ኢዮብ Chapter 14

For English

Read ኢዮብ Chapter 14 Online

Read ኢዮብ Chapter 14 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኢዮብ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

A+ A A-

ኢዮብ 14

ምዕራፍ 14

1. ከሴት የተወለደ ሰው የሕይወቱ ዘመን ጥቂት ቀን ነው፥ መከራም ይሞላዋል።

2. ፤ እንደ አበባ ይወጣል፥ ይረግፋልም፤ እንደ ጥላም ይሸሻል፥ እርሱም አይጸናም።

3. ፤ እንደዚህስ ባለ ሰው ላይ ዓይኖችህን ትከፍታለህን? ከአንተስ ጋር እኔን ወደ ፍርድ ታገባለህን?

4. ፤ ከርኩስ ነገር ንጹሕን ሊያወጣ ማን ይችላል? አንድ እንኳ የሚችል የለም።

5. ፤ የሰው ዕድሜ የተወሰነ ነው፥ የወሩም ቍጥር በአንተ ዘንድ ነው፥ እርሱም ሊተላለፈው የማይችለውን ዳርቻ አደረግህለት።

6. ፤ እንደ ምንደኛ ዕድሜው እስኪፈጸም ድረስ ያርፍ ዘንድ ከእርሱ ጥቂት ዘወር በል።

7. ፤ ዛፍ ቢቈረጥ ደግሞ ያቈጠቍጥ ዘንድ፥ ቅርንጫፉም እንዳያልቅ ተስፋ አለው።

8. ፤ ሥሩም በምድር ውስጥ ቢያረጅ፥ ግንዱም በመሬት ውስጥ ቢሞት፥

9. ፤ ከውኃ ሽታ የተነሣ ያቈጠቍጣል፤ እንደ አትክልት ቅርንጫፍ ያወጣል።

10. ፤ ሰው ግን ይሞትና ይጋደማል፤ ሰውም ነፍሱን ይሰጣል፥ እርሱስ ወዴት አለ?

11. ፤ ውኃ ከባሕር ውስጥ ያልቃል፤ ወንዙም ያንሳል ይደርቅማል።

12. ፤ ሰውም ተኝቶ አይነሣም፤ ሰማይ እስኪያልፍ ድረስ አይነቃም፥ ከእንቅልፉም አይነሣም።

13. ፤ በሲኦል ውስጥ ምነው በሰወርኸኝ ኖሮ! ቍጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! ቀጠሮም አድርገህ ምነው ባሰብኸኝ ኖሮ!

14. ፤ በውኑ ሰው ከሞተ ተመልሶ ሕያው ይሆናልን? መለወጤ እስኪመጣ ድረስ፥ የሰልፌን ዘመን ሁሉ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር።

15. ፤ በጠራኸኝና በመለስሁልህ ነበር፤ የእጅህንም ሥራ በተመኘኸው ነበር።

16. ፤ አሁን ግን እርምጃዬን ቈጥረኸዋል፤ ኃጢአቴንም ትጠባበቃለህ።

17. ፤ መተላልፌ በከረጢት ውስጥ ታትሞአል፥ ኃጢአቴንም ለብጠህበታል።

18. ፤ ተራራ ሲወድቅ ይጠፋል፥ ዓለቱም ከስፍራው ይፈልሳል፤

19. ፤ ውኆች ድንጋዮቹን ይፍቃሉ፤ ፈሳሾቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፤ እንዲሁ የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ።

20. ፤ ለዘላለም ታሸንፈዋለህ፥ እርሱም ያልፋል፤ ፊቱን ትለውጣለህ፥ እርሱንም ትሰድደዋለህ።

21. ፤ ልጆቹ ቢከብሩ አያውቅም፤ ቢዋረዱም አያይም።

22. ፤ ነገር ግን የገዛ ሥጋው ሕመም ብቻ ይሰማዋል፥ ለራሱም ብቻ ያለቅሳል። ች

About ኢዮብ Chapter 14

Read ኢዮብ Chapter 14 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ኢዮብ
Chapter: 14
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኢዮብ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ኢዮብ Chapter 14 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ኢዮብ Chapter 14?

ኢዮብ Chapter 14 is part of the Book of ኢዮብ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ኢዮብ Chapter 14 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 1
  3. አሞጽ Chapter 3
  4. አሞጽ Chapter 6
  5. አሞጽ Chapter 2
  6. አሞጽ Chapter 7
  7. አሞጽ Chapter 5

Explore More from ኢዮብ

  1. ኢዮብ Chapter 35
  2. ኢዮብ Chapter 20
  3. ኢዮብ Chapter 11
  4. ኢዮብ Chapter 2
  5. ኢዮብ Chapter 30
  6. ኢዮብ Chapter 42
  7. ኢዮብ Chapter 3

Related Chapters & Readings

  1. ዘፍጥረት Chapter 10
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 118
  3. ማቴዎስ Chapter 14
  4. ኢሳይያስ Chapter 60
  5. ምሳሌ Chapter 5
  6. ኢያሱ Chapter 18
  7. ኢዮብ Chapter 17
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *