ምሳሌ Chapter 27

For English

Read ምሳሌ Chapter 27 Online

Read ምሳሌ Chapter 27 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ምሳሌ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ምሳሌ 27

ምዕራፍ 27

1. ቀን የሚያመጣውን ምን እንደ ሆነ አታውቅምና ነገ በሚሆነው አትመካ።

2. ሌላ ያመስግንህ እንጂ አፍህ አይደለም፤ ባዕድ ሰው እንጂ ከንፈርህ አይደለም።

3. ድንጋይ ከባድ ነው አሸዋም ሸክሙ ጽኑ ነው፤ ከሁለቱ ግን የሰነፍ ቍጣ ይከብዳል።

4. ቍጣ ምሕረት የሌለው ነው፥ መዓትም እንደ ጎርፍ ነው፤ በቅንዓት ፊት ግን ማን ይቆማል?

5. የተገለጠ ዘለፋ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል።

6. የወዳጅ ማቍሰል የታመነ ነው፤ የጠላት መሳም ግን የበዛ ነው።

7. የጠገበች ነፍስ የማር ወላላ ትረግጣለች፤ ለተራበች ነፍስ ግን የመረረ ነገር ሁሉ ይጣፍጣታል።

8. ስፍራውን የሚተው ሰው፤ ቤቱን ትቶ እንደሚበርር ወፍ ነው።

9. ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤ እንዲሁ ነፍስ በወዳጁ ምክር ደስ ይላታል።

10. ወዳጅህንና የአባትህን ወዳጅ አትተው፤ በመከራህም ቀን ወደ ወንድምህ ቤት አትግባ፤ የቀረበ ወዳጅ ከራቀ ወንድም ይሻላል።

11. ልጄ ሆይ፥ ጠቢብ ሁን፥ ልቤንም ደስ አሰኘው፥ ለሚሰድበኝ መልስ መስጠት ይቻለኝ ዘንድ።

12. ብልህ ሰው ክፉን አይቶ ይሸሸጋል፤ አላዋቂዎች ግን አልፈው ይጐዳሉ።

13. ለማያውቀው ከተዋሰ ሰው ልብሱን ውሰድ፥ ለእንግዳ የተዋሰውንም እርሱን አግተው።

14. ባልንጀራውን በታላቅ ቃል ማለዳ የሚባርክ ሰው እንደሚራገም ያህል ነው።

15. በዝናብ ቀን የሚያንጠባጥብ ቤትና ጠበኛ ሴት አንድ ናቸው፤

16. እርስዋንም መከልከል ነፍስን መከልከልና ዘይትን በቀኝ እጅ መጨበጥ ነው።

17. ብረት ብረትን ይስለዋል፥ ሰውም ባልንጀራውን ይስላል።

18. በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል።

19. ፊት በውኃ ላይ ለፊት እንደሚታይ፥ እንዲሁ የሰው ልብ ለሰው ይታያል።

20. ሲኦልና ጥፋት እንዳይጠግቡ፥ እንዲሁ የሰው ዓይን አይጠግብም።

21. ብር በከውር ወርቅም በማቅለጫ ይፈተናል፤ ሰውም በሚያመሰገኑት ሰዎች አፍ ይፈተናል።

22. ሰነፍን በሙቀጫ ውስጥ ከእህል ጋር በዘነዘና ብትወቅጠው፥ ስንፍናው ከእርሱ አይርቅም።

23. የበጎችህን መልክ አስተውለህ እወቅ፥ በከብቶችህም ላይ ልብህን አኑር፤

24. ባለጠግነት ለዘላለም አይኖርምና፥ ዘውድም ለትውልድ ሁሉ አይጸናምና።

25. ደረቅ ሣር በታጨደ ጊዜ፥ አዲስ ለምለም በታየ ጊዜ፥ ከተራራውም ቡቃያ በተሰበሰበ ጊዜ፥

26. በጎች ለልብስህ ፍየሎችም የእርሻ ዋጋ ይሆናሉ።

27. ለሲሳይህ ለቤተ ሰቦችህም ሲሳይ ለገረዶችህም ምግብ የፍየል ወተት ይበቃል።

About ምሳሌ Chapter 27

Read ምሳሌ Chapter 27 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ምሳሌ
Chapter: 27
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ምሳሌ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ምሳሌ Chapter 27 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ምሳሌ Chapter 27?

ምሳሌ Chapter 27 is part of the Book of ምሳሌ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ምሳሌ Chapter 27 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ምሳሌ

  1. ምሳሌ Chapter 19
  2. ምሳሌ Chapter 17
  3. ምሳሌ Chapter 15
  4. ምሳሌ Chapter 4
  5. ምሳሌ Chapter 23
  6. ምሳሌ Chapter 12
  7. ምሳሌ Chapter 3

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. 1 ሳሙኤል Chapter 7
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 14
  3. ኢዮብ Chapter 40
  4. ዘጸአት Chapter 4
  5. ነህምያ Chapter 6
  6. ዘፍጥረት Chapter 11
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 16

Related Chapters & Readings

  1. ዘጸአት Chapter 9
  2. ዘጸአት Chapter 26
  3. ሩት Chapter 1
  4. 2 ሳሙኤል Chapter 1
  5. ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 1
  6. ነህምያ Chapter 9
  7. ሆሴዕ Chapter 12
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *