እጅ ተቤዣቸው።
11. ያሳደዱአቸውንም ውኃ ደፈናቸው፥ ከእነርሱም አንድ አልቀረም።
12. በዚያን ጊዜ በቃሉ አመኑ፥ ምስጋናውንም ዘመሩ።
13. ፈጥነውም ሥራውን ረሱ፥ በምክሩም አልታገሡም።
14. በምድረ በዳም ምኞትን ተመኙ፥ በበረሃም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።
15. የለመኑትንም ሰጣቸው፤ ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ።
16. ሙሴንም እግዚአብሔር የቀደሰውንም አሮንን በሰፈር ተመቀኙአቸው።
17. ምድርም ተከፈተች ዳታንንም ዋጠችው፥ የአቤሮንንም ወገን ደፈነች፤
18. በማኅበራቸውም እሳት ነደደች፥ ነበልባልም ኅጥኣንን አቃጠላቸው።
19. በኮሬብም ጥጃን ሠሩ፥ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ።
20. ሣርም በሚበላ በበሬ ምሳሌ ክብራቸውን ለወጡ።
21. –
22. ታላቅ ነገርንም በግብጽ፥ ድንቅንም በካራን ምድር፥ ግሩም ነገርንም በኤርትራ ባሕር ያደረገውን ያዳናቸውንም እግዚአብሔርን ረሱ።
23. እንዳያጠፋቸው ቍጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ።
24. የተወደደችውን ምድር ናቁ፥ በቃሉም አልታመኑም፥
25. በድንኳኖቻቸውም ውስጥ አንጐራጐሩ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም።
26. –
27. በምድረ በዳም ይጥላቸው ዘንድ፥ ዘራቸውንም በአሕዛብ መካከል ይጥል ዘንድ፥ በየአገሩም ይበትናቸው ዘንድ፥ እጁን አነሣባቸው።
28. በብዔል ፌጎርም ተባበሩበት፥ የሙታንንም መሥዋዕት በሉ።
29. በሥራቸውም አስመረሩት፥ ቸነፈርም በላያቸው በዛ።
30. ፊንሐስም ተነሥቶ ፈረደባቸው፥ ቸነፈሩም ተወ፤
31. ያም እስከ ዘላለም ለልጅ ልጅ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት።
32. –
33. በክርክር ውኃ ዘንድም አስቈጡት፥ መንፈሱን አስመርረዋታልና፤ ስለ እነርሱም ሙሴ ተበሳጨ፤ በከንፈሮቹም በስንፍና ተናገረ።
34. እግዚአብሔርም እንዳላቸው አሕዛብን አላጠፉም፤
35. ከአሕዛብም ጋር ተደባለቁ፥ ሥራቸውንም ተማሩ።
36. ለጣዖቶቻቸውም ተገዙ፥ ወጥመድም ሆኑባቸው።
37. ወንዶች ልጆቻቸውንና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአጋንንት ሠው፤
38. የወንዶች ልጆቻቸውንና የሴቶች ልጆቻቸን ደም፥ ለከነዓን ጣዖቶች የሠውአቸውን ንጹሕ ደም አፈሰሱ፥ ምድርም በደም ረከሰች።
39. በሥራቸው ረከሱ፥ በማድረጋቸውም አመነዘሩ።
40. የእግዚአብሔርም ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፥ ርስቱንም ተጸየፈ።
41. ወደ አሕዛብም እጅ አሳለፋቸው፥ የሚጠሉአቸውም ገዙአቸው።
42. ጠላቶቻቸውም ግፍ አደረጉባቸው፥ ከእጃቸውም በታች ተዋረዱ።
43. ብዙ ጊዜ አዳናቸው፤ ነገር ግን በምክራቸው አስመረሩት፥ በኃጢአታቸውም ተዋረዱ።
44. እርሱ ግን ጩኸታቸውን በሰማ ጊዜ ጭንቃቸውን ተመለከተ፤
45. ለእነርሱም ኪዳኑን አሰበ፥ እንደ ምሕረቱም ብዛት ተጸጸተ።
46. በማረኩአቸውም ሁሉ ፊት ሞገስን ሰጣቸው።
47. አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ አድነን፤ ቅዱስ ስምህን እናመሰግን ዘንድ፥ በምስጋናህም እንመካ ዘንድ፥ ከአሕዛብ መካከል ሰብስበን።
48. ከዘላለም እስከ ዘላለም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ ሕዝብም ሁሉ አሜን ይበል። ሃሌ ሉያ።
About መዝሙረ ዳዊት Chapter 106
Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 106 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: መዝሙረ ዳዊት
Chapter: 106
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መዝሙረ ዳዊት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading መዝሙረ ዳዊት Chapter 106 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is መዝሙረ ዳዊት Chapter 106?
መዝሙረ ዳዊት Chapter 106 is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete መዝሙረ ዳዊት Chapter 106 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from መዝሙረ ዳዊት
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 112
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 55
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 59
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 1
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 148
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 147
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 134
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- ዘኍልቍ Chapter 7
- አሞጽ Chapter 1
- ዘፍጥረት Chapter 31
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 115
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 132
- ኢሳይያስ Chapter 19
- ኢዮብ Chapter 14