Read ዘዳግም Chapter 9 Online
Read ዘዳግም Chapter 9 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዘዳግም in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ዘዳግም and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
ዘዳግም 9
ምዕራፍ 9
1. እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ከአንተ የበለጡትንና የበረቱትን አሕዛብ፥ እስከ ሰማይም ድረስ የተመሸጉትን ታላላቆች ከተሞች ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ዛሬ ዮርዳኖስን ትሻገረዋለህ።
2. ፤ አንተም የምታውቃቸው ስለ እነርሱም። በዔናቅ ልጆች ፊት መቆም ማን ይችላል? ሲባል የሰማኸው ታላቁና ረጅሙ ሕዝብ የዔናቅ ልጆች ናቸው።
3. ፤ አምላክህም እግዚአብሔር እንደሚበላ እሳት ሆኖ በፊትህ እንዲያልፍ ዛሬ እወቅ፤ እርሱ ያጠፋቸዋል፥ በፊትህም ያዋርዳቸዋል፤ እግዚአብሔርም እንደ ነገረህ አንተ ታሳድዳቸዋለህ፥ ፈጥነህም ታጠፋቸዋለህ።
4. ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ካወጣቸው በኋላ። ስለ ጽድቄ እወርሳት ዘንድ ወደዚች ምድር እግዚአብሔር አገባኝ ስትል በልብህ አትናገር፤ እነዚህን አሕዛብ ስለ ኃጢአታቸው እግዚአብሔር ከፊትህ ያወጣቸዋል።
5. ፤ ምድራቸውን ትወርሳት ዘንድ የምትገባው ስለ ጽድቅህና ስለ ልብህ ቅንነት አይደለም፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ በሚያጠፋቸው በእነዚያ አሕዛብ ኃጢአት ምክንያትና ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውን ቃል ይፈጽም ዘንድ ነው።
6. ፤ እንግዲህ አንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነህና አምላክህ እግዚአብሔር ይህችን መልካም ምድር ርስት አድርጎ የሰጠህ ስለ ጽድቅህ እንዳይደለ እወቅ።
7. ፤ አምላክህን እግዚአብሔርን በምድረ በዳ እንዳስቈጣኸው፤ ከግብፅ አገር ከወጣህበት ቀን ጀምሮ ወደዚህ ስፍራ እስከ መጣችሁ ድረስ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፃችሁ አስብ፥ አትርሳ።
8. ፤ በኮሬብ ደግሞ እግዚአብሔርን አስቈጣችሁ፤ እግዚአብሔርም ሊያጠፋችሁ ተቈጣባችሁ።
9. ፤ የድንጋዩን ጽላቶች፥ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የተማማለባቸውን የቃል ኪዳን ጽላቶች፥ እቀበል ዘንድ ወደ ተራራ በወጣሁ ጊዜ፥ በተራራው አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተቀምጬ ነበር፤ እንጀራ አልበላሁም፥ ውኃም አልጠጣሁም።
10. ፤ እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ጣት የተጻፋትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ሰጠኝ፤ ስብሰባ ተደርጎ በነበረበትም ቀን እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ የነገራችሁ ቃል ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር።
11. ፤ ከአርባ ቀንና ከአርባ ሌሊትም በኋላ እግዚአብሔር ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች፥ የቃል ኪዳኑን ጽላቶች፥ ሰጠኝ።
12. ፤ እግዚአብሔርም። ተነሥተህ ከዚህ ፈጥነህ ውረድ፤ ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ረክሰዋል፤ ፈጥነው ካዘዝኋቸው መንገድ ፈቀቅ ብለዋል፥ ቀልጦ የተሠራ ምስልም ለራሳቸው አድርገዋል አለኝ።
13. ፤ እግዚአብሔርም። ይህ ሕዝብ አንገተ ደንዳና ሕዝብ እንደሆነ አይቼአለሁ፤
14. ፤ አጠፋቸው ዘንድ፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች እደመስስ ዘንድ ተወኝ፤ አንተንም ከእነርሱ ለሚበረታና ለሚበዛ ሕዝብ አደርግሃለሁ ብሎ ተናገረኝ።
15. ፤ እኔም ተመልሼ ከተራራው ወረድሁ፥ ተራራውም በእሳት ይነድድ ነበር፤ ሁለቱም የቃል ኪዳን ጽላቶች በሁለቱ እጆቼ ነበሩ።
16. ፤ ተመለከትሁም፤ እነሆ፥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በድላችሁ ነበር፥ ለእናንተም ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ሠርታችሁ ነበር፤ እግዚአብሔር ካዘዛችሁ መንገድ ፈጥናችሁ ፈቀቅ ብላችሁ ነበር።
17. ፤ ሁለቱንም ጽላቶች ያዝሁ፥ ከሁለቱም እጆቼ ጣልኋቸው፥ እናንተም ስታዩ ሰበርኋቸው።
18. ፤
19. ፤ ስለ ሠራችሁት ኃጢአት ሁሉ፥ እርሱንም ለማስቈጣት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ስላደረጋችሁ፥ እግዚአብሔር ሊያጠፋችሁ ከተቈጣባችሁ ከቍጣውና ከመዓቱ የተነሣ ስለ ፈራሁ፥ እንደ ፊተኛው በእግዚአብሔር ፊት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ወደቅሁ፤ እንጀራ አልበላሁም፥ ውኃም አልጠጣሁም። እግዚአብሔርም በዚያን ጊዜ ደግሞ ሰማኝ።
20. ፤ እግዚአብሔርም አሮንን ሊያጠፋው እጅግ ተቈጣው፤ ስለ አሮንም ደግሞ በዚያን ጊዜ ጸለይሁ።
21. ፤ ያደረጋችሁትንም ኃጢአት ጥጃውን ወሰድሁ፥ በእሳትም አቃጠልሁት፥ አደቀቅሁትም፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨሁት፤ ትቢያውንም ከተራራ በሚወርድ ወንዝ ጣልሁት።
22. ፤ በተቤራም በማሳህም በምኞት መቃብርም እግዚአብሔርን አስቈጣችሁት።
23. ፤ እግዚአብሔርም። ውጡ የሰጠኋችሁንም ምድር ውረሱ ብሎ ከቃዴስ በርኔ በላካችሁ ጊዜ፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ቃል ዐመፃችሁ፥ በእርሱም አላመናችሁም፥ ድምፁንም አልሰማችሁም።
24. ፤ እናንተን ካወቅሁበት ቀን ጀምሮ በእግዚአብሔር ዓመፀኞች ነበራችሁ።
25. ፤ እግዚአብሔርም። አጠፋችኋለሁ ብሎ ስለ ተናገረ በወደቅሁበት ዘመን አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእግዚአብሔር ፊት ወደቅሁ።
26. ፤ በእግዚአብሔርም ፊት እንዲህ ብዬ ጸለይሁ። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ በታላቅነትህ የተቤዠኸውን፥ በጠነከረችውም እጅ ከግብፅ ያወጣኸውን ሕዝብህንና ርስትህን አታጥፋ።
27. ፤ ባሪያዎችህን አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም አስብ፤ የዚህን ሕዝብ ደንዳንነት ክፋቱንም ኃጢአቱንም አትመልከት፤
28. ፤ ከእርስዋ እኛን ያወጣህባት ምድር ሰዎች። እግዚአብሔር ተስፋ ወደ ሰጣቸው ምድር ያገባቸው ዘንድ አልቻለምና፥ ጠልቶአቸውማልና ስለዚህ በምድረ በዳ ሊገድላቸው አወጣቸው እንዳይሉ።
29. ፤ እነርሱም በታላቅ ኃይልህ በተዘረጋውም ክንድህ ያወጣሃቸው ሕዝብህና ርስትህ ናቸው።
About ዘዳግም Chapter 9
Read ዘዳግም Chapter 9 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዘዳግም in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: ዘዳግም
Chapter: 9
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ዘዳግም. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading ዘዳግም Chapter 9 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is ዘዳግም Chapter 9?
ዘዳግም Chapter 9 is part of the Book of ዘዳግም in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete ዘዳግም Chapter 9 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from ብሉይ ኪዳን
Explore More from ዘዳግም
- ዘዳግም Chapter 15
- ዘዳግም Chapter 29
- ዘዳግም Chapter 1
- ዘዳግም Chapter 8
- ዘዳግም Chapter 23
- ዘዳግም Chapter 28
- ዘዳግም Chapter 34