መዝሙረ ዳዊት Chapter 135

For English

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 135 Online

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 135 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መዝሙረ ዳዊት and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

መዝሙረ ዳዊት 135

ምዕራፍ 135

1. ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ፤ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት፥

2. በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ፥ በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ።

3. እግዚአብሔር ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ለስሙ ዘምሩ፥ መልካም ነውና፤

4. እግዚአብሔር ያዕቆብን ለራሱ፥ እስራኤልንም ለመዝገቡ መርጦታልና፤

5. እግዚአብሔር ታላቅ እንደ ሆነ፥ ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንዲበልጥ አውቄአለሁና።

6. በሰማይና በምድር በባሕርና በጥልቆች ሁሉ፥ እግዚአብሔር የወደደውን ሁሉ አደረገ።

7. ከምድር ዳር ደመናትን ያወጣል፤ በዝናብ ጊዜ መብረቅን አደረገ፤ ነፋሳትንም ከመዛግብቱ ያወጣል።

8. የግብጽን በኵር ልጆች ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ መታ።

9. ግብጽ ሆይ፥ በመካከልሽ በፈርዖንና በባሪያዎቹ ሁሉ ላይ ተኣምራትንና ድንቅን ሰደደ።

10. ብዙ አሕዛብን መታ፥ ብርቱዎችንም ነገሥታት ገደለ።

11. የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ የባሳንንም ንጉሥ ዐግን፥ የከነዓንን መንግሥታት ሁሉ ገደለ፤

12. ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ለእስራኤል ለሕዝቡ ርስት ሰጠ።

13. አቤቱ፥ ስምህ ለዘላለም ነው፥ ዝክርህም ለልጅ ልጅ ነው፤

14. እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳልና፥ ባሪያዎቹንም ይረዳልና።

15. የአሕዛብ ጣዖታት የብርና የወርቅ፥ የሰው እጅ ሥራ ናቸው።

16. አፍ አላቸው፥ አይናገሩምም፤ ዓይን አላቸው፥ አያዩምም፤

17. ጆሮ አላቸው፥ አይሰሙምም፤ እስትንፋስም በአፋቸው የለም።

18. የሚሠሩአቸው ሁሉ የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁን።

19. የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኩት። የአሮን ቤት ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኩት፤

20. የሌዊ ቤት ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኩት እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኩት።

21. በኢየሩሳሌም የሚያድር እግዚአብሔር ከጽዮን የተባረከ ነው። ሃሌ ሉያ።

About መዝሙረ ዳዊት Chapter 135

Read መዝሙረ ዳዊት Chapter 135 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: መዝሙረ ዳዊት
Chapter: 135
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መዝሙረ ዳዊት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading መዝሙረ ዳዊት Chapter 135 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is መዝሙረ ዳዊት Chapter 135?

መዝሙረ ዳዊት Chapter 135 is part of the Book of መዝሙረ ዳዊት in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete መዝሙረ ዳዊት Chapter 135 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from መዝሙረ ዳዊት

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 59
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 55
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 48
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 134
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 112
  6. መዝሙረ ዳዊት Chapter 58
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 37

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. 2 ዜና መዋዕል Chapter 2
  2. ኤርምያስ Chapter 17
  3. ዘሌዋውያን Chapter 3
  4. ምሳሌ Chapter 23
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 89
  6. ዘኍልቍ Chapter 34
  7. ዘፍጥረት Chapter 32

Related Chapters & Readings

  1. 1 ቆሮንቶስ Chapter 10
  2. የሐዋርያት ሥራ Chapter 14
  3. ዕብራውያን Chapter 2
  4. 2 ቆሮንቶስ Chapter 10
  5. ዘጸአት Chapter 12
  6. ኢዮብ Chapter 16
  7. ገላትያ Chapter 2
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *