ሩት Chapter 4

For English

Read ሩት Chapter 4 Online

Read ሩት Chapter 4 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሩት in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ሩት and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

A+ A A-

ሩት 4

ምዕራፍ 4

1. ቦዔዝም ወደ ከተማይቱ በር አደባባይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ። እነሆም፥ ቦዔዝ ስለ እርሱ ይናገር የነበረው የቅርብ ዘመድ ሲያልፍ ቦዔዝ። አንተ ቀርበህ በዚህ ተቀመጥ አለው። እርሱም ቀረብ ብሎ ተቀመጠ። – አንተ ቀርበህ በዚህ ተቀመጥ አለው።

2. ፤ ቦዔዝም ከከተማይቱ ሽማግሌዎች አሥር ሰዎች ጠርቶ። በዚህ ተቀመጡ አላቸው።

3. ፤ እነርሱም ተቀመጡ። ቦዔዝም የቅርብ ዘመዱን። ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ኑኃሚን የወንድማችንን የአቤሜሌክን ጢንጦ ትሸጣለች።

4. ፤ እኔም በዚህ በተቀመጡት በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊት እንድትገዛው አስታውቅህ ዘንድ አሰብሁ። መቤዠት ብትወድድ ተቤዠው፤ መቤዠት ባትወድድ ግን ከአንተ በቀር ሌላ ወራሽ የለምና፥ እኔም ከእአንተ በኋላ ነኝና እንዳውቀው ንገረኝ አለው። እርሱም። እቤዠዋለሁ አለው።

5. ፤ ቦዔዝም። እርሻውን ከኑኃሚን እጅ በምትገዛበት ቀን፥ ለሞተው በርስቱ ስሙን እንድታስነሣለት ከምዋቹ ሚስት ከሞዓባዊቱ ከሩት ደግሞ ትገዛለህ አለ።

6. ፤ የቅርብ ዘመዱም። የራሴን ርስት እንዳላበላሽ መቤዠት አልችልም፤ እኔ መቤዠቱን አልችልምና አንተ ከእኔ መቤዠቱን ውሰደው አለ።

7. ፤ በጥንት ጊዜም፥ ማንም ቢሸጥ ቢለውጥም፥ ነገሩን ለማጽናት ሰው ጫማውን እንዲያወልቅ ለባልንጀራውም እንዲሰጠው በእስራኤል ዘንድ ልማድ ነበረ። ይህም በእስራኤል ምስክር ነበረ።

8. ፤ የቅርብ ዘመዱም ቦዔዝን። አንተ ግዛው አለው፤ ጫማውንም አወለቀ።

9. ፤ ቦዔዝም ሽማግሌዎችንና ሕዝቡን ሁሉ። ለአቤሜሌክና ለኬሌዎን ለመሐሎንም የነበረውን ሁሉ ከኑኃሚን እጅ እንደ ገዛሁ እናንተ ዛሬ ምስክሮች ናችሁ።

10. ፤ ደግሞም የምዋቹ ስም ከወንድሞቹ መካከል ከአገሩም ደጅ እንዳይጠፋ፥ የምዋቹን ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ የመሐሎንን ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ወሰድሁአት፤ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ አላቸው።

11. ፤ በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ሽማግሌዎቹም። እኛ ምስክሮች ነን፤ እግዚአብሔር ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፤ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተ ልሔም ይጠራ።

12. ፤ ቤትህም እግዚአብሔር ከዚህች ቈንጆ ከሚሰጥህ ዘር ትዕማር ለይሁዳ እንደ ወለደችው እንደ ፋሬስ ቤት ይሁን አሉት።

13. ፤ ቦዔዝም ሩትን ወሰደ፥ ሚስትም ሆነችው፤ ደረሰባትም፥ እግዚአብሔርም ፅንስ ሰጣት፥ ወንድ ልጅም ወለደች።

14. ፤ ሴቶችም ኑኃሚንን። ዛሬ ዋርሳ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር ይባረክ፤ ስሙም በእስራኤል ይጠራ።

15. ፤ ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ ከምትሻል ከምትወድድሽ ምራት ተወልዶአልና ሰውነትሽን ያሳድሰዋል፥ በእርጅናሽም ይመግብሻል አሉአት።

16. ፤ ኑኃሚንም ሕፃኑን ወሰደች አቀፈችውም፥ ሞግዚትም ሆነችው።

17. ፤ ሴቶችም ጎረቤቶችዋ፥ ለኑኃሚን ወንድ ልጅ ተወለደላት እያሉ ስም አወጡለት፤ ስሙንም ኢዮቤድ ብለው ጠሩት። እርሱም የዳዊት አባት የእሴይ አባት ነው።

18. ፤ የፋሬስም ትውልድ ይህ ነው፤ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፥

19. ፤ ኤስሮምም አራምን ወለደ፥ አራምም አሚናዳብን ወለደ፥

20. ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፥ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፥

21. ፤ ሰልሞንም ቦዔዝን ወለደ፥

22. ፤ ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፥ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፥ እሴይም ዳዊትን ወለደ።

About ሩት Chapter 4

Read ሩት Chapter 4 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሩት in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ሩት
Chapter: 4
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ሩት. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ሩት Chapter 4 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ሩት Chapter 4?

ሩት Chapter 4 is part of the Book of ሩት in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ሩት Chapter 4 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ሩት

  1. ሩት Chapter 1
  2. ሩት Chapter 3
  3. ሩት Chapter 2

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. መሳፍንት Chapter 5
  2. ኢሳይያስ Chapter 12
  3. ዘሌዋውያን Chapter 4
  4. ሶፎንያስ Chapter 2
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 117
  6. 2 ሳሙኤል Chapter 1
  7. 2 ዜና መዋዕል Chapter 33

Related Chapters & Readings

  1. 2 ነገሥት Chapter 3
  2. አስቴር Chapter 5
  3. 2 ሳሙኤል Chapter 2
  4. 1 ተሰሎንቄ Chapter 3
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 87
  6. የሐዋርያት ሥራ Chapter 25
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 128
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *