መዝሙረ ዳዊት Chapter 18

For English

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 18 Online

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 18 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መዝሙረ ዳዊት and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

መዝሙረ ዳዊት 18

ምዕራፍ 18

1. አቤቱ ጕልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ።

2. እግዚአብሔር ዓለቴ፥ አምባዬ፥ መድኃኒቴ፥ አምላኬ፥ በእርሱም የምተማመንበት ረዳቴ፥ መታመኛዬና የደኅንነቴ ቀንድ መጠጊያዬም ነው።

3. ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ።

4. የሞት ጣር ያዘኝ፥ የዓመፅ ፈሳሽም አስፈራኝ፤

5. የሲኦል ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድም ደረሰብኝ።

6. በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፤ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።

7. ምድርም ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም፥ የተራሮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ እግዚአብሔርም ተቈጥቶአልና ተንቀጠቀጡ።

8. ከቍጣው ጢስ ወጣ፥ ከፊቱም የሚበላ እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእርሱ በራ።

9. ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም፥ ጨለማ ከእግሩ በታች ነበረ።

10. በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ በረረ፥ በነፋስም ክንፍ በረረ።

11. መሰወሪያውን ጨለማ አደረገ፤ በዙሪያውም ድንኳኑ፤ በደመናት ውስጥ የጨለማ ውኃ ነበረ።

12. በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ ደመናትና በረዶ የእሳት ፍምም አለፉ።

13. እግዚአብሔርም ከሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ።

14. ፍላጻውን ላከ በተናቸውም፤ መብረቆችን አበዛ አወካቸውም።

15. አቤቱ፥ ከዘለፋህ ከመዓትህም መንፈስ እስትንፋስ የተነሣ፥ የውኆች ምንጮች ታዩ፥ የዓለም መሠረቶችም ተገለጡ።

16. ከላይ ሰደደ ወሰደኝም፥ ከብዙ ውኆችም አወጣኝ።

17. ከብርቱዎች ጠላቶቼ ከሚጠሉኝም አዳነኝ፥ በርትተውብኝ ነበርና።

18. በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ደገፋዬ ሆነ።

19. ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፤ ወድዶኛልና አዳነኝ።

20. እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ ይከፍለኛል፤ እንደ እጄ ንጽሕና ይመልስልኛል።

21. የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፥ በአምላኬም አላመፅሁም።

22. ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበረና፥ ሥርዓቱንም ከፊቴ አላራቅሁም።

23. በእርሱ ዘንድ ቅን ነበርሁ፥ ከኃጢአቴም ተጠበቅሁ።

24. እግዚአብሔርም እንደ ጽድቄ እንደ እጄም ንጽሕና በዓይኖቹ ፊት መለሰልኝ።

25. ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤

26. ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ።

27. አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ።

28. አንተ መብራቴን ታበራለህና፤ እግዚአብሔር አምላኬ ጨለማዬን ያበራል።

29. በአንተ ከጥፋት እድናለሁና በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁ።

30. የአምላኬ መንገድ ፍጹም ነው፥ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፥ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው።

31. ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችን በቀር አምላክ ማን ነው?

32. ኃይልን የሚያስታጥቀኝ መንገዴንም የሚያቃና፥

33. እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች የሚያረታ በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው።

34. እጆቼን ሰልፍ ያስተምራል፥ በክንዴም የናስ ቀስት እገትራለሁ።

35. ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች።

36. አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፥ እግሮቼም አልተንሸራተቱም።

37. ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ እይዛቸዋለሁም፥ እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም።

38. አስጨንቃቸዋለሁ መቆምም አይችሉም፥ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ።

39. ለሰልፍም ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፤ በበላዬ የቆሙትን ሁሉ በበታቼ ታስገዛቸዋለህ።

40. የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው።

41. ጮኹ የሚረዳቸውም አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ አልሰማቸውም።

42. እንደ ትቢያ በነፋስ ፊት እፈጫቸዋለሁ፥ እንደ አደባባይም ጭቃ እረግጣቸዋለሁ።

43. ከሕዝብ ክርክር ታድነኛለህ፥ የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፥ የማላውቀው ሕዝብም ይገዛልኛል።

44. በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ፤ የባዕድ ልጆች ደለሉኝ።

45. የባዕድ ልጆች አረጁ፥ በመንገዳቸውም ተሰናከሉ።

46. እግዚአብሔር ሕያው ነው፥ አምላኬም ቡሩክ ነው፥ የመድኃኒቴም አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።

47. በቀሌን የሚመልስልኝ አምላክ አሕዛብን በበታቼ ያስገዛልኛል።

48. ከጠላቶቼ የሚታደገኝ እርሱ ነው፤ በእኔም ላይ ከቆሙ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፥ ከግፈኛ ሰው ታድነኛለህ።

49. አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ ለስምህም እዘምራለሁ።

50. የንጉሡን መድኃኒት ታላቅ ያደርጋል፥ ቸርነቱንም ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም ይሰጣል።

About መዝሙረ ዳዊት Chapter 18

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 18 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: መዝሙረ ዳዊት
Chapter: 18
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መዝሙረ ዳዊት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading መዝሙረ ዳዊት Chapter 18 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is መዝሙረ ዳዊት Chapter 18?

መዝሙረ ዳዊት Chapter 18 is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete መዝሙረ ዳዊት Chapter 18 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from መዝሙረ ዳዊት

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 112
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 59
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 55
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 1
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 148
  6. መዝሙረ ዳዊት Chapter 134
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 122

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. 1 ነገሥት Chapter 18
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 72
  3. ዘኍልቍ Chapter 31
  4. አሞጽ Chapter 8
  5. መሳፍንት Chapter 20
  6. ኢዮብ Chapter 7
  7. 2 ሳሙኤል Chapter 6

Related Chapters & Readings

  1. ሉቃስ Chapter 13
  2. ኢሳይያስ Chapter 18
  3. ኤርምያስ Chapter 37
  4. ማቴዎስ Chapter 20
  5. ሕዝቅኤል Chapter 47
  6. ዘፍጥረት Chapter 2
  7. ኢሳይያስ Chapter 14
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *