Read ምሳሌ Chapter 21 Online
Read ምሳሌ Chapter 21 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ምሳሌ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
ምሳሌ 21
ምዕራፍ 21
1. የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል።
2. የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለች፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል።
3. እግዚአብሔር ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ቅን ነገርን ማድረግ ይወድዳል።
4. ትዕቢተኛ ዓይንና ደፋር ልብ የኀጥኣንም እርሻ ኃጢአት ነው።
5. የትጉህ አሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፤ ችኵል ሰው ሁሉ ግን ለመጕደል ይቸኩላል።
6. በሐሰተኛ ምላስ መዝገብ ማከማቸት የሚበንን ጉም ነው፤ ይህን የሚፈልጉ ሞትን ይፈልጋሉ።
7. ቅን ነገርን ያደርጉ ዘንድ አይወድዱምና የኀጥኣን ንጥቂያ ራሳቸውን ያጠፋቸዋል።
8. የበደለኛ መንገድ የጠመመች ናት፤ የንጹሕ ሥራ ግን የቀና ነው።
9. ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ከመቀመጥ በውጪ በቤት ማዕዘን ላይ መቀመጥ ይሻላል።
10. የኀጥእ ነፍስ ክፉን ትመኛለች፥ በፊቱም ባልንጀራው ሞገስን አያገኝም።
11. ፌዘኛ ቅጣትን በተቀበለ ጊዜ አላዋቂ ሰው ጥበብን ያገኛል፤ ጠቢብም ቢማር እውቀትን ይቀበላል።
12. ጻድቅ ስለ ኀጥእ ቤት ያስባል፥ ኀጥኣንም ለጥፋት እንደ ተገለበጡ።
13. የድሀውን ጩኸት እንዳይሰማ ጆሮውን የሚደፍን ሰው፥ እርሱ ራሱ ይጮኻል አይሰማለትምም።
14. ስጦታ በስውር ቍጣን ታጠፋለች፥ የብብትም ውስጥ ጉቦ ጽኑ ቍጣን ታበርዳለች።
15. ፍርድን ማድረግ ለጻድቅ ደስታ ነው፤ ኃጢአትን ለሚያደርጉ ግን ጥፋት ነው።
16. ከማስተዋል መንገድ የሚሳሳት ሰው በሙታን ጉባኤ ያርፋል።
17. ተድላ የሚወድድ ድሀ ይሆናል፥ የወይን ጠጅንና ዘይትንም የሚወድድ ባለጠጋ አይሆንም።
18. ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው፤ በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ነው።
19. ከጠበኛና ከቍጡ ሴት ጋር ከመቀመጥ በምድረ በዳ መቀመጥ ይሻላል።
20. የከበረ መዝገብና ዘይት በጠቢብ ሰው ቤት ይኖራል። አእምሮ የሌለው ሰው ግን ይውጠዋል።
21. ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል ሕይወትንና ጽድቅን ክብርንም ያገኛል።
22. ጠቢብ የኃያላንን ከተማ ይገባባታል፥ የሚታመኑበትንም ኃይል ያፈርሳል።
23. አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል።
24. ኵሩና ተጓዳጅ ሰው ፌዘኛ ይባላል፤ እርሱም በትዕቢት ቍጣ ያደርጋል።
25. ታካችን ምኞቱ ትገድለዋለች፥ እጆቹ ይሠሩ ዘንድ አይፈቅዱምና።
26. ኀጥእ ቀኑን ሁሉ ምኞትን ይመኛል፤ ጻድቅ ግን ይሰጣል፥ አይሰስትም።
27. የኀጥኣን መሥዋዕት አስጸያፊ ነው፤ ይልቁንም በክፉ አሳብ ሲያቀርቡት አስጸያፊ ነው።
28. ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፤ የሚሰማ ሰው ግን ተጠንቅቆ ይናገራል።
29. ኀጥእ ፊቱን ያጠነክራል፤ ቅን ሰው ግን መንገዱን ያጸናል።
30. ጥበብ ወይም ማስተዋል ወይም ምክር በእግዚአብሔር ላይ የለም።
31. ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤ ድል ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
About ምሳሌ Chapter 21
Read ምሳሌ Chapter 21 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: ምሳሌ
Chapter: 21
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ምሳሌ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading ምሳሌ Chapter 21 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is ምሳሌ Chapter 21?
ምሳሌ Chapter 21 is part of the Book of ምሳሌ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete ምሳሌ Chapter 21 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from ምሳሌ
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- ኢዮብ Chapter 15
- ኢዮብ Chapter 17
- ኢያሱ Chapter 1
- ኤርምያስ Chapter 21
- ዘጸአት Chapter 9
- ኢሳይያስ Chapter 65
- ዳንኤል Chapter 7