Read ምሳሌ Chapter 23 Online
Read ምሳሌ Chapter 23 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ምሳሌ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
ምሳሌ 23
ምዕራፍ 23
1. ከመኰንን ጋር ለመብላት በተቀመጥህ ጊዜ፥ በፊትህ ያለውን በደኅና አስተውል፤
2. ሰውነትህም ቢሳሳ፥ በጕሮሮህ ላይ ካራ አድርግ።
3. ጣፋጩ መብል አይመርህ የሐሰት እንጀራ ነውና።
4. ባለጠጋ ለመሆን አትድከም፤ የገዛ ራስህን ማስተዋል ተው።
5. በእርሱ ላይ ዓይንህን ብታዘወትርበት ይጠፋል፤ ባለጠግነት ወደ ሰማይ እንደሚበርር እንደ ንስር ለራሱ ክንፍ ያበጃልና።
6. የቀናተኛን ሰው እንጀራ አትብላ፥ ጣፋጩ መብልም አይመርህ፤
7. በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፤ ብላ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ካንተ ጋር አይደለም።
8. የበላኸውን መብል ትተፋዋለህ፥ ያማረውንም ቃልህን ታጠፋዋለህ።
9. በሰነፍ ጆሮ አንዳች አትናገር፥ የቃልህን ጥበብ ያፌዝብሃልና።
10. የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍልስ፤ ወደ ድሀ አደጎች እርሻ አትግባ፤
11. ታዳጊአቸው ጽኑ ነውና፥ እርሱም ፍርዳቸውን ከአንተ ጋር ይፋረዳልና።
12. ልብህን ለተግሣጽ ስጥ፥ ጆሮህንም ወደ እውቀት ቃል።
13. ሕፃንን ከመቅጣት ቸል አትበል፥ በበትር ብትመታው አይሞትምና።
14. በበትር ትመታዋለህ፥ ነፍሱንም ትታደጋለህ።
15. ልጄ ሆይ፥ ልብህ ጠቢብ ቢሆን ልቤ ደግሞ ደስ ይለዋል፤
16. ከንፈሮችህም በቅን ቢናገሩ ኵላሊቶቼ ደስ ይላቸዋል።
17. ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፤ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር፤
18. በእውነት ፍጻሜ አለህና፥ ተስፋህም አይጠፋምና።
19. ልጄ ሆይ፥ ስማ ጠቢብም ሁን ልብህንም በቀናው መንገድ ምራ።
20. የወይን ጠጅ ከሚጠጡ ጋር አትቀመጥ ለሥጋም ከሚሣሡ ጋር፤
21. ሰካርና ሆዳም ይደኸያሉና፥ የእንቅልፍም ብዛት የተቦጫጨቀ ጨርቅ ያስለብሳልና።
22. የወለደህን አባትህን ስማ፥ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።
23. እውነትን ግዛ አትሽጣትም፥ ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም።
24. የጻድቅ አባት እጅግ ደስ ይለዋል፥ ጠቢብንም ልጅ የወለደ ሐሤትን ያገኛል።
25. አባትህና እናትህ ደስ ይበላቸው፥ አንተንም የወለደች ደስ ይበላት።
26. ልጄ ሆይ፥ ልብህን ስጠኝ፥ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ፤
27. ጋለሞታ ሴት የጠለቀች ዐዘቅት ናትና፥ ሌላይቱም ሴት የጠበበች ጕድጓድ ናትና።
28. እንደ ሌባ ታደባለች ወስላቶችንም በሰው ልጆች መካከል ታበዛለች።
29. ዋይታ ለማን ነው? ኀዘን ለማን ነው? ጠብ ለማን ነው? ጩኸት ለማን ነው? ያለ ምክንያት መቍሰል ለማን ነው? የዓይን ቅላት ለማን ነው?
30. የወይን ጠጅ በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን? የተደባለቀ የወይንን ጠጅ ይፈትኑ ዘንድ ለሚከተሉ አይደለምን?
31. ወደ ወይን ጠጅ አትመልከት በቀላ ጊዜ፥ መልኩም በብርሌ ባንጸባረቀ ጊዜ፥ እየጣፈጠም በገባ ጊዜ።
32. በኋላ እንደ እባብ ይነድፋል፥ እንደ እፉኝትም መርዙን ያፈስሳል።
33. ዓይኖችህ ጋለሞታዎችን ያያሉ፥ ልብህም ጠማማ ነገርን ይናገራል።
34. በባሕር ውስጥ እንደ ተኛ ትሆናለህ፥ በደቀልም ላይ እንደ ተኛ።
35. መቱኝ፥ ያውም አልተሰማኝም፤ ጐሰሙኝ፥ አላወቅሁምም። መቼ እነሣለሁ? ደግሞ ጨምሬ እሻታለሁ ትላለህ።
About ምሳሌ Chapter 23
Read ምሳሌ Chapter 23 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: ምሳሌ
Chapter: 23
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ምሳሌ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading ምሳሌ Chapter 23 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is ምሳሌ Chapter 23?
ምሳሌ Chapter 23 is part of the Book of ምሳሌ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete ምሳሌ Chapter 23 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from ምሳሌ
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- ኢሳይያስ Chapter 1
- ዘፍጥረት Chapter 21
- ዳንኤል Chapter 6
- ሶፎንያስ Chapter 3
- ዘሌዋውያን Chapter 22
- ሆሴዕ Chapter 8
- ዘካርያስ Chapter 10