ምሳሌ Chapter 11

For English

Read ምሳሌ Chapter 11 Online

Read ምሳሌ Chapter 11 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ምሳሌ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ምሳሌ 11

ምዕራፍ 11

1. አባይ ሚዛን በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው፤ እውነተኛ ሚዛን ግን ደስ ያሰኘዋል።

2. ትዕቢት ከመጣች ውርደት ትመጣለች፤ በትሑታን ዘንድ ግን ጥበብ ትገኛለች።

3. ቅኖች ቅንነታቸው ትመራቸዋለች፤ ወስላቶችን ግን ጠማማነታቸው ታጠፋቸዋለች።

4. በቍጣ ቀን ሀብት አትረባም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች።

5. የፍጹም ሰው ጽድቁ መንገዱን ያቀናለታል፤ ኃጥእ ግን በኃጢአቱ ይወድቃል።

6. ቅኖችን ጽድቃቸው ይታደጋቸዋል፤ ወስላቶች ግን በምኞታቸው ይጠመዳሉ።

7. ኀጥእ በሞተ ጊዜ ተስፋው ይቈረጣል፥ የኃያል አለኝታም ይጠፋል።

8. ጻድቅ ከጭንቀት ይድናል፥ ኀጥእም በእርሱ ፋንታ ይመጣል።

9. ዝንጉ ሰው በአፉ ባልንጀራውን ያጠፋል፤ ጻድቃን ግን በእውቀት ይድናሉ።

10. በጻድቃን ልማት ከተማ ደስ ይላታል፥ በኀጥኣንም ጥፋት እልል ትላለች።

11. በቅኖች በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች፤ በኀጥኣን አፍ ግን ትገለበጣለች።

12. ወዳጁን የሚንቅ እርሱ አእምሮ የጐደለው ነው፤ አስተዋይ ግን ዝም ይላል።

13. ለሐሜት የሚሄድ ምሥጢሩን ይገልጣል፤ በመንፈስ የታመነ ግን ነገሩን ይሰውራል።

14. መልካም ምክር ከሌለ ዘንድ ሕዝብ ይወድቃል፤ በመካሮች ብዛት ግን ደኅንነት ይሆናል።

15. ለማያውቅ የሚዋስ ክፉ መከራን ይቀበላል፤ ዋስነትን የሚጠላ ግን ይድናል።

16. ሞገስ ያላት ሴት ክብርን ታገኛለች፥ ሀኬተኖችም ሀብትን ያገኛሉ።

17. ቸር ሰው ለራሱ መልካም ያደርጋል፤ ጨካኝ ግን ሥጋውን ይጐዳል።

18. የኀጥእ ሰው ሞያ ሐሰተኛ ነው፤ ጽድቅን የሚዘራ ግን የታመነ ዋጋ አለው።

19. በጽድቅ የሚጸና በሕይወት ይኖራል፤ ክፋትን የሚከተል ግን ለሞቱ ነው።

20. ልበ ጠማሞች በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው፤ በመንገዳቸው ፍጹማን የሆኑ ግን የተወደዱ ናቸው።

21. ክፉ ሰው እጅ በእጅ ሳይቀጣ አይቀርም፤ የጻድቃን ዘር ግን ይድናል።

22. የወርቅ ቀለበት በእርያ አፍንጫ እንደ ሆነ፥ ከጥበብ የተለየች ቆንጆ ሴትም እንዲሁ ናት።

23. የጻድቃን ምኞት በጎ ብቻ ነው፤ የኀጥኣን ተስፋ ግን መቅሠፍት ነው።

24. ያለውን የሚበትን ሰው አለ፥ ይጨመርለታልም፤ ያለ ቅጥ የሚነፍግ ሰውም አለ፥ ይደኸያልም።

25. የምትባረክ ነፍስ ትጠግባለች፥ የረካም እርሱ ደግሞ ይረካል።

26. እህልን የሚያስቀር ሰው በሕዝብ ዘንድ ይረገማል፤ በረከት ግን በሚሸጠው ራስ ላይ ነው።

27. መልካምን ተግቶ የሚሻ ደስታን ይፈልጋል፤ ክፉን በሚፈልግ ግን ክፉ ይመጣበታል።

28. በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል ጻድቃን ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ።

29. ቤቱን የሚያውክ ሰው ነፋስን ይወርሳል፥ ሰነፍም ለጠቢብ ተገዥ ይሆናል።

30. የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ናት፥ ነፍሶችንም የሚሰበስብ እርሱ ጠቢብ ነው።

31. እነሆ፥ ጻድቅ በምድር ላይ ፍዳውን የሚቀበል ከሆነ፥ ይልቁንስ ኀጥእና ዓመፀኛ እንዴት ይሆናሉ!

About ምሳሌ Chapter 11

Read ምሳሌ Chapter 11 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ምሳሌ
Chapter: 11
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ምሳሌ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ምሳሌ Chapter 11 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ምሳሌ Chapter 11?

ምሳሌ Chapter 11 is part of the Book of ምሳሌ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ምሳሌ Chapter 11 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ምሳሌ

  1. ምሳሌ Chapter 19
  2. ምሳሌ Chapter 17
  3. ምሳሌ Chapter 15
  4. ምሳሌ Chapter 4
  5. ምሳሌ Chapter 23
  6. ምሳሌ Chapter 3
  7. ምሳሌ Chapter 31

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ሕዝቅኤል Chapter 39
  2. ኢያሱ Chapter 6
  3. ዘጸአት Chapter 21
  4. ዘፍጥረት Chapter 46
  5. 2 ሳሙኤል Chapter 4
  6. ኤርምያስ Chapter 2
  7. ዘዳግም Chapter 27

Related Chapters & Readings

  1. ሶፎንያስ Chapter 1
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 86
  3. ዮሐንስ Chapter 13
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 147
  5. ኢሳይያስ Chapter 26
  6. ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 3
  7. ሮሜ Chapter 6
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *