መኃልየ መኃልይ Chapter 5

For English

Read መኃልየ መኃልይ Chapter 5 Online

Read መኃልየ መኃልይ Chapter 5 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መኃልየ መኃልይ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መኃልየ መኃልይ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

መኃልየ መኃልይ 5

ምዕራፍ 5

1. እኅቴ ሙሽራዬ ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከርቤዬን ከሽቱዬ ጋር ለቀምሁ፥ እንጀራዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወይን ጠጄን ከወተቴ ጋር ጠጣሁ። ባልንጀሮቼ ሆይ፥ ብሉ፤ ወዳጄ ሆይ፥ ጠጪ፤ እስክትረኪ ድረስ ጠጪ።

2. ፤ እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፤ የውዴ ቃል ነው፥ እርሱም ደጁን ይመታል፤ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደምደሚያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቈንዳላዬም የሌሊት ነጠብጣብ ሞልቶበታልና ክፈችልኝ።

3. ፤ ቀሚሴን አወለቅሁ፤ እንዴት እለብሰዋለሁ? እግሬን ታጠብሁ፤ እንዴት አሳድፈዋለሁ?

4. ፤ ውዴ እጁን በቀዳዳ ሰደደ፥ አንጀቴም ስለ እርሱ ታወከ።

5. ፤ ለውዴ እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ፤ እጆቼ በደጅ መወርወሪያ ላይ ከርቤን አፈሰሱ፥ ጣቶቼ ፈሳሹን ከርቤ አንጠበጠቡ።

6. ፤ ለውዴ ከፈትሁለት፥ ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ አልፎ ነበር። ነፍሴ ከቃሉ የተነሣ ደነገጠች፤ ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፤ ጠራሁት፥ አልመለሰልኝም።

7. ፤ ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፤ መቱኝ፥ አቈሰሉኝም፤ ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት።

8. ፤ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ አምላችኋለሁ፤ ውዴን ያገኛችሁት እንደ ሆነ፥ እኔ ከፍቅር የተነሣ መታመሜን ንገሩት።

9. ፤ አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ውድሽ ማን ነው? ይህን የሚያህል አምለሽናልና ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ውድሽ ማን ነው?

10. ፤ ውዴ ነጭና ቀይ ነው፥ ከእልፍ የተመረጠ ነው።

11. ፤ ራሱ ምዝምዝ ወርቅ ነው፤ ቈንዳላው የተዝረፈረፈ ነው፥ እንደ ቁራ ጥቁረትም ጥቁር ነው።

12. ፤ ዓይኖቹ በሙሉ ፈሳሽ አጠገብ እንዳሉ በወተት እንደ ታጠቡ በፈሳሽ ውኃ አጠገብ እንደ ተቀመጡ እንደ ርግቦች ናቸው።

13. ፤ ጕንጩና ጕንጩ የሽቱ መደብ እርከን እንዳለበት እንደ ሽቱ አትክልት ናቸው፤ ከንፈሮቹ እንደ አበቦች ናቸው፥ የሚፈስስ ከርቤንም ያንጠበጥባሉ።

14. ፤ እጆቹ የቢረሌ ፈርጥ እንዳለበት እንደ ወርቅ ቀለበት ናቸው፤ አካሉ ብልሃተኛ እንደ ሠራው በሰንፔር እንዳጌጠ እንደ ዝሆን ጥርስ ነው።

15. ፤ እግሮቹ በምዝምዝ ወርቅ እንደ ተመሠረቱ እንደ ዕብነ በረድ ምሰሶች ናቸው፤ መልኩ እንደ ሊባኖስና እንደ ዝግባ ዛፍ መልካም ነው።

16. ፤ አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፥ እርሱም ፈጽሞ ያማረ ነው፤ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ውዴ ይህ ነው፥ ባልንጀራዬም ይህ ነው።

About መኃልየ መኃልይ Chapter 5

Read መኃልየ መኃልይ Chapter 5 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መኃልየ መኃልይ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: መኃልየ መኃልይ
Chapter: 5
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መኃልየ መኃልይ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading መኃልየ መኃልይ Chapter 5 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is መኃልየ መኃልይ Chapter 5?

መኃልየ መኃልይ Chapter 5 is part of the Book of መኃልየ መኃልይ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete መኃልየ መኃልይ Chapter 5 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from መኃልየ-መኃልይ

  1. መኃልየ መኃልይ Chapter 1
  2. መኃልየ መኃልይ Chapter 8
  3. መኃልየ መኃልይ Chapter 3
  4. መኃልየ መኃልይ Chapter 6
  5. መኃልየ መኃልይ Chapter 4
  6. መኃልየ መኃልይ Chapter 7
  7. መኃልየ መኃልይ Chapter 2

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. 1 ሳሙኤል Chapter 19
  2. አሞጽ Chapter 3
  3. ኢዮብ Chapter 23
  4. መክብብ Chapter 4
  5. መክብብ Chapter 11
  6. ኢያሱ Chapter 5
  7. ኢሳይያስ Chapter 28

Related Chapters & Readings

  1. ዘዳግም Chapter 10
  2. መክብብ Chapter 1
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 25
  4. ዘካርያስ Chapter 1
  5. ዘጸአት Chapter 20
  6. ምሳሌ Chapter 11
  7. ሮሜ Chapter 15
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *