መሳፍንት Chapter 19

For English

Read መሳፍንት Chapter 19 Online

Read መሳፍንት Chapter 19 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መሳፍንት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መሳፍንት and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

መሳፍንት 19

ምዕራፍ 19

1. በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ በሌለበት ጊዜ በተራራማው በኤፍሬም አገር ማዶ የተቀመጠ ሌዋዊ ነበረ፤ ከቤተ ልሔምም ይሁዳ ቁባት አገባ።

2. ፤ ቁባቱም አመነዘረችበት፥ ትታውም ወደ አባትዋ ቤት ወደ ቤተ ልሔም ይሁዳ ሄደች፤ በዚያም አራት ወር ተቀመጠች።

3. ፤ ባልዋም ተነሣ፥ ከእርስዋም ዕርቅ ሽቶ ወደ ቤቱ ሊመልሳት ፍለጋዋን ተከትሎ ሄደ፤ ከእርሱም ጋር አንድ አሽከር ሁለትም አህዮች ነበሩ። እርስዋም ወደ አባትዋ ቤት አገባችው፤ አባትዋም ባየው ጊዜ ደስ ብሎት ተገናኘው።

4. ፤ የብላቴናይቱም አባት አማቱ የግድ አለ፥ በቤቱም ሦስት ቀን ተቀመጠ፤ በሉም፥ ጠጡም፥ በዚያም አደሩ።

5. ፤ በአራተኛውም ቀን ማልደው ተነሡ፥ እርሱም ለመሄድ ተነሣ፤ የብላቴናይቱም አባት አማቹን። ሰውነትህን በቍራሽ እንጀራ አበርታ፥ ከዚያም በኋላ ትሄዳለህ አለው።

6. ፤ ተቀመጡም በአንድ ላይም በሉ ጠጡም፤ የብላቴናይቱም አባት ሰውዮውን። ዛሬ ደግሞ ከዚህ ለማደር፥ እባክህ፥ ፍቀድ፥ ልብህንም ደስ ይበለው አለው።

7. ፤ ሰውዮውም ሊሄድ ተነሣ፤ አማቱ ግን የግድ አለው፥ ዳግመኛም በዚያ አደረ።

8. ፤ በአምስተኛውም ቀን ለመሄድ ማልዶ ተነሣ፤ የብላቴናይቱም አባት። እባክህ፥ ሰውነትህን አበርታ፥ ቀኑም እስኪዋገድ ድረስ ቆይ አለው። ሁለቱም በሉ።

9. ፤ ሰውዮውም ከቁባቱና ከአሽከሩ ጋር ለመሄድ በተነሣ ጊዜ የብላቴናይቱ አባት አማቱ። እነሆ፥ ቀኑ ተዋግዶአል፤ በዚህ እደሩ፤ እነሆ፥ ቀኑ ለማለፍ ተዋግዶአል፤ ልባችሁ ደስ እንዲለው በዚህ እደሩ፤ ነገም ወደ ቤታችሁ እንድትደርሱ ማልዳችሁ መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ አለው።

10. ፤ ሰውዮው ግን በዚያ ሌሊት ለማደር አልፈቀደም፥ ተነሥቶም ሄደ፥ ኢየሩሳሌምም ወደ ተባለች ወደ ኢያቡስ ፊት ለፊት ደረሰ። ከእርሱም ጋር ሁለት የተጫኑ አህዮች ነበሩ፥ ቁባቱም ከእርሱ ጋር ነበረች።

11. ፤ ወደ ኢያቡስም በደረሱ ጊዜ መሸባቸው፥ አሽከሩም ጌታውን። ና፥ ወደዚህ ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ፥ እባክህ፥ እናቅና፥ በእርስዋም እንደር አለው።

12. ፤ ጌታውም። ከእስራኤል ወገን ወዳልሆነች ወደ እንግዳ ከተማ አንገባም፤ እኛ ወደ ጊብዓ እንለፍ አለው።

13. ፤ አሽከሩንም። ና፥ ከእነዚህ ስፍራ ወደ አንዱ እንቅረብ፤ በጊብዓ ወይም በራማ እንደር አለው።

14. ፤ መንገዳቸውንም ይዘው ሄዱ፤ የብንያምም ነገድ በምትሆነው በጊብዓ አጠገብ ሳሉ ፀሐይ ገባችባቸው።

15. ፤ በጊብዓም ገብተው ያድሩ ዘንድ ወደዚያ አቀኑ። በገባም ጊዜ ሊያሳድራቸው ማንም በቤቱ አልተቀበላቸውምና በከተማው አደባባይ ተቀመጡ።

16. ፤ እነሆም፥ አንድ ሽማግሌ ከእርሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፤ ይህም ሰው ከተራራማው ከኤፍሬም አገር ነበረ በጊብዓም በእንግድነት ተቀምጦ ነበር፤ የዚያ አገር ሰዎች ግን ብንያማውያን ነበሩ።

17. ፤ ዓይኑንም አንሥቶ መንገደኛውን በከተማው አደባባይ አየ፤ ሽማግሌውም። ወዴት ትሄዳለህ? ከወዴትስ መጣህ? አለው።

18. ፤ እርሱም። እኛ ከቤተ ልሔም ይሁዳ ወደ ተራራማው ወደ ኤፍሬም አገር ማዶ እናልፋለን፤ እኔ ከዚያ ነኝ፥ ወደ ቤተ ልሔምም ይሁዳ ሄጄ ነበር፥ አሁንም ወደ እግዚአብሔር ቤት እሄዳለሁ፤ በቤቱም የሚያሳድረኝ አጣሁ፤

19. ፤ ለአህዮቻችን ገለባና ገፈራ አለን፤ ለእኔና ለገረድህ ከባሪያዎችህም ጋር ላለው አሽከር እንጀራና የወይን ጠጅ አለን፤ አንዳችም አላጣንም አለው።

20. ፤ ሽማግሌውም። ሰላም ከአንተ ጋር ይሁን፤ የምትሻውንም ሁሉ እኔ እሰጥሃለሁ፤ በአደባባይ ግን አትደር አለው።

21. ፤ ወደ ቤቱም አስገባው፥ ለአህዮቹም ገፈራ ጣለላቸው፤ እግራቸውንም ታጠቡ፥ በሉም ጠጡም።

22. ፤ ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ ወስላቶች የሆኑ የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ በሩንም ይደበድቡ ነበር፤ ባለቤቱንም ሽማግሌውን። ወደ ቤትህ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን አሉት።

23. ፤ ባለቤቱም ሽማግሌው ወደ እነርሱ ወጥቶ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር፥ እባካችሁ፥ አታድርጉ፤ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ገብቶአልና እንደዚህ ያለ ኃጢአት አትሥሩ።

24. ፤ ድንግል ልጄና የእርሱም ቁባት፥ እነሆ፥ አሉ፥ አሁንም አወጣቸዋለሁ፤ አዋርዱአቸው እንደ ወደዳችሁም አድርጉባቸው፤ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እንደዚህ ያለ ኃጢአት አታድርጉ አላቸው።

25. ፤ ሰዎቹ ግን ነገሩን አልሰሙም፤ ሰውዮውም ቁባቱን ይዞ አወጣላቸው፤ ደረሱባትም፥ ሌሊቱንም ሁሉ እስኪነጋ ድረስ አመነዘሩባት፤ ጎህ በቀደደም ጊዜ ለቀቁአት።

26. ፤ ሴቲቱም ማለዳ መጣች፥ ጌታዋም ባለበት በሰውዮው ቤት ደጅ ወድቃ እስኪነጋ ድረስ በዚያ ቀረች።

27. ፤ ጌታዋም ማለዳ ተነሣ የቤቱንም ደጅ ከፈተ፥ መንገዱንም ለመሄድ ወጣ፤ እነሆም ቁባቲቱ ሴት በቤቱ ደጃፍ ወድቃ፥ እጅዋም በመድረክ ላይ ነበረ።

28. ፤ እርሱም። ተነሺ፥ እንሂድ አላት፤ እርስዋ ግን ሞታ ነበርና አልመለሰችም፤ በዚያን ጊዜ በአህያው ላይ ጫናት፥ ተነሥቶም ወደ ስፍራው ሄደ።

29. ፤ ወደ ቤቱም በመጣ ጊዜ ካራ አነሣ፥ ቁባቱንም ይዞ ከአጥንቶችዋ መለያያ ላይ ለአሥራ ሁለት ቈራርጦ ወደ እስራኤል አገር ሁሉ ሰደደ።

30. ፤ ያየም ሁሉ። የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልተደረገም፥ አልታየምም፤ አስቡት፥ በዚህም ተመካከሩ፥ ተነጋገሩም ይባባል ነበር።

About መሳፍንት Chapter 19

Read መሳፍንት Chapter 19 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መሳፍንት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: መሳፍንት
Chapter: 19
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መሳፍንት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading መሳፍንት Chapter 19 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is መሳፍንት Chapter 19?

መሳፍንት Chapter 19 is part of the Book of መሳፍንት in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete መሳፍንት Chapter 19 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from መሳፍንት

  1. መሳፍንት Chapter 7
  2. መሳፍንት Chapter 18
  3. መሳፍንት Chapter 16
  4. መሳፍንት Chapter 20
  5. መሳፍንት Chapter 15
  6. መሳፍንት Chapter 13
  7. መሳፍንት Chapter 11

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ኢሳይያስ Chapter 28
  2. አስቴር Chapter 3
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 100
  4. ነህምያ Chapter 2
  5. ምሳሌ Chapter 28
  6. መሳፍንት Chapter 15
  7. ኢሳይያስ Chapter 33

Related Chapters & Readings

  1. 1 ነገሥት Chapter 5
  2. ዘጸአት Chapter 26
  3. ሆሴዕ Chapter 11
  4. ኢዮብ Chapter 11
  5. መክብብ Chapter 7
  6. ሚክያስ Chapter 3
  7. ዕዝራ Chapter 7
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *