ኢዮብ Chapter 13

For English

Read ኢዮብ Chapter 13 Online

Read ኢዮብ Chapter 13 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኢዮብ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ኢዮብ 13

ምዕራፍ 13

1. እነሆ፥ ይህን ሁሉ ዓይኔ አየች፤ ጆሮዬም ሰምታ አስተዋለችው።

2. ፤ እናንተ የምታውቁትን እኔ ደግሞ አውቃለሁ፤ ከእናንተ የማንስ አይደለሁም።

3. ፤ ነገር ግን ሁሉን ለሚችል አምላክ መናገር እፈልጋለሁ፥ ከእግዚአብሔርም ጋር ለመዋቀስ እሻለሁ።

4. ፤ እናንተ ግን በሐሰት ለባጮች ናችሁ፤ ሁላችሁ የማትጠቅሙ ባለ መድኃኒቶች ናችሁ።

5. ፤ ምነው ዝም ብላችሁ ብትኖሩ! ይህ ጥበብ በሆነላችሁ ነበር።

6. ፤ አሁንም ክርክሬን ስሙ፥ የከንፈሬንም ሙግት አድምጡ።

7. ፤ በውኑ ስለ እግዚአብሔር ሐሰትን ትናገራላችሁን? ስለ እርሱም ሽንገላን ታወራላችሁን?

8. ፤ ለፊቱስ ታደላላችሁን? ስለ እግዚአብሔርስ ትከራከራላችሁን?

9. ፤ ቢመረምራችሁስ መልካም ይሆንልችኋልን? ወይስ በሰው እንደምትሳለቁ ትሳለቁበታላችሁን?

10. ፤ በስውር ለሰው ፊት ብታደሉ ዘለፋ ይዘልፋችኋል።

11. ፤ ክብሩስ አያስፈራችሁምን? ግርማውስ አይወድቅባችሁምን?

12. ፤ ምስሌዎቻችሁ የአመድ ምሳሌዎች ናቸው፤ ምሽጎቻችሁ የጭቃ ምሽጎች ናቸው።

13. ፤ ዝም በሉ፥ እናገርም ዘንድ ተዉኝ፤ የሆነው ነገር ይምጣብኝ።

14. ፤ ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፥ ሕይወቴንም በእጄ አኖራለሁ።

15. ፤ እነሆ፥ ቢገድለኝ ስንኳ እርሱን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፤ ነገር ግን መንገዴን በፊቱ አጸናለሁ።

16. ፤ ዝንጉ ሰው በፊቱ አይገባምና እርሱ መድኃኒት ይሆንልኛል።

17. ፤ ነገሬን ተግታችሁ ስሙ፥ ምስክርነቴንም በጆሮአችሁ አድምጡ።

18. ፤ እነሆ፥ ሙግቴን አዘጋጅቻለሁ። እንደምጸድቅም አውቃለሁ።

19. ፤ ከእኔስ ጋር የሚፋረድ ማን ነው? አሁን እኔ ዝም ብል እሞታለሁ።

20. ፤ ነገር ግን ሁለት ነገር አታድርግብኝ፤ የዚያን ጊዜ ከፊትህ አልሰወርም፤

21. ፤ እጅህን ከእኔ አርቅ፤ ግርማህም አታስደንግጠኝ።

22. ፤ ከዚያም በኋላ ጥራኝ፥ እኔም እመልስልሃለሁ። ወይም እኔ ልናገር፥ አንተም መልስልኝ።

23. ፤ ያለብኝስ በደልና ኃጢአት ምን ያህል ነው? መተላለፌንና ኃጢአቴን አስታውቀኝ።

24. ፤ ፊትህን ከእኔ የሰወርህ፥ እንደ ጠላትህም የቈጠርኸኝ ስለ ምን ነው?

25. ፤ የረገፈውን ቅጠል ታስጨንቃለህን? ወይስ የደረቀውን ዕብቅ ታሳድዳለህን?

26. ፤ የመረረ ነገር ጽፈህብኛልና፤ የሕፃንነቴንም ኃጢአት ታወርሰኛለህ።

27. ፤ እግሬንም በእግር ግንድ አግብተሃል፥ መንገዴንም ሁሉ መርምረሃል፤ የእግሬን ፍለጋ ወስነሃል።

28. ፤ እኔ እንደሚጠፋ በስባሳ ነገር፥ ብልም እንደሚበላው ልብስ ነኝ።

About ኢዮብ Chapter 13

Read ኢዮብ Chapter 13 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ኢዮብ
Chapter: 13
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኢዮብ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ኢዮብ Chapter 13 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ኢዮብ Chapter 13?

ኢዮብ Chapter 13 is part of the Book of ኢዮብ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ኢዮብ Chapter 13 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 1
  3. አሞጽ Chapter 3
  4. አሞጽ Chapter 2
  5. አሞጽ Chapter 7
  6. አሞጽ Chapter 6
  7. አሞጽ Chapter 5

Explore More from ኢዮብ

  1. ኢዮብ Chapter 29
  2. ኢዮብ Chapter 17
  3. ኢዮብ Chapter 9
  4. ኢዮብ Chapter 15
  5. ኢዮብ Chapter 37
  6. ኢዮብ Chapter 36
  7. ኢዮብ Chapter 28

Related Chapters & Readings

  1. መኃልየ መኃልይ Chapter 1
  2. 1 ዜና መዋዕል Chapter 19
  3. 1 ነገሥት Chapter 15
  4. 2 ሳሙኤል Chapter 14
  5. ነህምያ Chapter 9
  6. 1 ነገሥት Chapter 21
  7. ኢሳይያስ Chapter 19
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *