ምሳሌ Chapter 17

For English

Read ምሳሌ Chapter 17 Online

Read ምሳሌ Chapter 17 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ምሳሌ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ምሳሌ 17

ምዕራፍ 17

1. ጥል ባለበት ዘንድ እርድ ከሞላበት ቤት በጸጥታ ደረቅ ቍራሽ ይሻላል።

2. አስተዋይ ባሪያ ነውረኛውን ልጅ ይገዛል፥ በወንድማማች መካከልም ርስትን ይካፈላል።

3. ማቅለጫ ለብር፥ ከውር ለወርቅ ነው፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይፈትናል።

4. ክፉ ሰው የበደለኛን ከንፈር ይሰማል፤ ሐሰተኛም ወደ ተንኰለኛ ምላስ ያደምጣል።

5. በድሀ የሚያላግጥ ፈጣሪውን ይሰድባል፤ በጥፋትም ደስ የሚለው ሳይቀጣ አይቀርም።

6. የሽማግሌዎች አክሊል የልጅ ልጆች ናቸው፤ የልጆችም ክብር አባቶቻቸው ናቸው።

7. ለሰነፍ የኵራት አነጋገር አይገባውም፤ ይልቁንም ሐሰተኛ ከንፈር ለመኰንን አይገባውም።

8. ገንዘብ ባደረገው ፊት መማለጃ እንደ ተዋበ ዕንቍ ነው፥ ወደ ዞረበትም ስፍራ ሁሉ ሥራውን ያቀናል።

9. ኃጢአትን የሚከድን ሰው ፍቅርን ይሻል፤ ነገርን የሚደጋግም ግን የተማመኑትን ወዳጆቹን ይለያያል።

10. መቶ ግርፋት በሰነፍ ጠልቆ ከሚገባ ይልቅ ተግሣጽ በአስተዋይ ሰው ጠልቆ ወደ ልቡ ይገባል።

11. ክፉ ሰው ዓመፃን ብቻ ይሻል፤ ስለዚህ ጨካኝ መልአክ ይላክበታል።

12. ሰነፍን በስንፍናው ከመገናኘት ልጆችዋ የተነጠቁባትን ድብ መገናኘት ይሻላል።

13. በመልካም ፋንታ ክፉን የሚመልስ፥ ክፉ ነገር ከቤቱ አትርቅም።

14. የጠብ መጀመሪያ እንደ ውኃ አፈሳሰስ ነው፤ ስለዚህ ጠብ ሳይበረታ አንተ ክርክርን ተው።

15. ኀጥኡን የሚያጸድቅና በጻድቁ ላይ የሚፈርድ፥ ሁለቱ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው።

16. በሰነፍ እጅ የጥበብ መግዣ ገንዘብ መኖሩ ስለ ምንድር ነው? ጥበብን ይገዛ ዘንድ አእምሮ የለውምና።

17. ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወድዳል፤ ወንድምም ለመከራ ይወለዳል።

18. አእምሮ የጐደለው ሰው አጋና ይመታል፥ በባልንጀራውም ፊት ይዋሳል።

19. ዓመፃን የሚወድድ ክርክርን ይወድዳል፤ ደጁንም ዘለግ የሚያደርግ ውድቀትን ይሻል።

20. ጠማማ ልብ ያለው መልካምን አያገኝም፥ ምላሱንም የሚገለብጥ በክፉ ላይ ይወድቃል።

21. ሰነፍን የሚወልድ ኀዘን ይሆንበታል፥ የደንቆሮ ልጅም አባት ደስ አይለውም።

22. ደስ ያላት ልብ መልካም መድኃኒት ናት፤ ያዘነች ነፍስ ግን አጥንትን ታደርቃለች።

23. ኀጥእ የፍርድን መንገድ ለማጥመም ከብብት መማለጃን ይወስዳል።

24. በአስተዋይ ፊት ጥበብ ትኖራለች፤ የሰነፍ ዓይን ግን በምድር ዳርቻ ነው።

25. ሰነፍ ልጅ ለአባቱ ፀፀት ነው፥ ለወለደችውም ምሬት ነው።

26. ጻድቅን መቅጣት፥ ጨዋ ሰውንም በጻድቅነቱ መምታት መልካም አይደለም።

27. ጥቂት ቃልን የሚናገር አዋቂ ነው፥ መንፈሱም ቀዝቃዛ የሆነ አስተዋይ ነው።

28. ሰነፍ ዝም ቢል ጠቢብ ሆኖ ይቈጠራል፥ ከንፈሩንም የሚቈልፍ። ባለ አእምሮ ነው ይባላል።

About ምሳሌ Chapter 17

Read ምሳሌ Chapter 17 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ምሳሌ
Chapter: 17
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ምሳሌ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ምሳሌ Chapter 17 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ምሳሌ Chapter 17?

ምሳሌ Chapter 17 is part of the Book of ምሳሌ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ምሳሌ Chapter 17 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ምሳሌ

  1. ምሳሌ Chapter 29
  2. ምሳሌ Chapter 24
  3. ምሳሌ Chapter 4
  4. ምሳሌ Chapter 19
  5. ምሳሌ Chapter 15
  6. ምሳሌ Chapter 1
  7. ምሳሌ Chapter 31

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ሕዝቅኤል Chapter 19
  2. ዘፍጥረት Chapter 10
  3. ኤርምያስ Chapter 40
  4. 1 ሳሙኤል Chapter 12
  5. መዝሙረ ዳዊት Chapter 102
  6. ዘኍልቍ Chapter 31
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 83

Related Chapters & Readings

  1. ምሳሌ Chapter 18
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 124
  3. 2 ዜና መዋዕል Chapter 28
  4. ዘፍጥረት Chapter 21
  5. 1 ሳሙኤል Chapter 2
  6. ማርቆስ Chapter 7
  7. 1 ቆሮንቶስ Chapter 16
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *