1 ሳሙኤል Chapter 7

For English

Read 1 ሳሙኤል Chapter 7 Online

Read 1 ሳሙኤል Chapter 7 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ሳሙኤል and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

1 ሳሙኤል 7

ምዕራፍ 7

1. የቂርያትይዓሪም ሰዎችም መጥተው የእግዚአብሔርን ታቦት አወጡ፥ በኮረብታውም ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት አገቡት፤ የእግዚአብሔርም ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት።

2. ፤ ታቦቱም በቂርያትይዓሪም ከተቀመጠበት ቀን ጀምሮ ወራቱ ረዘመ፥ ሀያ ዓመትም ሆነ፤ የእስራኤልም ቤት ሁሉ አዝኖ እግዚአብሔርን ተከተለ።

3. ፤ ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ። በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ እግዚአብሔር አቅኑ፥ እርሱንም ብቻ አምልኩ፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ያድናችኋል ብሎ ተናገራቸው።

4. ፤ የእስራኤልም ልጆች በኣሊምንና አስታሮትን አራቁ፥ እግዚአብሔርንም ብቻ አመለኩ።

5. ፤ ሳሙኤልም። እስራኤልን ሁሉ ወደ ምጽጳ ሰብስቡ፥ ስለ እናንተም ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ አለ።

6. ፤ ወደ ምጽጳም ተሰበሰቡ፤ ውኃም ቀድተው በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሱ፥ በዚያም ቀን ጾሙ፥ በዚያም። እግዚአብሔርን በድለናል አሉ። ሳሙኤልም በእስራኤል ልጆች ላይ በምጽጳ ፈረደ።

7. ፤ ፍልስጥኤማውያንም የእስራኤል ልጆች ወደ ምጽጳ እንደ ተሰበሰቡ በሰሙ ጊዜ የፍልስጥኤማውያን አለቆች በእስራኤል ላይ ወጡ፤ የእስራኤልም ልጆች ሰምተው ፍልስጥኤማውያንን ፈሩ።

8. ፤ የእስራኤልም ልጆች ሳሙኤልን። ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድነን ዘንድ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ትጸልይልን ዘንድ አትታክት አሉት።

9. ፤ ሳሙኤልም አንድ የሚጠባ የበግ ጠቦት ወስዶ ለእግዚአብሔር ፈጽሞ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው፤ ሳሙኤልም ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው።

10. ፤ ሳሙኤልም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሲያሳርግ ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር ሊዋጉ ቀረቡ፤ እግዚአብሔርም በዚያች ቀን በፍልስጥኤማውያን ላይ ታላቅ ነጐድጓድ አንጐደጐደ፥ አስደነገጣቸውም በእስራኤልም ፊት ድል ተመቱ።

11. ፤ የእስራኤልም ሰዎች ከምጽጳ ወጡ፥ ፍልስጥኤማውያንንም አሳደዱ፤ በቤትካር ታችም እስኪደርሱ ድረስ መቱአቸው።

12. ፤ ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አኖረው፤ ስሙንም። እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።

13. ፤ ፍልስጥኤማውያንም ተዋረዱ፥ ዳግመኛም ከዚያ ወዲያ ወደ እስራኤል ድንበር አልወጡም፤ በሳሙኤል ዕድሜ ሁሉ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ነበረች።

14. ፤ ፍልስጥኤማውያንም ከአስቀሎና ጀምሮ እስከ ጌት ድረስ ከእስራኤል የወሰዱአቸው ከተሞች ለእስራኤል ተመለሱ፤ እስራኤልም ድንበሩን ከፍልስጥኤማውያን እጅ አዳነ። በእስራኤልና በአሞራውያንም መካከል ዕርቅ ነበረ።

15. ፤ ሳሙኤልም በዕድሜው ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር።

16. ፤ በየዓመቱም ወደ ቤቴል ወደ ጌልገላ ወደ ምጽጳም ይዞር ነበር፤ በእነዚያም ስፍራዎች ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር።

17. ፤ ቤቱም በዚያ ነበረና ወደ አርማቴም ይመለስ ነበር፤ በዚያም በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።

About 1 ሳሙኤል Chapter 7

Read 1 ሳሙኤል Chapter 7 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 1 ሳሙኤል
Chapter: 7
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ሳሙኤል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 1 ሳሙኤል Chapter 7 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 1 ሳሙኤል Chapter 7?

1 ሳሙኤል Chapter 7 is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 1 ሳሙኤል Chapter 7 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 1 ሳሙኤል

  1. 1 ሳሙኤል Chapter 9
  2. 1 ሳሙኤል Chapter 30
  3. 1 ሳሙኤል Chapter 22
  4. 1 ሳሙኤል Chapter 20
  5. 1 ሳሙኤል Chapter 13
  6. 1 ሳሙኤል Chapter 3
  7. 1 ሳሙኤል Chapter 29

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ኢዮብ Chapter 5
  2. ዕዝራ Chapter 4
  3. ሆሴዕ Chapter 13
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 145
  5. ኤርምያስ Chapter 23
  6. ነህምያ Chapter 12
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 39

Related Chapters & Readings

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 51
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 74
  3. ኢሳይያስ Chapter 42
  4. መኃልየ መኃልይ Chapter 6
  5. ዘፍጥረት Chapter 24
  6. ሆሴዕ Chapter 3
  7. መክብብ Chapter 5
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *