መሳፍንት Chapter 20

For English

Read መሳፍንት Chapter 20 Online

Read መሳፍንት Chapter 20 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መሳፍንት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መሳፍንት and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

መሳፍንት 20

ምዕራፍ 20

1. የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወጡ፥ ማኅበሩም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፥ ከገለዓድም አገር ሰዎች ጋር፥ ወደ እግዚአብሔር ወደ ምጽጳ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ።

2. ፤ ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ የሆኑ የሕዝብ ሁሉ አለቆች ሰይፍ በሚመዝዙ በቍጥርም አራት መቶ ሺህ እግረኞች በሆኑ በእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ ቆሙ።

3. ፤ የብንያምም ልጆች የእስራኤል ልጆች ወደ ምጽጳ እንደ ወጡ ሰሙ። የእስራኤልም ልጆች። ይህ ክፉ ነገር እንደምን እንደ ተደረገ ንገሩን አሉ።

4. ፤ የተገደለችውም ሴት ባል ሌዋዊው እንዲህ ብሎ መለሰላቸው። እኔና ቁባቴ በዚያ ለማደር ወደ ብንያም አገር ወደ ጊብዓ መጣን።

5. ፤ የጊብዓም ሰዎች ተነሡብኝ፥ ቤቱንም በሌሊት በእኛ ላይ ከበቡት፤ ሊገድሉኝም ወደዱ፥ በቁባቴም አጥብቀው አመነዘሩባት፥ እርስዋም ሞተች።

6. ፤ እኔም ቁባቴን ይዤ ቈራረኋጥጥኋት በእስራኤልም ዘንድ እንደዚህ ያለ ኃጢአትና ስንፍና ስለ ተሠራ ወደ እስራኤል ርስት አገር ሁሉ ሰደድሁ።

7. ፤ እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ ሁላችሁ፥ ምክራችሁንና እዝናታችሁን በዚህ ስጡ።

8. ፤ ሕዝቡም ሁሉ እንደ አንድ ሰው ተነሥተው አሉ። ከእኛ ዘንድ ማንም ወደ ድንኳኑ አይሄድም፥ ወደ ቤቱም አይመለስም።

9. ፤ ነገር ግን በጊብዓ ላይ የምናደርገው ነገር ይህ ነው፤ በዕጣ እንወጣባታለን።

10. ፤ ወደ ብንያም ጊብዓ በመጡ ጊዜ እርስዋ በእስራኤል ላይ እንዳደረገችው እንደ ስንፍናዋ እንዲያደርጉ፥ ለሕዝብ ስንቅ የሚይዙ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ከመቶው አሥር ሰው ከሺሁም መቶ ሰው ከአሥሩም ሺህ አንድ ሺህ ሰው እንወስዳለን።

11. ፤ የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው በከተማይቱ ላይ ተሰበሰቡ።

12.

13. ፤ የእስራኤልም ነገዶች። በእናንተ መካከል የተደረገ ይህ ክፉ ነገር ምንድር ነው? አሁንም እንድንገድላቸው ከእስራኤልም ክፋትን እንድናርቅ በጊብዓ ውስጥ ያሉትን ምናምንቴዎቹን ሰዎች አውጥታችሁ ስጡን ብለው ወደ ብንያም ነገድ ሁሉ

14. ፤ የብንያምም ልጆች ከእስራኤል ልጆች ጋር ሊዋጉ ከየከተማው ወደ ጊብዓ ተሰበሰቡ።

15. ፤ በዚያም ቀን ከየከተማው የመጡ የብንያም ልጆች ተቈጠሩ፤ ቍጥራቸውም ከጊብዓ ሰዎች ሌላ ሀያ ስድስት ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከጊብዓም ሰባት መቶ የተመረጡ ሰዎች ተቈጠሩ።

16. ፤ ከእነዚያም ሕዝብ ሁሉ ሰባት መቶ የተመረጡ ግራኝ ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህም ሁሉ ድንጋይ ይወነጭፉ ነበር፤ አንዲት ጠጕርስ እንኳ አይስቱም።

17. ፤ ከብንያምም ልጆች ሌላ የእስራኤል ሰዎች አራት መቶ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ተቈጠሩ፤ እነዚህም ሁሉ ሰልፈኞች ነበሩ።

18. ፤ የእስራኤልም ልጆች ተነሥተው ወደ ቤቴል ወጡ፥ እግዚአብሔርንም። የብንያምን ልጆች ለመውጋት አስቀድሞ ማን ይውጣልን? ብለው ጠየቁት፤ እግዚአብሔርም። ይሁዳ ይቅደም አለ።

19. ፤ የእስራኤልም ልጆች በማለዳ ተነሥተው በጊብዓ ፊት ሰፈሩ።

20. ፤ የእስራኤልም ሰዎች ከብንያም ጋር ሊዋጉ ወጡ፤ የእስራኤልም ሰዎች በጊብዓ አጠገብ በእነርሱ ላይ ተሰልፈው ቆሙ።

21. ፤ የብንያምም ልጆች ከጊብዓ ወጡ፥ በዚያም ቀን ከእስራኤላውያን ሀያ ሁለት ሺህ ሰዎች ገደሉ።

22. ፤ ሕዝቡም፥ የእስራኤል ሰዎች፥ ተበራቱ፥ በፊተኛውም ቀን በተሰለፉበት ስፍራ ደግመው ተሰለፉ።

23. ፤ የእስራኤልም ልጆች ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለቀሱ፤ እግዚአብሔርንም። ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንቀርባለን? ብለው ጠየቁ። እግዚአብሔርም። በእነርሱ ላይ ውጡ አለ።

24. ፤ በሁለተኛውም ቀን የእስራኤል ልጆች ከብንያም ልጆች ጋር ሊዋጉ ቀረቡ።

25. ፤ በሁለተኛውም ቀን ብንያም ከጊብዓ በእነርሱ ላይ ወጣ፥ ከእስራኤልም ልጆች ደግሞ አሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች ገደሉ፤ እነዚህም ሁሉ ሰይፍ የሚመዝዙ ነበሩ።

26. ፤ የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ሕዝቡም ሁሉ ወጥተው ወደ ቤቴል መጡ፥ አለቀሱም፥ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጡ፥ በዚያም ቀን እስከ ማታ ድረስ ጾሙ፤ በእግዚአብሔር ፊት የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕት አቀረቡ።

27.

28. ፤ በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት በዚያ ነበረና፥ በዚያም ዘመን የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በፊቱ ይቆም ነበርና የእስራኤል ልጆች እግዚአብሔርን። ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንውጣን

29. ፤ እስራኤልም በጊብዓ ዙሪያ የተደበቁ ሰዎች አኖሩባት።

30. ፤ በሦስተኛውም ቀን የእስራኤል ልጆች ወደ ብንያም ልጆች ወጡ፥ በጊብዓም ፊት እንደ ቀድሞው ጊዜ ተሰለፉ።

31. ፤ የብንያምም ልጆች በሕዝቡ ላይ ወጡ፥ ከከተማይቱም ተሳቡ፤ እንደ ቀድሞውም ጊዜ፥ በአውራዎቹ መንገዶች፥ አንደኛው ወደ ቤቴል ሁለተኛውም ወደ ጊብዓ ሜዳ በሚወስዱት መንገዶች ላይ፥ ሕዝቡን ይመቱ ይገድሉም ጀመር፤

32. ፤ የብንያምም ልጆች። እንደ ቀድሞው በፊታችን ተመቱ አሉ። የእስራኤል ልጆች ግን። እንሽሽ፥ ከከተማም ወደ መንገድ እንሳባቸው አሉ።

33. ፤ የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ከስፍራቸው ተነሥተው በበኣልታማር ተሰለፉ። ከእስራኤልም ተደብቀው የነበሩት ከስፍራቸው ከጊብዓ ሜዳ ወጡ።

34. ፤ ከእስራኤልም ሁሉ የተመረጡ አሥር ሺህ ሰዎች ወደ ጊብዓ አንጻር መጡ፤ ሰልፍም በርትቶ ነበር፤ መከራም እንዲያገኛቸው አላወቁም ነበር።

35. ፤ እግዚአብሔርም ብንያምን በእስራኤል ፊት መታ፤ በዚያም ቀን የእስራኤል ልጆች ከብንያም ሀያ አምስት ሺህ አንድ መቶ ሰዎች ገደሉ፤ እነዚህ ሁሉ ሰይፍ የሚመዝዙ ነበሩ።

36. ፤ የብንያም ልጆች እንደ ተመቱ አዩ፤ የእስራኤል ልጆች ግን በጊብዓ ላይ ባኖሩት ድብቅ ጦር ታምነዋልና ለብንያም ስፍራ ለቀቁላቸው።

37. ፤ ተደብቀውም የነበሩት ፈጥነው ወደ ጊብዓ ሮጡ፤ ተደብቀውም የነበሩት መጥተው ከተማውን ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱ።

38. ፤ የተደበቁትም ሰዎች ከከተማው ብዙ ጢስ እንደ ደመና እንዲያስነሡ በእስራኤል ልጆችና በተደበቁት ሰዎች መካከል ምልክት ተደርጎ ነበር።

39. ፤ የእስራኤልም ሰዎች ከሰልፉ አፈገፈጉ፤ ብንያማውያንም። እንደ ቀድሞው ሰልፍ በፊታችን ተመትተዋል እያሉ ከእስራኤል ሰዎች ሠላሳ የሚያህሉ ሰዎች መምታትና መግደል ጀመሩ።

40. ፤ ምልክቱ በጢሱ ዓምድ ከከተማው ሊወጣ በጀመረ ጊዜ ብንያማውያን ወደ ኋላቸው ተመለከቱ፥ እነሆም፥ የሞላ ከተማው ጥፋት ወደ ሰማይ ወጣ።

41. ፤ የእስራኤልም ሰዎች ተመለሱ፥ የብንያምም ሰዎች ክፉ ነገር እንደ ደረሰባቸው አይተዋልና ደነገጡ።

42. ፤ ከእስራኤልም ሰዎች ፊት ጀርባቸውን መልሰው ወደ ምድረ በዳ መንገድ ሸሹ፤ ሰልፉም ተከታትሎ ደረሰባቸው፤ ከየከተማውም የወጡት በመካከላቸው ገደሉአቸው።

43. ፤ ብንያማውያንንም ከበቡ፥ በምሥራቅም በኩል እስካለው እስከ ጊብዓ አንጻር ድረስ አሳደዱአቸው፥ በመኑሔም አጠፉአቸው።

44. ፤ ከብንያምም አሥራ ስምንት ሺህ ሰው ሞተ፤ እነዚህ ሁሉ ጽኑዓን ነበሩ።

45. ፤ ከእነርሱም የተረፉት ተመልሰው ወደ ምድረ በዳ ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፥ ከእነርሱም በየመንገዱ ላይ አምስት ሺህ ሰው ለቀሙ፤ ወደ ጊድአምም አሳደዱአቸው፥ ከእነርሱም ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደሉ።

46. ፤ እንዲሁም በዚያ ቀን ከብንያም የሞቱት ሀያ አምስት ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህ ሁሉ ጽኑዓን ነበሩ።

47. ፤ ስድስቱም መቶ ሰዎች ተመልሰው ወደ ምድረ በዳ ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፥ በሬሞን ዓለት አራት ወር ተቀመጡ።

48. ፤ የእስራኤልም ሰዎች በብንያም ልጆች ላይ ዳግመኛ ተመለሱ፤ ሞላውን ከተማ ከብቱንም ያገኙትንም ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱ፤ ያገኙትንም ከተማ ሁሉ በእሳት አቃጠሉ።

About መሳፍንት Chapter 20

Read መሳፍንት Chapter 20 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መሳፍንት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: መሳፍንት
Chapter: 20
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መሳፍንት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading መሳፍንት Chapter 20 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is መሳፍንት Chapter 20?

መሳፍንት Chapter 20 is part of the Book of መሳፍንት in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete መሳፍንት Chapter 20 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from መሳፍንት

  1. መሳፍንት Chapter 7
  2. መሳፍንት Chapter 18
  3. መሳፍንት Chapter 19
  4. መሳፍንት Chapter 16
  5. መሳፍንት Chapter 6
  6. መሳፍንት Chapter 15
  7. መሳፍንት Chapter 13

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ሕዝቅኤል Chapter 40
  2. ዘኍልቍ Chapter 34
  3. ኢሳይያስ Chapter 13
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 14
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 107
  6. 1 ነገሥት Chapter 9
  7. ዘፍጥረት Chapter 26

Related Chapters & Readings

  1. ዘኍልቍ Chapter 24
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 85
  3. ዘፍጥረት Chapter 42
  4. ኤርምያስ Chapter 33
  5. ማርቆስ Chapter 14
  6. ዘፍጥረት Chapter 47
  7. 1 ነገሥት Chapter 5
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *