Read አሞጽ Chapter 3 Online
Read አሞጽ Chapter 3 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of አሞጽ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of አሞጽ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
አሞጽ 3
ምዕራፍ 3
1. የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር በእናንተ፥ ከግብጽ ምድር ባወጣሁት ወገን ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤
2. ፤ እንዲህም ብሎአል። እኔ ከምድር ወገን ሁሉ እናንተን ብቻችሁን አውቄአችኋለሁ፤ ስለዚህ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ።
3. ፤ በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ በአንድነት ይሄዳሉን?
4. ፤ ወይስ አንበሳ የሚነጥቀው ነገር ሳያገኝ በጫካ ውስጥ ያገሣልን? ወይስ የአንበሳ ደቦል አንዳች ሳይዝ በመደቡ ሆኖ ይጮኻልን?
5. ፤ ወይስ ወፍ፥ አጥማጅ ከሌለው፥ በምድር ላይ በወጥመድ ይያዛልን? ወይስ ወስፈንጠር አንዳች ሳይዝ ከምድር ይፈነጠራልን?
6. ፤ ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? ወይስ ክፉ ነገር በከተማ ላይ የመጣ እንደ ሆነ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?
7. ፤ በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።
8. ፤ አንበሳው አገሣ፤ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ትንቢት የማይናገር ማን ነው?
9. ፤ በአዛጦን አዳራሾችና በግብጽ ምድር አዳራሾች አውሩና። በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፥ በውስጥዋም የሆነውን ታላቁን ውካታ፥ በመካከልዋም ያለውን ግፍ ተመልከቱ በሉ።
10. ፤ ግፍንና ቅሚያን በአዳራሾቻቸው የሚያከማቹት ቅን ነገርን ያደርጉ ዘንድ አያውቁም፥ ይላል እግዚአብሔር።
11. ፤ ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በምድሪቱ ዙሪያ ጠላት ይመጣል፤ ብርታትሽንም ከአንቺ ያወርዳል፥ አዳራሾችሽም ይበዘበዛሉ።
12. ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት እግርን ወይም የጆሮን ጫፍ እንደሚያድን፥ እንዲሁ በሰማርያ በአልጋ ማዕዘን፥ በደማስቆም በምንጣፍ ላይ የተቀመጡት የእስራኤል ልጆች ይድናሉ።
13. ፤ ስሙ፥ በያዕቆብም ቤት ላይ መስክሩ፥ ይላል የሠራዊት አምላክ ጌታ እግዚአብሔር።
14. ፤ እስራኤልን ስለ ኃጢአቱ በምበቀልበት ቀን የቤቴልን መሠዊያዎች ደግሞ እበቀላለሁ፤ የመሠዊያው ቀንዶች ይሰበራሉ፥ ወደ ምድርም ይወድቃሉ።
15. ፤ የክረምቱንና የበጋውን ቤት እመታለሁ፤ በዝሆንም ጥርስ የተለበጡት ቤቶች ይጠፋሉ፥ ታላላቆችም ቤቶች ይፈርሳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።
About አሞጽ Chapter 3
Read አሞጽ Chapter 3 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of አሞጽ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: አሞጽ
Chapter: 3
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading አሞጽ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading አሞጽ Chapter 3 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is አሞጽ Chapter 3?
አሞጽ Chapter 3 is part of the Book of አሞጽ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete አሞጽ Chapter 3 online for free with easy chapter navigation.