ምሳሌ Chapter 7

For English

Read ምሳሌ Chapter 7 Online

Read ምሳሌ Chapter 7 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ምሳሌ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ምሳሌ 7

ምዕራፍ 7

1. ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ጠብቅ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽግ።

2. ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ፤ ሕጌንም እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቅ፤

3. በጣቶችህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት ጻፋቸው።

4. ጥበብን። አንቺ እኅቴ ነሽ በላት፥ ማስተማውልንም። ወዳጄ ብለህ ጥራት፥

5. ከጋለሞታ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ ቃልዋን ካለዘበች ከሌላይቱ ሴት።

6. በቤቴ መስኮት ሆኜ ወደ አደባባይ ተመለከትሁ፤

7. ከአላዋቂዎች መካከል አስተዋልሁ፤ ከጐበዛዝትም መካከል ብላቴናውን አእምሮ ጐድሎት አየሁ፥

8. በአደባባይ ሲሄድ በቤትዋም አቅራቢያ ሲያልፍ፤ የቤትዋን መንገድ ይዞ ወደ እርስዋ አቀና፥

9. ማታ ሲመሽ፥ ውድቅትም ሲሆን፥ በሌሊትም በጽኑ ጨለማ።

10. እነሆ፥ ሴት ተገናኘችው የጋለሞታ ልብስ የለበሰች፥ ነፍሳትን ለማጥመድ የተዘጋጀች።

11. ሁከተኛና አባያ ናት፥ እግሮችዋም በቤትዋ አይቀመጡም፤

12. አንድ ጊዜ በጎዳና፥ አንድ ጊዜ በአደባባይ፥ በማዕዘኑም ሁሉ ታደባለች።

13. ያዘችውም ሳመችውም፤ ፊትዋም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው።

14. መሥዋዕትንና የደኅንነት ቍርባንን ማቅረብ ነበረብኝ፤ ዛሬ ስእለቴን ፈጸምሁ።

15. ስለዚህ እንድገናኝህ፥ ፊትህንም በትጋት ለመሻት ወጥቻለሁ፥ አግኝቼሃለሁም።

16. በአልጋዬ ላይ ማለፊያ ሰርፍ ዘርግቼበታለሁ፥ የግብጽንም ሽመልመሌ ለሀፍ።

17. በመኝታዬ ከርቤንና ዓልሙን ቀረፋም ረጭቼበታለሁ።

18. ና፥ እስኪነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ፥ በተወደደ መተቃቀፍም ደስ ይበለን።

19. ባለቤቴ በቤቱ የለምና፥ ወደ ሩቅ መንገድ ሄዶአልና፤

20. በእጁም የብር ከረጢት ወስዶአል፤ ሙሉ ጨረቃ በሆነች ጊዜ ወደ ቤቱ ይመለሳል።

21. በብዙ ጨዋታዋ እንዲስት ታደርገዋለች፤ በከንፈርዋ ልዝብነት ትጐትተዋለች።

22. እርሱ እንዲህ ስቶ ይከተላታል፥ በሬ ለመታረድ እንዲነዳ፥ ውሻም ወደ እስራት እንዲሄድ፥

23. ወፍ ወደ ወጥመድ እንደሚቸኩል፥ ለነፍሱ ጥፋት እንደሚሆን ሳያውቅ፥ ፍላጻ ጕበቱን እስኪሰነጥቀው ድረስ።

24. ልጆቼ ሆይ፥ አሁን እንግዲህ ስሙኝ ወደ አፌም ቃል አድምጡኝ።

25. ልብህ ወደ መንገድዋ አያዘንብል በጎዳናዋ አትሳት።

26. ወግታ የጣለቻቸው ብዙ ናቸውና፤ እርስዋም የገደለቻቸው እጅግ ብዙ ናቸው።

27. ቤትዋ የሲኦል መንገድ ነው፤ ወደ ሞት ማጀት የሚወርድ ነው።

About ምሳሌ Chapter 7

Read ምሳሌ Chapter 7 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ምሳሌ
Chapter: 7
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ምሳሌ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ምሳሌ Chapter 7 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ምሳሌ Chapter 7?

ምሳሌ Chapter 7 is part of the Book of ምሳሌ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ምሳሌ Chapter 7 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ምሳሌ

  1. ምሳሌ Chapter 24
  2. ምሳሌ Chapter 4
  3. ምሳሌ Chapter 29
  4. ምሳሌ Chapter 17
  5. ምሳሌ Chapter 19
  6. ምሳሌ Chapter 30
  7. ምሳሌ Chapter 15

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ዳንኤል Chapter 9
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 27
  3. ዘጸአት Chapter 11
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 76
  5. ዘፍጥረት Chapter 28
  6. ሆሴዕ Chapter 7
  7. ኢያሱ Chapter 4

Related Chapters & Readings

  1. ዘዳግም Chapter 17
  2. ኢሳይያስ Chapter 46
  3. 2 ሳሙኤል Chapter 19
  4. ዮናስ Chapter 3
  5. ኢሳይያስ Chapter 62
  6. ሐጌ Chapter 1
  7. ኤርምያስ Chapter 3
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *