ምሳሌ Chapter 9

For English

Read ምሳሌ Chapter 9 Online

Read ምሳሌ Chapter 9 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ምሳሌ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ምሳሌ 9

ምዕራፍ 9

1. ጥበብ ቤትዋን ሠራች፥ ሰባቱንም ምሰሶችዋን አቆመች።

2. ፍሪዳዋን አረደች፥ የወይን ጠጅዋን ደባለቀች፥ ማዕድዋን አዘጋጀች።

3. ባሪያዎችዋን ልካ በከተማይቱ ከፍተኛ ስፍራ ላይ ጠራች።

4. አላዋቂ የሆነ ወደዚህ ፈቀቅ ይበል፤ አእምሮ የጐደላቸውንም እንዲህ አለች።

5. ኑ፥ እንጀራዬን ብሉ፥ የደባለቅሁትንም የወይን ጠጅ ጠጡ።

6. አላዋቂነትን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥ በማስተዋልም መንገድ ሂዱ።

7. ፌዘኛን የሚገሥጽ ለራሱ ስድብን ይቀበላል፥ ኅጥአንም የሚዘልፍ ነውርን ያገኛል።

8. ፌዘኛን አትገሥጽ እንዳይጠላህ፤ ጠቢብን ገሥጽ ይወድድህማል።

9. ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጽድቅንም አስተምረው፥ እውቀትንም ያበዛል።

10. የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው።

11. ዘመንህ በእኔ ይበዛልና፥ የሕይወትህም ዕድሜ ይጨመርልሃልና።

12. ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ጠቢብ ትሆናለህ፥ ፌዘኛም ብትሆን ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከማለህ። ፍን [የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።] ልጄ ለራስህ አዋቂ ብትሆን ለባልንጀራህም አዋቂ ትሆናለህ፤ ለራስህ ክፉ ብትሆን ግን ክፋትህን ትማራለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚያዘጋጅ ሰው ነው፤ የሚበርር ወፍንም እንደሚከተል ይመስላል። የወይኑ ቦታ መንገዱን ተወ፤ የሚሠማራባትን መንገድ ዘነጋ፤ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል ለጥም ወደ ተሠራች አገር ይሄዳል፤ የማያፈራ የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።

13. ሰነፍ ሴት ሁከተኛ ናት፤ አሳብ የላትም፥ አንዳችም አታውቅም።

14. በቤትዋ ደጅ በከተማይቱ ከፍተኛ ስፍራ በወንበር ላይ ትቀመጣለች፥

15. በመንገድ የሚያልፉትን አካሄዳቸውንም ያቀኑትን ለመጥራት።

16. አላዋቂ የሆነ ወደዚህ ፈቀቅ ይበል፤ አእምሮ የጐደለውንም እንዲህ አለች።

17. የስርቆት ውኃ ይጣፍጣል፥ የተሸሸገም እንጀራ ደስ ያሰኛል።

18. ነገር ግን እርሱ ሙታን ከዚያ እንዳሉ፥ እድምተኞችዋም በሲኦል ጥልቀት እንዳሉ አያውቅም።

About ምሳሌ Chapter 9

Read ምሳሌ Chapter 9 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ምሳሌ
Chapter: 9
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ምሳሌ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ምሳሌ Chapter 9 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ምሳሌ Chapter 9?

ምሳሌ Chapter 9 is part of the Book of ምሳሌ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ምሳሌ Chapter 9 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ምሳሌ

  1. ምሳሌ Chapter 19
  2. ምሳሌ Chapter 17
  3. ምሳሌ Chapter 15
  4. ምሳሌ Chapter 4
  5. ምሳሌ Chapter 30
  6. ምሳሌ Chapter 26
  7. ምሳሌ Chapter 24

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 2
  2. ዘካርያስ Chapter 8
  3. ዘካርያስ Chapter 11
  4. 1 ዜና መዋዕል Chapter 23
  5. 2 ዜና መዋዕል Chapter 13
  6. ሕዝቅኤል Chapter 39
  7. ዘጸአት Chapter 14

Related Chapters & Readings

  1. ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 1
  2. ኤርምያስ Chapter 32
  3. ሕዝቅኤል Chapter 14
  4. ኢሳይያስ Chapter 18
  5. መሳፍንት Chapter 1
  6. ኢዮብ Chapter 39
  7. 2 ዜና መዋዕል Chapter 28
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *