Read ኢዮብ Chapter 40 Online
Read ኢዮብ Chapter 40 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኢዮብ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
ኢዮብ 40
ምዕራፍ 40
1. እግዚአብሔርም መለሰ ኢዮብንም እንዲህ አለው።
2. ፤ በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር ይከራከራልን? ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት።
3. ፤ ኢዮብም መለሰ እግዚአብሔርንም እንዲህ አለው።
4. ፤ እነሆ፥ እኔ ወራዳ ሰው ነኝ፤ የምመልስልህ ምንድር ነው? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ።
5. ፤ አንድ ጊዜ ተናገርሁ፥ አልመልስምም፤ ሁለተኛ ጊዜም፥ ከእንግዲህ ወዲህ አልናገርም።
6. ፤ እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰ እንዲህም አለ።
7. ፤ እንግዲህ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ተናገረኝ።
8. ፤ በውኑ ፍርዴን ታፈርሳለህን? አንተስ ጻድቅ ትሆን ዘንድ በእኔ ትፈርዳለህን?
9. ፤ እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን? ወይስ እንደ እርሱ ባለ ድምፅ ታንጐደጕዳለህን?
10. ፤ በታላቅነትና በልዕልና ተላበስ፤ በክብርና በግርማም ተጐናጸፍ።
11. ፤ የቍጣህን ፈሳሽ አፍስስ፤ ትዕቢተኛውንም ሁሉ ተመልክተህ አዋርደው።
12. ፤ ትዕቢተኛውንም ሁሉ ተመልከት፥ ዝቅ ዝቅም አድርገው፤ በደለኞችንም ወዲያውኑ እርገጣቸው።
13. ፤ በአፈር ውስጥ በአንድነት ሰውራቸው፤ በተሸሸገም ስፍራ ፊታቸውን ሸፍን።
14. ፤ በዚያን ጊዜም ቀኝ እጅህ ታድንህ ዘንድ እንድትችል እኔ ደግሞ እመሰክርልሃለሁ።
15. ፤ ከአንተ ጋር የሠራሁትን ጉማሬ፥ እስኪ፥ ተመልከት፤ እንደ በሬ ሣር ይበላል።
16. ፤ እነሆ፥ ብርታቱ በወገቡ ውስጥ ነው፤ ኃይሉም በሆዱ ጅማት ውስጥ ነው።
17. ፤ ጅራቱን እንደ ጥድ ዛፍ ያወዛውዛል፤ የወርቹ ጅማት የተጐነጐነ ነው።
18. ፤ አጥንቱ እንደ ናስ አገዳ ነው፤ አካላቱ እንደ ብረት ዘንጎች ናቸው።
19. ፤ እርሱ የእግዚአብሔር ፍጥረት አውራ ነው፤ ሠሪውም ሰይፉን ሰጠው።
20. ፤ የሜዳ እንስሶች ሁሉ የሚጫወቱበት ተራራ ምግብን ያበቅልለታል።
21. ፤ ጥላ ካለው ዛፍ በታች፥ በደንገልና በረግረግ ውስጥ ይተኛል።
22. ፤ ጥላ ያለው ዛፍ በጥላው ይሰውረዋል፤ የወንዝ አኻያ ዛፎች ይከብቡታል።
23. ፤ እነሆ፥ ወንዙ ቢጐርፍ አይደነግጥም፤ ዮርዳኖስም እስከ አፉ ድረስ ቢፈስስ እርሱ ይተማመናል።
24. ፤ ዓይኖቹ እያዩ ይያዛልን? አፍንጫውስ በወጥመድ ይበሳልን?
25. ፤ በውኑ አዞውን በመቃጥን ታወጣለህን? ምላሱንስ በገመድ ታስረዋለህን?
26. ፤ ወይስ ስናጋ በአፍንጫው ታደርጋለህን? ወይስ በችንካር ጕንጩን ትበሳለህን?
27. ፤ በውኑ ወደ አንተ እጅግ ይለምናልን? በጣፈጠስ ቃል ይናገርሃልን?
28. ፤ በውኑ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን ይገባልን? ወይስ ለዘላለም ባሪያ ታደርገዋለህን?
29. ፤ ከወፍ ጋር እንደምትጫወት ከእርሱ ጋር ትጫወታለህን? ወይስ ለሴት ባሪያዎችህ ታስረዋለህን?
30. ፤ አጥማጆች በእርሱ ይከራከራሉን? ወይስ ነጋዴዎች ያካፍሉታልን?
31. ፤ በውኑ ቁርበቱን በጭሬ፥ ራሱንስ በዓሣ ጦር ትሞላዋለህን?
32. ፤ እጅህን በላዩ ጫን፤ ሰልፉን አስብ፥ እንግዲህም አትድገም።
About ኢዮብ Chapter 40
Read ኢዮብ Chapter 40 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኢዮብ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: ኢዮብ
Chapter: 40
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኢዮብ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading ኢዮብ Chapter 40 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is ኢዮብ Chapter 40?
ኢዮብ Chapter 40 is part of the Book of ኢዮብ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete ኢዮብ Chapter 40 online for free with easy chapter navigation.