ኢዮብ Chapter 30

For English

Read ኢዮብ Chapter 30 Online

Read ኢዮብ Chapter 30 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኢዮብ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ኢዮብ 30

ምዕራፍ 30

1. አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ፥ አባቶቻቸውን ከመንጋዬ ውሾች ጋር ለማኖር የናቅኋቸው፥ በእኔ ላይ ተሳለቁብኝ።

2. ፤ ሙሉ ሰው መሆናቸው ጠፍቶባቸው ነበርና የእጃቸው ብርታት ለእኔ ምን ይጠቅማል?

3. ፤ በራብና በቀጠና የመነመኑ ናቸው፤ የመፍረስና የመፈታት ጨለማ ወዳለበት ወደ ምድረ በዳ ይሸሻሉ።

4. ፤ በቍጥቋጦ አጠገብ ያለውን ጨው ጨው የሚለውን አትክልት ይለቅማሉ፤ የክትክታ ሥር ደግሞ መብላቸው ነው።

5. ፤ ከሰዎች ተለይተው ተሰደዱ፤ በሌባ ላይ እንደሚጮኽ ይጮኹባቸዋል።

6. ፤ በሸለቆ ፈረፈርና በምድር ጕድጓድ በድንጋይም ዋሻ ውስጥ ይኖራሉ።

7. ፤ በቍጥቋጦ መካከል ይጮኻሉ፤ ከሳማ በታች ተሰብስበዋል።

8. ፤ የሰነፎችና የነውረኞች ልጆች ናቸው፤ ከምድርም በግርፋት የተባረሩ ናቸው።

9. ፤ አሁንም እኔ መዝፈኛና መተረቻ ሆንኋቸው።

10. ፤ ተጸየፉኝ፥ ከእኔም ራቁ፤ አክታቸውንም በፊቴ መትፋትን አልተዉም።

11. ፤ የቀስቴን አውታር አላልቶብኛል፥ አዋርዶኝማል፤ እነርሱም በፊቴ ልጓማቸውን ፈትተዋል።

12. ፤ በቀኜ በኩል ዱርዬዎች ተነሥተዋል፥ እግሬንም ይገለብጣሉ፤ የጥፋታቸውን መንገድ በእኔ ላይ ይጐድባሉ።

13. ፤ ጐዳናዬን ያበላሻሉ፤ ረዳት የሌላቸው ሰዎች መከራዬን ያበዛሉ።

14. ፤ በሰፊ ፍራሽ እንደሚመጡ ይመጡብኛል፤ በባድማ ውስጥ ይንከባለሉብኛል።

15. ፤ ድንጋጤ በላዬ ተመለሰችብኝ፥ ክብሬንም እንደ ነፋስ ያሳድዱአታል፤ ደኅንነቴም እንደ ደመና አልፋለች።

16. ፤ አሁንም ነፍሴ በውስጤ ፈሰሰች፤ የመከራም ዘመን ያዘችኝ።

17. ፤ በሌሊት አጥንቴ በደዌ ተነደለች፥ ጅማቶቼም አያርፉም።

18. ፤ ከታላቁ ደዌ ኃይል የተነሣ ልብሴ ተበላሸች፤ እንደ ቀሚስ ክሳድ አነቀችኝ።

19. ፤ እርሱ በጭቃ ውስጥ ጣለኝ፥ አፈርና አመድም መሰልሁ።

20. ፤ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ አልመለስህልኝም፤ ተነሣሁ፥ አልተመለከትኸኝም።

21. ፤ ተመልሰህ ጨካኝ ሆንህብኝ፤ በእጅህም ብረታት አስጨነቅኸኝ።

22. ፤ በነፋስ አነሣኸኝ፥ በላዩም አስቀመጥኸኝ፤ በዐውሎ ነፋስ አቀለጥኸኝ።

23. ፤ ለሞት ሕያዋንም ሁሉ ለሚሰበሰቡበት ቤት አሳልፈህ እንደምትሰጠኝ አውቄአለሁና።

24. ፤ ነገር ግን ሰው በወደቀ ጊዜ እጁን አይዘረጋምን? በጥፋቱስ ጊዜ አይጮኽምን?

25. ፤ ጭንቅ ቀን ላገኘው ሰው አላለቀስሁምን? ለችግረኛስ ነፍሴ አላዘነችምን?

26. ፤ ነገር ግን በጎነትን በተጠባበቅሁ ጊዜ ክፉ ነገር መጣችብኝ፤ ብርሃንን በትዕግሥት ጠበቅሁ፥ ጨለማም መጣ።

27. ፤ አንጀቴ ፈላች፥ አላረፈችም፤ የመከራም ዘመን መጣችብኝ።

28. ፤ ያለ ፀሐይ በትካዜ ሄድሁ፤ በጉባኤም መካከል ቆሜ ጮኽሁ።

29. ፤ ለቀበሮ ወንድም፥ ለሰጐንም ባልንጀራ ሆንሁ።

30. ፤ ቁርበቴ ጠቈረ፥ ከእኔም ተለይቶ እርግፍግፍ አለ፤ አጥንቴም ከትኵሳት የተነሣ ተቃጠለች።

31. ፤ ስለዚህ መሰንቆዬ ለኀዘን፥ እምቢልታዬም ለሚያለቅሱ ቃል ሆነ።

About ኢዮብ Chapter 30

Read ኢዮብ Chapter 30 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ኢዮብ
Chapter: 30
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኢዮብ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ኢዮብ Chapter 30 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ኢዮብ Chapter 30?

ኢዮብ Chapter 30 is part of the Book of ኢዮብ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ኢዮብ Chapter 30 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 2
  3. አሞጽ Chapter 7
  4. አሞጽ Chapter 6
  5. አሞጽ Chapter 3
  6. አሞጽ Chapter 1
  7. አሞጽ Chapter 9

Explore More from ኢዮብ

  1. ኢዮብ Chapter 23
  2. ኢዮብ Chapter 15
  3. ኢዮብ Chapter 24
  4. ኢዮብ Chapter 41
  5. ኢዮብ Chapter 25
  6. ኢዮብ Chapter 19
  7. ኢዮብ Chapter 1

Related Chapters & Readings

  1. ኢሳይያስ Chapter 55
  2. 1 ሳሙኤል Chapter 25
  3. ኢሳይያስ Chapter 60
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 54
  5. ዘጸአት Chapter 2
  6. ኤርምያስ Chapter 40
  7. ኢዮብ Chapter 28
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *