1 ዜና መዋዕል Chapter 9

For English

Read 1 ዜና መዋዕል Chapter 9 Online

Read 1 ዜና መዋዕል Chapter 9 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ዜና መዋዕል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ዜና መዋዕል and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

1 ዜና መዋዕል 9

ምዕራፍ 9

1. እስራኤልም ሁሉ በየትውልዳቸው ተቈጠሩ፤ እነሆም፥ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል። ይሁዳም ስለ ኃጢአታቸው ወደ ባቢሎን ተማረኩ።

2. ፤ በአውራጃዎቻቸውና በከተሞቻቸው መጀመሪያ የተቀመጡ እስራኤልና ካህናት ሌዋውያንም ናታኒምም ነበሩ።

3. ፤ ከይሁዳ ልጆችና ከብንያም ልጆች ከኤፍሬምና ከምናሴ ልጆች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።

4. ፤ ከይሁዳ ልጅ ከፋሬስ ልጆች የባኒ ልጅ የአምሪ ልጅ የፆምሪ ልጅ የዓሚሁድ ልጅ ዑታይ ደግሞ ተቀመጠ።

5. ፤ ከሴሎናዊያንም በኵሩ ዓሣያና ልጆቹ።

6. ፤ ከዛራም ልጆች ይዑኤልና ወንድሞቻቸው፥ ስድስት መቶ ዘጠና።

7. ፤ ከብንያምም ልጆች የሐስኑአ ልጅ የሆዳይዋ ልጅ የሜሱላም ልጅ ሰሉ፤

8. ፤ የይሮሐም ልጅ ብኔያ፤ የሚክሪ ልጅ የኦዚ ልጅ ኤላ፤ የዪብኒያ ልጅ የራጉኤል ልጅ የሰፋጥያስ ልጅ ሜሱላም፤

9. ፤ በየትውልዳቸውም ወንድሞቻቸው ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስድስት ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች ሁሉ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ።

10. ፤ ከካህናቱም ዮዳሄ፥ ዮአሪብ፥ ያኪን፤

11. ፤ የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ የመራዮት ልጅ የሳዶቅ ልጅ ሜሱላም ልጅ የኬልቂያስ ልጅ ዓዛርያስ፤

12. ፤ የመልኪያ ልጅ የጳስኮር ልጅ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፤ የኢሜር ልጅ የምሺላሚት ልጅ የሜሱላም ልጅ የየሕዜራ ልጅ የዓዲኤል ልጅ መዕሣይ፤

13. ፤ የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች ወንድሞቻቸው ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ነበሩ፤ ለእግዚአብሔር ቤት ማገልገል ሥራ እጅግ ብልሃተኞች ሰዎች ነበሩ።

14. ፤ ከሌዋውያንም የሜራሪ ልጆች የአሳብያ ልጅ የዓዝሪቃም ልጅ የአሱብ ልጅ ሸማያ፤

15. ፤ በቅበቃር፥ ኤሬስ፥ ጋላል፥ የኣሳፍ ልጅ የዝክሪ ልጅ የሚካ ልጅ መታንያ፤

16. ፤ የኤዶታም ልጅ የጋላል ልጅ የሰሙስ ልጅ አብድያ፤ በነጦፋውያንም መንደሮች የተቀመጠው የሕልቃና ልጅ የአሳ ልጅ በራክያ።

17. ፤ በረኞችም ሰሎም፥ ዓቁብ፥ ጤልሞን፥ አሒማን፥ ወንድሞቻቸውም ነበሩ፤ ሰሎምም አለቃ ነበረ።

18. ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በንጉሥ በር በምሥራቅ በኩል ነበሩ፤ ለሌዊ ልጆች ሰፈር በረኞች ነበሩ።

19. ፤ የቆሬም ልጅ የአብያሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአባቱም ቤት የነበሩ ወንድሞቹ ቆሬያውያን በማገልገል ሥራ ላይ ነበሩ፥ የድንኳኑንም መድረክ ይጠብቁ ነበር። አባቶቻቸውም የእግዚአብሔርን ሰፈር መግቢያ ጠብቀው ነበር።

20. ፤ አስቀድሞም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ አለቃቸው ነበረ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ።

21. ፤ የሜሱላም ልጅ ዘካርያስ የመገናኛው ድንኳን ደጅ በረኛ ነበረ።

22. ፤ የመድረኩ በረኞች ይሆኑ ዘንድ የተመረጡ እነዚህ ሁሉ ሁለት መቶ አሥራ ሁለት ነበሩ። ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል በሥራቸው ያቆሙአቸው እነዚህ በመንደሮቻቸው በየትውልዳቸው ተቈጠሩ።

23. ፤ እነርሱና ልጆቻቸውም በእግዚአብሔር ቤት በድንኳኑ ደጆች ላይ ዘበኞች ነበሩ።

24. ፤ በአራቱ ማዕዘኖች፥ በምሥራቅ፥ በምዕራብ፥ በሰሜን፥ በደቡብ፥ በረኞች ነበሩ።

25. ፤ ወንድሞቻቸውም በመንደሮቻቸው ሆነው፥ በየሰባትም ቀን ከእነርሱ ጋር ሊሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይገቡ ነበር።

26. ፤ ከሌዋውያንም የነበሩ አራቱ የበረኞች አለቆች ዘወትር በሥራቸው ይቀመጡ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ቤት ባሉ ጓዳዎችና ቤተ መዛግብት ላይ ነበሩ።

27. ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት የሚጠብቁ፥ ጥዋት ጥዋትም ደጆቹን የሚከፍቱ እነርሱ ነበሩና በዚያ ያድሩ ነበር።

28. ፤ ዕቃውም በቍጥር ይገባና ይወጣ ነበርና ከእነዚህ አንዳንዱ በማገልገያው ዕቃ ላይ ሹሞች ነበሩ።

29. ፤ ከእነርሱም አንዳንዶቹ በመቅደሱ ዕቃ ሁሉ በመልካሙም ዱቄት፥ በወይን ጠጁ፥ በዘይቱም፥ በዕጣኑም፥ በሽቱውም ላይ ሹሞች ነበሩ።

30. ፤ ከካህናቱም ልጆች አንዳንዶቹ የሽቱውን ቅባት ያጣፍጡ ነበር።

31. ፤ የቆሬያዊውም የሰሎም በኵር ሌዋዊው ማቲትያ በምጣድ በሚጋገረው ነገር ላይ ሹም ነበረ።

32. ፤ በየሰንበቱም ያዘጋጁ ዘንድ ከወንድሞቻቸው ከቀዓታውያን አንዳንዱ በገጹ ኅብስት ላይ ሹሞች ነበሩ።

33. ፤ ከሌዋውያኑም ወገን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች የነበሩ መዘምራን እነዚህ ናቸው፤ ሥራቸውም ሌሊትና ቀን ነበረና ያለሌላ ሥራ በየጓዳቸው ይቀመጡ ነበር።

34. ፤ እነዚህ ከሌዋውያን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች በየትውልዳቸው አለቆች ነበሩ። እነዚህም በኢየሩሳሌም ይቀመጡ ነበር።

35. ፤ የሚስቱ ስም መዓካ የነበረው የገባዖን አባት ይዒኤል፥

36. ፤ የበኵር ልጁም ዓብዶን፥

37. ፤ ዱር፥ ቂስ፥ በኣል፥ ኔር፥ ናዳብ፥ ጌዶር፥ አሒዮ፥ ዛኩር፥ ሚቅሎት፥ በገባኦን ይቀመጡ ነበር።

38. ፤ ሚቅሎትም ሳምአን ወለደ፤ እነርሱ ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ይቀመጡ ነበር።

39. ፤ ኔርም ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሚልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስበኣልን ወለደ።

40. ፤ የዮናታንም ልጅ መሪበኣል ነበረ፤ መሪበኣልም ሚካን ወለደ።

41. ፤ የሚካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓ፥ አካዝ ነበሩ።

42. ፤ አካዝም የዕራን ወለደ፤ የዕራም ዓሌሜትን፥ ዓዝሞትን፥ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞጻን ወለደ።

43. ፤ ሞጻም ቢንዓን ወለደ፥ ልጁም ረፋያ ነበረ፥ ልጁ ኤልዓሣ፥ ልጁ ኤሴል፤

44. ፤ ለኤሴልም ስድስት ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ይህ ነበረ፤ ዓዝሪቃም፥ ቦክሩ፥ እስማኤል፥ ሸዓሪያ፥ አብድዩ፥ ሐናን፤ እነዚህ የኤሴል ልጆች ነበሩ።

About 1 ዜና መዋዕል Chapter 9

Read 1 ዜና መዋዕል Chapter 9 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ዜና መዋዕል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 1 ዜና መዋዕል
Chapter: 9
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ዜና መዋዕል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 1 ዜና መዋዕል Chapter 9 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 1 ዜና መዋዕል Chapter 9?

1 ዜና መዋዕል Chapter 9 is part of the Book of 1 ዜና መዋዕል in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 1 ዜና መዋዕል Chapter 9 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 1-ዜና-መዋዕል

  1. 1 ዜና መዋዕል Chapter 2
  2. 1 ዜና መዋዕል Chapter 15
  3. 1 ዜና መዋዕል Chapter 13
  4. 1 ዜና መዋዕል Chapter 27
  5. 1 ዜና መዋዕል Chapter 25
  6. 1 ዜና መዋዕል Chapter 12
  7. 1 ዜና መዋዕል Chapter 7

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ዳንኤል Chapter 1
  2. ኢዮብ Chapter 34
  3. ኤርምያስ Chapter 18
  4. ምሳሌ Chapter 28
  5. ኢዮብ Chapter 19
  6. መዝሙረ ዳዊት Chapter 128
  7. ኢያሱ Chapter 2

Related Chapters & Readings

  1. ኢዮብ Chapter 3
  2. አሞጽ Chapter 8
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 127
  4. 1 ጴጥሮስ Chapter 1
  5. 2 ቆሮንቶስ Chapter 10
  6. መዝሙረ ዳዊት Chapter 1
  7. ዘዳግም Chapter 7
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *