Read ኢዮብ Chapter 18 Online
Read ኢዮብ Chapter 18 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኢዮብ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
ኢዮብ 18
ምዕራፍ 18
1. ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ።
2. ፤ እስከ መቼ ቃልን ታጠምዳለህ? አስተውል፥ ከዚያም በኋላ እንናገራለን።
3. ፤ ስለ ምንስ እንደ እንስሶች ተቈጠርን? ስለ ምንስ በዓይንህ ፊት ረከስን?
4. ፤ ቍጣ ወርሶሃል፤ አንተስ የሞትህ እንደ ሆነ፥ ምድር ስለ አንተ ባድማ ትሆናለችን? ወይስ ዓለት ከስፍራው ይነቀላልን?
5. ፤ የኃጢአተኛ መብራት ይጠፋል፥ የእሳቱም ነበልባል ብልጭ አይልም።
6. ፤ ብርሃን በድንኳኑ ውስጥ ይጨልማል፥ መብራቱም በላዩ ይጠፋል።
7. ፤ የኃይሉም እርምጃ ትጠብባለች፥ ምክሩም ትጥለዋለች።
8. ፤ እግሩ በወጥመድ ትያዛለች፥ በመረብም ላይ ይሄዳል።
9. ፤ አሽክላ ሰኰናውን ይይዛል፥ ወስፈንጠርም ይበረታበታል።
10. ፤ በምድር ላይ የሸምቀቆ ገመድ፥ በመንገዱም ላይ ወጥመድ ለእርሱ ተሰውራለች።
11. ፤ ድንጋጤ በዙሪያው ታስፈራዋለች፥ በስተ ኋላውም ሆና ታባርራቸዋለች።
12. ፤ ኃይሉ በራብ ትደክማለች፥ መቅሠፍትም እስኪሰናከል ተዘጋጅቶለታል።
13. ፤ የሰውነቱ ብልቶች ይጠፋሉ፤ የሞትም በኵር ልጅ ብልቶቹን ይበላል።
14. ፤ ከሚታመንበት ድንኳን ይነቀላል፤ ወደ ድንጋጤም ንጉሥ ያስቸኵሉታል።
15. ፤ በድንኳኑ ውስጥ ለእርሱ የማይሆነው ይኖራል፤ በመኖሪያውም ላይ ዲን ይበተናል።
16. ፤ ሥሩ ከበታቹ ይደርቃል፥ ጫፉም ከበላይ ይረግፋል።
17. ፤ መታሰቢያው ከምድር ላይ ይጠፋል፥ በሜዳም ስም አይቀርለትም።
18. ፤ ከብርሃን ወደ ጨለማ ያፈልሱታል፥ ከዓለምም ያሳድዱታል።
19. ፤ ዘርም ትውልድም በሕዝቡ መካከል አይሆንለትም፤ በመኖሪያውም ውስጥ የሚቀመጥ ሰው አይቀርለትም።
20. ፤ የፊተኞች ሰዎች እንደ ደነገጡ፥ እንዲሁ የኋለኞች ሰዎች ስለ ዘመኑ ይደነቃሉ።
21. ፤ በእውነት የኃጢአተኞች ቤት እንዲሁ ናት፥ እግዚአብሔርንም የማያውቅ ሰው ስፍራ ይህ ነው።
About ኢዮብ Chapter 18
Read ኢዮብ Chapter 18 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: ኢዮብ
Chapter: 18
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኢዮብ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading ኢዮብ Chapter 18 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is ኢዮብ Chapter 18?
ኢዮብ Chapter 18 is part of the Book of ኢዮብ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete ኢዮብ Chapter 18 online for free with easy chapter navigation.