ኢያሱ Chapter 18

For English

Read ኢያሱ Chapter 18 Online

Read ኢያሱ Chapter 18 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢያሱ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኢያሱ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ኢያሱ 18

ምዕራፍ 18

1. የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ፥ በዚያም የመገናኛውን ድንኳን ተከሉ፤ ምድሩም ጸጥ ብሎ ተገዛላቸው።

2. ፤ ከእስራኤልም ልጆች ርስት ያልተካፈሉ ሰባት ነገድ ቀርተው ነበር።

3. ፤ ኢያሱም የእስራኤልን ልጆች አላቸው። የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ እስከ መቼ ለመግባት ቸል ትላላችሁ?

4. ፤ ከየነገዱ ሁሉ ሦስት ሦስት ሰዎች ምረጡ፥ እኔም እልካቸዋለሁ፤ ተነሥተውም አገሩን ይዞራሉ፥ እንደ ርስታቸውም መጠን ይጽፉታል፤ ወደ እኔም ይመለሳሉ።

5. ፤ በሰባትም ክፍል ይከፍሉታል፤ ይሁዳ በደቡብ በኩል በዳርቻው ውስጥ ይቀመጣል፤ የዮሴፍ ወገኖች በሰሜን በኩል በዳርቻው ውስጥ ይቀመጣሉ።

6. ፤ እናንተም ምድሩን በሰባት ክፍል ጻፉት፥ የጻፋችሁትንም ወዲህ አምጡልኝ፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ፊት በዚህ ዕጣ አጣጥላችኋለሁ።

7. ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ክህነት ርስታቸው ነውና ለሌዋውያን በመካከላችሁ እድል ፈንታ የላቸውም፤ ጋድም ሮቤልም የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀብለዋል።

8. ፤ ሰዎችም ተነሥተው ሄዱ፤ ኢያሱም ምድሩን ሊጽፉ የሄዱትን። ሂዱ፥ ምድሩንም ዞራችሁ ጻፉት፥ ወደ እኔም ተመለሱ፤ በዚህም በሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ ብሎ አዘዛቸው።

9. ፤ ሰዎቹም ሄደው ምድሩን ዞሩ፥ እንደ ከተሞችም በሰባት ክፍል ከፈሉት፥ በመጽሐፍም ጻፉት፤ ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ሴሎ ተመለሱ።

10. ፤ ኢያሱም በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ ዕጣ አጣጣላቸው፤ በዚያም ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች እንደ ክፍሎቻቸው ምድሩን ከፈለ።

11. ፤ የብንያምም ልጆች ነገድ ዕጣ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ የዕጣቸውም ዳርቻ በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ወጣ።

12. ፤ በሰሜን በኩል ድንበራቸው ከዮርዳኖስ ጀመረ፤ ድንበሩም ወደ ኢያሪኮ ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፥ ከዚያም በተራራማው አገር ወደ ምዕራብ ወጣ፥ መውጫውም በቤትአዌን ምድረ በዳ ነበረ።

13. ፤ ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ አለፈ፤ ድንበሩም በታችኛው ቤትሖሮን በደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ አጣሮትአዳር ወረደ።

14. ፤ ድንበሩም ወደ ምዕራብ ሄደ፥ በቤትሖሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ ደቡብ ዞረ፤ መውጫውም ቂርያትይዓሪም በምትባል በይሁዳ ልጆች ከተማ በቂርያትበኣል ነበረ፤ ይህ የምዕራቡ ዳርቻ ነበረ።

15. ፤ የደቡብም ዳርቻ ከቂርያትይዓሪም መጨረሻ ነበረ፤ ድንበሩም በምዕራብ በኩል ወደ ነፍቶ ውኃ ምንጭ ወጣ።

16. ፤ ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፥ እርሱም በራፋይም ሸሰቆ በሰሜን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ዳር በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ዓይንሮጌልም ወረደ።

17. ፤ ወደ ሰሜንም አለፈ በቤትሳሚስ ምንጭ ላይ ወጣ፥ በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ጌሊሎት ደረሰ፤ ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወረደ፤

18. ፤ በሰሜንም ወገን ወደ ዓረባ አጠገብ አለፈ፥ ወደ ዓረባም ወረደ፤

19. ፤ ድንበሩም ወደ ቤትሖግላ ወደ ሰሜን ወገን አለፈ፤ መውጫውም በዮርዳኖስ መጨረሻ በደቡብ በኩል ባለው በጨው ባሕር ልሳን አጠገብ ነበረ፤ ይህ የደቡቡ ዳርቻ ነበረ።

20. ፤ በምሥራቅም በኩል ድንበሩ ዮርዳኖስ ነበረ። ይህ በዙርያቸው ዳርቻ በየወገኖቻቸው የብንያም ልጆች ርስት ነበረ።

21. ፤ የብንያምም ልጆች ነገድ ከተሞች በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ ኢያሪኮ፥ ቤትሖግላ፥ ዓመቀጺጽ፥

22. ፤ ቤትዓረባ፥ ዘማራይም፥ ቤቴል፥

23.

24. ፤ ዓዊም፥ ፋራ፥ ኤፍራታ፥ ክፊርዓሞናይ፥ ዖፍኒ፥ ጋባ፤ አሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።

25. ፤ ገባዖን፥ ራማ፥ ብኤሮት፥

26. ፤ ምጽጳ፥ ከፊራ፥ አሞቂ፥

27.

28. ፤ ሬቄም፥ ይርጵኤል፥ ተርአላ፥ ጼላ፥ ኤሌፍ፥ ኢየሩሳሌም የምትባል የኢያቡስ ከተማ፥ ቂርያትጊብዓት፤ አሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።

About ኢያሱ Chapter 18

Read ኢያሱ Chapter 18 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢያሱ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ኢያሱ
Chapter: 18
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኢያሱ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ኢያሱ Chapter 18 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ኢያሱ Chapter 18?

ኢያሱ Chapter 18 is part of the Book of ኢያሱ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ኢያሱ Chapter 18 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 1
  3. አሞጽ Chapter 3
  4. አሞጽ Chapter 2
  5. አሞጽ Chapter 7
  6. አሞጽ Chapter 5
  7. አሞጽ Chapter 6

Explore More from ኢያሱ

  1. ኢያሱ Chapter 19
  2. ኢያሱ Chapter 17
  3. ኢያሱ Chapter 1
  4. ኢያሱ Chapter 5
  5. ኢያሱ Chapter 7
  6. ኢያሱ Chapter 14
  7. ኢያሱ Chapter 4

Related Chapters & Readings

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 87
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 50
  3. ማቴዎስ Chapter 7
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 79
  5. ዘዳግም Chapter 10
  6. ኢያሱ Chapter 2
  7. 2 ነገሥት Chapter 3
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *