Read ኢዮብ Chapter 3 Online
Read ኢዮብ Chapter 3 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኢዮብ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
ኢዮብ 3
ምዕራፍ 3
1. ከዚያም በኋላ ኢዮብ አፉን ከፍቶ የተወለደበትን ቀን ረገመ።
2. ፤ ኢዮብም መለሰ እንዲህ አለ።
3. ፤ ያ የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፥ ያም። ወንድ ልጅ ተፀነሰ የተባለበት ሌሊት።
4. ፤ ያ ቀን ጨለማ ይሁን፤ እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው፥ ብርሃንም አይብራበት።
5. ፤ ጨለማና የሞት ጥላ የራሳቸው ገንዘብ ያድርጉት፤ ዳመናም ይረፍበት፤ የቀን ጨለማ ሁሉ ያስፈራው።
6. ፤ ያን ሌሊት ጨለማ ይያዘው፤ በዓመቱ ቀኖች መካከል ደስ አይበለው፤ በወሮች ውስጥ ገብቶ አይቈጠር።
7. ፤ እነሆ፥ ያ ሌሊት መካን ይሁን፤ እልልታ አይግባበት።
8. ፤ ሌዋታንን ለማንቀሳቀስ የተዘጋጁ ቀኑን የሚረግሙ ይርገሙት።
9. ፤ አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ፤ ብርሃንን ቢጠባበቅ አያግኘው፥ የንጋትንም ቅንድብ አይይ፤
10. ፤ የእናቴን ማኅፀን ደጅ አልዘጋምና፥ መከራንም ከዓይኔ አልሰወረምና።
11. ፤ በማኅፀን ሳለሁ ስለ ምን አልሞትሁም? ከሆድስ በወጣሁ ጊዜ ፈጥኜ ስለ ምን አልጠፋሁም?
12. ፤ ጕልበቶች ስለ ምን ተቀበሉኝ? ጡትስ ስለ ምን ጠባሁ?
13. ፤ አሁን ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፤ አንቀላፍቼ ባረፍሁ ነበር፤
14. ፤ የፈረሰውን ለራሳቸው ከሚሠሩት ከምድር ነገሥታትና መካሮች ጋር፥
15. ፤ ወይም ቤታቸውን ብር ከሞሉ ወርቅም ካላቸው መኳንንት ጋር፥
16. ፤ ወይም እንደ ተቀበረ ጭንጋፍ፥ ብርሃንም እንዳላዩ ሕፃናት በሆንሁ ነበር።
17. ፤ ክፉዎች በዚያ መናደዳቸውን ይተዋሉ፤ በዚያም ደካሞች ያርፋሉ።
18. ፤ በዚያ ግዞተኞች በአንድነት ተዘልለው ተቀምጠዋል፤ የአስጨናቂውን ድምፅ አይሰሙም።
19. ፤ ታናሽና ታላቅ በዚያ አሉ፤ ባሪያም ከጌታው ነጻ ወጥቶአል።
20. ፤ በመከራ ላሉት ብርሃን፥ ነፍሳቸው መራራ ለሆነችባቸው፥
21. ፤ የተሰወረ ሀብትን ከሚቈፍሩ ይልቅ ሞትን ለሚጠብቁ ለማያገኙትም፥
22. ፤ መቃብርን ባገኙ ጊዜ በእልልታ ደስ ለሚላቸው፥ ሐሤትንም ለሚያደርጉ ሕይወት ስለ ምን ተሰጠ?
23. ፤ መንገዱ ለተሰወረበት ሰው፥ እግዚአብሔርም በአጥር ላጠረው ብርሃን ስለ ምን ተሰጠ?
24. ፤ ከእንጀራዬ በፊት ልቅሶዬ መጥቶአልና፥ ጩኸቴም እንደ ውኃ ፈስሶአል።
25. ፤ የፈራሁት ነገር መጥቶብኛልና፥ የደነገጥሁበትም ደርሶብኛል።
26. ፤ ተዘልዬ አልተቀመጥሁም፥ አልተማመንሁም፥ አላረፍሁም፤ ነገር ግን መከራ መጣብኝ።
About ኢዮብ Chapter 3
Read ኢዮብ Chapter 3 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: ኢዮብ
Chapter: 3
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኢዮብ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading ኢዮብ Chapter 3 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is ኢዮብ Chapter 3?
ኢዮብ Chapter 3 is part of the Book of ኢዮብ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete ኢዮብ Chapter 3 online for free with easy chapter navigation.