Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 51 Online
Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 51 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መዝሙረ ዳዊት and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
መዝሙረ ዳዊት 51
ምዕራፍ 51
1. አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።
2. ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ፤
3. እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።
4. አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፥ በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ።
5. እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ።
6. እነሆ፥ እውነትን ወደድህ፤ የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ።
7. በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፤ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።
8. ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፥ የሰበርሃቸውም አጥንቶቼ ደስ ይላቸዋል።
9. ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።
10. አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።
11. ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ።
12. የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ።
13. ለሕግ ተላላፎች መንገድህን አስተምራለሁ፥ ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ።
14. የመድኃኒቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከደም አድነኝ፥ አንደበቴም በአንተ ጽድቅ ትደሰታለች።
15. አቤቱ፥ ከንፈሮቼን ክፈት፥ አፌም ምስጋናህን ያወራል።
16. መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር፤ የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሰኝህም።
17. የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም።
18. አቤቱ፥ በውዴታህ ጽዮንን አሰማምራት፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጽሮች ሥራ።
19. የጽድቁን መሥዋዕት መባውንም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በወደድህ ጊዜ፥ ያን ጊዜ በመሠዊያህ ላይ ፍሪዳዎችን ይሠዋሉ።
About መዝሙረ ዳዊት Chapter 51
Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 51 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: መዝሙረ ዳዊት
Chapter: 51
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መዝሙረ ዳዊት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading መዝሙረ ዳዊት Chapter 51 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is መዝሙረ ዳዊት Chapter 51?
መዝሙረ ዳዊት Chapter 51 is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete መዝሙረ ዳዊት Chapter 51 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from መዝሙረ ዳዊት
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 112
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 59
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 55
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 1
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 147
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 122
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 120
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 36
- ኢያሱ Chapter 5
- ኢሳይያስ Chapter 19
- ኢዩኤል Chapter 3
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 80
- ኤርምያስ Chapter 12
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 15