ኢዮብ Chapter 24

For English

Read ኢዮብ Chapter 24 Online

Read ኢዮብ Chapter 24 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኢዮብ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ኢዮብ 24

ምዕራፍ 24

1. ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ ዘመናት አልተሰወረምና እርሱን የሚያውቁ ለምን ወራቱን አያዩም?

2. ፤ የድንበሩን ምልክት የሚያፈርሱ አሉ፤ መንጋዎቹን በዝብዘው ያሰማራሉ።

3. ፤ የድሀ አድጎቹን አህያ ይነዳሉ፤ የመበለቲቱን በሬ ስለ መያዣ ይወስዳሉ።

4. ፤ ድሆቹን ከመንገዱ ያወጣሉ፤ የምድርም ችግረኞች ሁሉ ይሸሸጋሉ።

5. ፤ እነሆ፥ በምድረ በዳ እንዳሉ እንደ ሜዳ አህዮች፥ መብልን ፈልገው ወደ ሥራቸው ይወጣሉ፤ ምድረ በዳውም ለልጆቻቸው መብልን ይሰጣቸዋል።

6. ፤ እነዚያ በእርሻ ውስጥ እህላቸውን ያጭዳሉ፤ የበደለኛውንም ወይን ይቃርማሉ።

7. ፤ ራቁታቸውን ያለ ልብስ ያድራሉ፥ በብርድ ጊዜ መጐናጸፊያ የላቸውም።

8. ፤ ከተራሮች በሚወርድ ዝናብ ይረጥባሉ፤ መጠጊያም አጥተው ቋጥኙን ያቅፋሉ።

9. ፤ ድሀ አደጉን ልጅ ከጡቱ የሚነጥሉ አሉ ከችግረኛውም መያዣ ይወስዳሉ።

10. ፤ ያለ ልብስ ራቁታቸውን ይሄዳሉ፤ ተርበውም ነዶዎችን ይሸከማሉ፤

11. ፤ በእነዚህ ሰዎች አጥር ውስጥ ዘይት ያደርጋሉ፤ ወይንም ይጠምቃሉ፥ ነገር ግን ይጠማሉ።

12. ፤ ከከተማውና ከገዛ ቤቶቻቸው ይባረራሉ፤ የልጆችም ነፍስ ለእርዳታ ትጮኻለች፤ እግዚአብሔር ግን ስንፍናቸውን አይመለከትም።

13. ፤ እነዚህ በብርሃን ላይ የሚያምፁ ናቸው፤ መንገዱን አያውቁም፥ በጎዳናውም አይጸኑም።

14. ፤ ነፍሰ ገዳዩም ሳይነጋ ማልዶ ይነሣል፤ ችግረኞችንና ድሆችን ይገድላል፤ በሌሊትም እንደ ሌባ ነው።

15. ፤ የአመንዝራም ዓይን ድግዝግዝታን ይጠብቃል። የማንም ዓይን አያየኝም ይላል፥ ፊቱንም ይሸፍናል።

16. ፤ ቤቶቹን በጨለማ ይነድላሉ፤ በቀን ይሸሸጋሉ፤ ብርሃንም አያውቁም።

17. ፤ የጥዋት ብርሃን ለእነርሱ ሁሉ እንደ ሞት ጥላ ነው፤ የሞትን ጥላ ድንጋጤ ያውቃሉና።

18. ፤ እነርሱ በውኃ ፊት ላይ በርረው ያልፋሉ፤ እድል ፈንታቸውም በምድር ላይ የተረገመች ናት፤ ወደ ወይኑ ቦታ መንገድ አይዞሩም።

19. ፤ ድርቅና ሙቀት የአመዳዩን ውኃ ያጠፋሉ፤ እንዲሁ ሲኦል በደለኞችን ታጠፋለች።

20. ፤ ማኅፀን ትረሳዋለች፤ ትልም በደስታ ይጠባዋል፤ ዳግመኛም አይታሰብም፤ ክፋትም እንደ ዛፍ ይሰበራል።

21. ፤ የማትወልደውን መካኒቱን ይበድላታል፤ ለመበለቲቱም በጎነት አያደርግም።

22. ፤ ነገር ግን በኃይሉ ኃያላንን ይስባል፤ እርሱም በተነሣ ጊዜ ሰው በሕይወቱ አይታመንም።

23. ፤ እግዚአብሔር በደኅና አኑሮአቸዋል፥ በዚያም ይታመናሉ፤ ዓይኖቹ ግን በመንገዳቸው ላይ ናቸው።

24. ፤ ጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፤ ይሄዳሉ፥ ይጠወልጋሉም፤ እንደ ሌሎች ሁሉ ይከማቻሉ፤ እንደ እሸትም ራስ ይቈረጣሉ።

25. ፤ እንዲህስ ባይሆን ሐሰተኛ የሚያደርገኝ፥ ነገሬንስ እንደ ምናምን የሚያደርገው ማን ነው?

About ኢዮብ Chapter 24

Read ኢዮብ Chapter 24 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ኢዮብ
Chapter: 24
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኢዮብ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ኢዮብ Chapter 24 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ኢዮብ Chapter 24?

ኢዮብ Chapter 24 is part of the Book of ኢዮብ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ኢዮብ Chapter 24 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 1
  3. አሞጽ Chapter 3
  4. አሞጽ Chapter 2
  5. አሞጽ Chapter 7
  6. አሞጽ Chapter 6
  7. አሞጽ Chapter 5

Explore More from ኢዮብ

  1. ኢዮብ Chapter 7
  2. ኢዮብ Chapter 37
  3. ኢዮብ Chapter 6
  4. ኢዮብ Chapter 17
  5. ኢዮብ Chapter 42
  6. ኢዮብ Chapter 21
  7. ኢዮብ Chapter 2

Related Chapters & Readings

  1. ኢያሱ Chapter 2
  2. ዘሌዋውያን Chapter 11
  3. 1 ዜና መዋዕል Chapter 27
  4. ኤርምያስ Chapter 31
  5. ማቴዎስ Chapter 13
  6. ዘፍጥረት Chapter 17
  7. 1 ዜና መዋዕል Chapter 16
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *