መክብብ Chapter 9

For English

Read መክብብ Chapter 9 Online

Read መክብብ Chapter 9 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መክብብ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መክብብ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

መክብብ 9

ምዕራፍ 9

1. ጻድቃንና ጠቢባን ሥራዎቻቸውም በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ እመረምር ዘንድ በልቤ አኖርሁ፤ ፍቅር ወይም ጥል ቢሆን ሰው አያውቅም ሁሉ ወደ ፊታቸው ነው።

2. ፤ የጻድቁና የበደለኛው፥ የመልካሙና የክፉው፥ የንጹሑና የርኩሱ፥ መሥዋዕትን የሚሠዋውና የማይሠዋው፥ የሰው ሁሉ ድርሻው አንድ ነው፤ እንደ መልካሙ ሰው እንዲሁ ኃጢአተኛው፥ እንደ መሐለኛው ሰው እንዲሁ መሐላን የሚፈራው ነው።

3. ፤ አንድ ድርሻ ሁሉን እንዲያገኝ ከፀሐይ በታች በተደረገው ሁሉ ይህ ነገር ክፉ ነው፤ ደግሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋትን ትሞላለች፥ በሕይወታቸውም ሳሉ እብደት በልባቸው ነው፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ።

4. ፤ ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላልና ሰው ከሕያዋን ሁሉ ጋር በአንድነት ቢኖር ተስፋ አለው።

5. ፤ ሕያዋን እንዲሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን አንዳች አያውቁም፤ መታሰቢያቸውም ተረስቶአልና ከዚያ በኋላ ዋጋ የላቸውም።

6. ፤ ፍቅራቸውና ጥላቸው ቅንዓታቸውም በአንድነት ጠፍቶአል፥ ከፀሐይ በታችም በሚሠራው ነገር ለዘላለም እድል ፈንታ ከእንግዲህ ወዲህ የላቸውም።

7. ፤ እግዚአብሔር ሥራህን ተቀብሎታልና ሂድ፥ እንጀራህን በደስታ ብላ፥ የወይን ጠጅህንም በተድላ ጠጣ።

8. ፤ ሁልጊዜ ልብስህ ነጭ ይሁን፤ ቅባትም ከራስህ ላይ አይታጣ።

9. ፤ በሕይወትህ፥ አንተም ከፀሐይ በታች በምትደክምበት ድካም ይህ እድል ፈንታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀሐይ በታች በሰጠህ፥ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ፥ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።

10. ፤ አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ።

11. ፤ እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።

12. ፤ ሰውም ጊዜውን አያውቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።

13. ፤ ከፀሐይ በታችም ይህን ጥበብ አየሁ፥ እርስዋም በእኔ ዘንድ ታላቅ መሰለችኝ።

14. ፤ ታናሽ ከተማ ነበረች፥ ጥቂቶች ሰዎችም ነበሩባት፤ ታላቅ ንጉሥም መጣባት ከበባትም፥ ታላቅ ግንብም ሠራባት።

15. ፤ ጠቢብ ድሀ ሰውም ተገኘባት፥ ያችንም ከተማ በጥበቡ አዳናት፤ ያን ድሀ ሰው ግን ማንም አላሰበውም።

16. ፤ እኔም። ከኃይል ይልቅ ጥበብ ትበልጣለች፤ የድሀው ጥበብ ግን ተናቀች ቃሉም አልተሰማችም አልሁ።

17. ፤ በሰነፎች መካከል ከሚጮኽ ከገዢው ጩኸት ይልቅ የጠቢባን ቃል በጸጥታ ትሰማለች።

18. ፤ ከጦር መሣሪያዎች ይልቅ ጥበብ ትሻላለች፤ አንድ ኃጢአተኛ ግን ብዙ መልካምን ያጠፋል።

About መክብብ Chapter 9

Read መክብብ Chapter 9 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መክብብ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: መክብብ
Chapter: 9
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መክብብ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading መክብብ Chapter 9 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is መክብብ Chapter 9?

መክብብ Chapter 9 is part of the Book of መክብብ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete መክብብ Chapter 9 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from መክብብ

  1. መክብብ Chapter 6
  2. መክብብ Chapter 5
  3. መክብብ Chapter 12
  4. መክብብ Chapter 11
  5. መክብብ Chapter 8
  6. መክብብ Chapter 3
  7. መክብብ Chapter 7

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ኢዮብ Chapter 13
  2. መክብብ Chapter 1
  3. መክብብ Chapter 4
  4. ዘሌዋውያን Chapter 21
  5. ሚክያስ Chapter 1
  6. ኤርምያስ Chapter 2
  7. 2 ዜና መዋዕል Chapter 13

Related Chapters & Readings

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 131
  2. ዘኍልቍ Chapter 10
  3. 1 ሳሙኤል Chapter 13
  4. ማቴዎስ Chapter 16
  5. 2 ነገሥት Chapter 9
  6. ዘኍልቍ Chapter 24
  7. ቆላስይስ Chapter 1
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *