Read መኃልየ መኃልይ Chapter 2 Online
Read መኃልየ መኃልይ Chapter 2 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መኃልየ መኃልይ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of መኃልየ መኃልይ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
መኃልየ መኃልይ 2
ምዕራፍ 2
1. እኔ የሳሮን ጽጌ ረዳ የቈላም አበባ ነኝ።
2. ፤ በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ፥ እንዲሁ ወዳጄ በቈነጃጅት መካከል ናት።
3. ፤ በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በልጆች መካከል ነው። ከጥላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀመጥሁ፥ ፍሬውም በጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው።
4. ፤ ወደ ወይን ጠጁም ቤት አገባኝ፥ በእኔ ላይ ያለው ዓላማውም ፍቅር ነው።
5. ፤ በዘቢብም አጽናኑኝ፥ በእንኮይ አበረታቱኝ፥ በፍቅሩ ተነድፌ ታምሜያለሁና።
6. ፤ ግራው ከራሴ በታች ናት፥ ቀኙም ታቅፈኛለች።
7. ፤ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እርሱ እስኪፈልግ ድረስ፥ ፍቅርን እንዳታስነሱትና እንዳታነሣሡት በሚዳቋ በምድረ በዳም ዋላ አምላችኋለሁ።
8. ፤ እነሆ፥ የውዴ ቃል! በተራሮች ላይ ሲዘልል፥ በኮረብቶችም ላይ ሲወረወር ይመጣል።
9. ፤ ውዴ ሚዳቋን ወይም የዋላን እምቦሳ ይመስላል፤ እነሆ፥ በመስኮቶች ሲጐበኝ፥ በዓይነ ርግብም ሲመለከት፥ እርሱ ከቅጥራችን በኋላ ቆሞአል።
10. ፤ ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ። ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፤ ውበቴ ሆይ፥ ነዪ።
11. ፤ እነሆ፥ ክረምት አለፈ፥ ዝናቡም አልፎ ሄደ።
12. ፤ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ።
13. ፤ በለሱ ጐመራ፥ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውንም ሰጡ፤ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፤ ውበቴ ሆይ፥ ነዪ።
14. ፤ በዓለት ንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ያለሽ ርግብ ሆይ፥ ቃልሽ መልካም ፊትሽም ያማረ ነውና መልክሽን አሳዪኝ፥ ድምፅሽንም አሰሚኝ።
15. ፤ ወይናችን አብቦአልና የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮች፥ ጥቃቅኑን ቀበሮች አጥምዳችሁ ያዙልን።
16. ፤ ውዴ የእኔ ነው፥ እኔም የእርሱ ነኝ፤ በሱፍ አበባዎች መካከልም መንጋውን ያሰማራል።
17. ፤ ውዴ ሆይ፥ ቀኑ እስኪነፍስ፥ ጥላውም እስኪሸሽ ድረስ ተመለስ፤ በቅመም ተራራ ላይ ሚዳቋውን ወይም የዋላውን እምቦሳ ምሰል።
About መኃልየ መኃልይ Chapter 2
Read መኃልየ መኃልይ Chapter 2 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of መኃልየ መኃልይ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: መኃልየ መኃልይ
Chapter: 2
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading መኃልየ መኃልይ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading መኃልየ መኃልይ Chapter 2 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is መኃልየ መኃልይ Chapter 2?
መኃልየ መኃልይ Chapter 2 is part of the Book of መኃልየ መኃልይ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete መኃልየ መኃልይ Chapter 2 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from መኃልየ-መኃልይ
- መኃልየ መኃልይ Chapter 1
- መኃልየ መኃልይ Chapter 8
- መኃልየ መኃልይ Chapter 3
- መኃልየ መኃልይ Chapter 6
- መኃልየ መኃልይ Chapter 4
- መኃልየ መኃልይ Chapter 7
- መኃልየ መኃልይ Chapter 5
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- ኤርምያስ Chapter 23
- ኢሳይያስ Chapter 65
- 1 ዜና መዋዕል Chapter 16
- ዘጸአት Chapter 4
- ዮናስ Chapter 4
- ኢሳይያስ Chapter 23
- መሳፍንት Chapter 13