Read ኢዮብ Chapter 20 Online
Read ኢዮብ Chapter 20 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኢዮብ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
ኢዮብ 20
ምዕራፍ 20
1. ናዕማታዊውም ሶፋር መለሰ እንዲህም አለ።
2. ፤ ስለዚህ በውስጤ ስላለው ችኰላ አሳቤ ትመልስልኛለች።
3. ፤ የሚያሳፍረኝንም ተግሣጽ ሰምቻለሁ፥ የማስተዋሌም መንፈስ ይመልስልኛል።
4. ፤ ሰው በምድር ላይ ከተቀመጠ፥ ከዱሮ ዘመን ጀምሮ፥
5. ፤ የኃጢአተኛ ፉከራ አጭር መሆኑን የዝንጉዎችም ደስታ ቅጽበት መሆኑን አታውቁምን?
6. ፤ ከፍታው ወደ ሰማይ ቢወጣ፥ ራሱም እስከ ደመና ቢደርስ፥
7. ፤ እንደ ፋንድያ ለዘላለም ይጠፋል፤ ያዩትም። ወዴት ነው? ይላሉ።
8. ፤ እንደ ሕልም ይበርራል፥ እርሱም አይገኝም፤ እንደ ሌሊትም ራእይ ይሰደዳል።
9. ፤ ያየችውም ዓይን ዳግመኛ አታየውም፤ ስፍራውም ከእንግዲህ ወዲህ አይመለከተውም።
10. ፤ ልጆቹ ድሆቹን ያቈላምጣሉ፤ እጁ ሀብቱን ይመልሳል።
11. ፤ አጥንቶቹ ብላቴንነቱን ሞልተዋል፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ ይተኛል።
12. ፤ ክፋት በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፥ ከምላሱም በታች ቢሰውረው፥
13. ፤ ቢጠብቀውም ባይተወውም፥ በጕሮሮውም ቢይዘው፥
14. ፤ መብሉ በአንጀቱ ውስጥ ይገላበጣል፤ እንደ እፉኝትም ሐሞት በውስጡ ይሆናል።
15. ፤ የዋጠውን ሀብት ይተፋዋል፤ እግዚአብሔርም ከሆዱ ውስጥ ያወጣዋል።
16. ፤ የእፉኝትን መርዝ ይጠባል፤ የእባብም ምላስ ይገድለዋል።
17. ፤ የማሩንና የቅቤውን ፈሳሽ ወንዞቹንም አይመለከትም።
18. ፤ የድካሙን ፍሬ ሳይውጠው ይመልሰዋል፤ እንደ ንግዱም ትርፍ አይደሰትም።
19. ፤ ድሀውን አስጨንቆአል፥ ትቶታልም፤ ያልሠራውንም ቤት በዝብዞአል።
20. ፤ ሆዱ ዕረፍትን አላወቀምና የወደደው ነገር አላዳነውም።
21. ፤ እርሱ ከበላ በኋላ ምንም አልተረፈም፤ ስለዚህ በረከቱ አይከናወንለትም።
22. ፤ በጠገበ ጊዜ ይጨነቃል፤ የችግረኞችም ሁሉ እጅ ታገኘዋለች።
23. ፤ ሆዱን ሳያጠግብ እግዚአብሔር የቍጣውን ትኵሳት ይሰድድበታል፥ ሲበላም ያዘንብበታል።
24. ፤ ከብረት መሣርያም ይሸሻል፥ የናስም ቀስት ይወጋዋል።
25. ፤ እርሱም ይመዝዘዋል፥ ከሥጋውም ይወጣል፤ ከሐሞቱም ብልጭ ብሎ ይሠርጻል፤ ፍርሃትም ይወድቅበታል።
26. ፤ ጨለማ ሁሉ ስለ ከበረው ዕቃ ተዘጋጅቶአል፤ በሰው አፍ እፍ የማትባል እሳት ትበላዋለች፤ በድንኳኑ ውስጥ የቀረው ይጨነቅባታል።
27. ፤ ሰማይ ኃጢአቱን ይገልጥበታል፥ ምድርም ትነሣበታለች።
28. ፤ የቤቱም ባለጠግነት ይሄዳል፤ በቍጣው ቀን እንደ ፈሳሽ ውኃ ያልፋል።
29. ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ ሰው እድል ፈንታ፥ ከእግዚአብሔርም የተመደበ ርስቱ ይህ ነው።
About ኢዮብ Chapter 20
Read ኢዮብ Chapter 20 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: ኢዮብ
Chapter: 20
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኢዮብ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading ኢዮብ Chapter 20 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is ኢዮብ Chapter 20?
ኢዮብ Chapter 20 is part of the Book of ኢዮብ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete ኢዮብ Chapter 20 online for free with easy chapter navigation.