ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 1

For English

Read ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 1 Online

Read ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሰቆቃወ ኤርምያስ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ሰቆቃወ ኤርምያስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ሰቆቃወ ኤርምያስ 1

ምዕራፍ 1

1. አሌፍ። ሕዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ ብቻዋን እንዴት ተቀመጠች! በአሕዛብ መካከል ታላቅ የነበረች እንደ መበለት ሆናለች፤ በአውራጆች መካከል ልዕልት የነበረች ተገዢ ሆናለች።

2. ፤ ቤት። በሌሊት እጅግ ታላቅሳለች፥ እንባዋም በጕንጭዋ ላይ አለ፤ ከውሽሞችዋ ሁሉ የሚያጽናናት የለም፤ ወዳጆችዋ ሁሉ ወነጀሉአት ጠላቶችም ሆኑአት።

3. ፤ ጋሜል። ይሁዳ ስለ መጨነቅና ስለ ባርነት ብዛት ተማረከች፤ በአሕዛብ መካከል ተቀመጠች ዕረፍትም አላገኘችም፤ የሚያስጨንቁአት ሁሉ ተጨንቃ አገኙአት።

4. ፤ ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓልም የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፤ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል ካህናቶችዋም እየጮኹ ያለቅሳሉ፤ ደናግሎችዋም ተጨነቁ እርስዋም በምሬት አለች።

5. ፤ ሄ። ስለ ኃጢአትዋ ብዛት እግዚአብሔር አስጨንቆአታልና አስጨናቂዎችዋ ራስ ሆኑ ጠላቶችዋም ተከናወነላቸው፤ ሕፃናቶችዋ በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል።

6. ፤ ዋው። ከጽዮን ሴት ልጅ ውበትዋ ሁሉ ወጥቶአል፤ አለቆችዋ ማሰማርያ እንደማያገኙ ዋላዎች ሆኑ፤ ከሚያባርሩአቸው ፊት ተዳክመው ሄዱ።

7. ፤ ዛይ። ኢየሩሳሌም በጭንቀትዋና በመከራዋ ወራት ከጥንት ጀምሮ የነበረላትን የከበረን ነገር ሁሉ አሰበች፤ ሕዝብዋ በአስጨናቂዎች እጅ በወደቀ ጊዜ የሚረዳትም በሌላት ጊዜ፥ አስጨናቂዎች አዩአት በመፍረስዋም ሳቁ።

8. ፤ ሔት። ኢየሩሳሌም እጅግ ኃጢአት ሠርታለች፤ ስለዚህ ረክሳለች፤ ያከብሩአት የነበሩ ሁሉ ኀፍረተ ሥጋዋን አይተዋታልና አቃለሉአት፤ እርስዋም እየጮኸች ታለቅሳለች ወደ ኋላም ዘወር አለች።

9. ፤ ጤት። አደፍዋ በልብስዋ ዘርፍ ነበረ፤ ፍጻሜዋን አላሰበችም፤ ስለዚህ በድንቅ ተዋርዳለች፥ የሚያጽናናትም የለም፤ አቤቱ፥ ጠላት ከፍ ከፍ ብሎአልና መከራዬን ተመልከት።

10. ፤ ዮድ። አስጨናቂው በከበረ ነገርዋ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ ያዘዝሃቸው አሕዛብ ወደ መቅደስዋ ሲገቡ አይታለችና።

11. ፤ ካፍ። ሕዝብዋ ሁሉ እየጮኹ ያለቅሳሉ እንጀራም ይፈልጋሉ፤ ሰውነታቸውን ለማበርታት የከበረ ሀብታቸውን ስለ መብል ሰጥተዋል፤ አቤቱ፥ ተጐሳቍያለሁና እይ፥ ተመልከትም።

12. ፤ ላሜድ። እናንተ መንገድ አላፊዎች ሁሉ፥ በእናንተ ዘንድ ምንም የለምን? እግዚአብሔር በጽኑ ቍጣው ቀን እኔን እንዳስጨነቀበት በእኔ ላይ እንደ ተደረገው እንደ እኔ መከራ የሚመስል መከራ እንዳለ ተመልከቱ፥ እዩ።

13. ፤ ሜም። ከላይ እሳትን ወደ አጥንቴ ሰደደ በረታችበትም፤ ለእግሬ ወጥመድ ዘረጋ ወደ ኋላም መለሰኝ፥ አጠፋኝም ቀኑንም ሁሉ አደከመኝ።

14. ፤ ኖን። የኃጢአቶቼ ቀንበር በእጁ ተይዛለች፤ ታስረው በአንገቴ ላይ ወጥተዋል፤ ጕልበቴን አደከመ። ጌታ በፊታቸው እቆም ዘንድ በማልችላቸው እጅ አሳልፎ ሰጠኝ።

15. ፤ ሳምኬት። ጌታ ኃያላኖቼን ሁሉ ከውስጤ አስወገዳቸው፤ ጕልማሶቼን ያደቅቅ ዘንድ ጉባኤን ጠራብኝ፤ ጌታ ድንግሊቱን የይሁዳን ልጅ በመጥመቂያ እንደሚረገጥ አድርጎ ረገጣት።

16. ፤ ዔ። የሚያጽናናኝ ነፍሴንም የሚያበረታት ከእኔ ርቆአልና ስለዚህ አለቅሳለሁ፤ ዓይኔ፥ ዓይኔ ውኃ ያፈስሳል። ጠላት በርትቶአልና ልጆቼ ጠፍተዋል።

17. ፤ ፌ። ጽዮን እጅዋን ዘረጋች፤ የሚያጽናናት የለም፤ እግዚአብሔር በያዕቆብ ዙሪያ ያሉትን እንዲያስጨንቁት አዘዘ፤ ኢየሩሳሌም በመካከላቸው እንደ ርኩስ ነገር ሆናለች።

18. ፤ ጻዴ። በአፉ ነገር ላይ ዓመፅ አድርጌአለሁና እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። እናንተ አሕዛብ ሁሉ፥ እባካችሁ፥ ስሙ መከራዬንም ተመልከቱ፤ ደናግሎቼና ጐበዛዝቴ ተማርከው ሄዱ።

19. ፤ ቆፍ። ውሽሞቼን ጠራሁ እነርሱም አታለሉኝ፤ ካህናቶቼና ሽማግሌዎቼ ሰውነታቸውን ያበረቱ ዘንድ መብል ሲፈልጉ በከተማ ውስጥ ሞቱ።

20. ፤ ሬስ። አቤቱ፥ ተጨንቄአለሁና፥ አንጀቴም ታውኮብኛልና ተመልከት፤ ዓመፃን ፈጽሞ አድርጌአለሁና ልቤ በውስጤ ተገላበጠብኝ፤ በሜዳ ሰይፍ ልጆቼን አጠፋ በቤትም ሞት አለ።

21. ፤ ሳን። እኔ እየጮኽሁ እንደማለቅስ ሰምተዋል፤ የሚያጽናናኝ የለም፤ ጠላቶቼ ሁሉ ስለ መከራዬ ሰምተዋል፤ አንተ አድርገኸዋልና ደስ አላቸው፤ ስለ እርሱ የተናገርኸውን ቀን ታመጣለህ እነርሱም እንደ እኔ ይሆናሉ።

22. ፤ ታው። ልቅሶዬ እጅግ ነውና፥ ልቤም ደክሞአልና ክፋታቸው ሁሉ ወደ ፊትህ ይድረስ፥ ስለ ኃጢአቴ ሁሉ እንዳደረግህብኝ አድርግባቸው።

About ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 1

Read ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሰቆቃወ ኤርምያስ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ሰቆቃወ ኤርምያስ
Chapter: 1
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ሰቆቃወ ኤርምያስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 1 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 1?

ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 1 is part of the Book of ሰቆቃወ ኤርምያስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 1 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ሰቆቃወ ኤርምያስ

  1. ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 4
  2. ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 3
  3. ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 5
  4. ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 2

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ዘኍልቍ Chapter 33
  2. ኤርምያስ Chapter 29
  3. ኢሳይያስ Chapter 58
  4. 1 ሳሙኤል Chapter 30
  5. ኤርምያስ Chapter 36
  6. ሩት Chapter 1
  7. 2 ነገሥት Chapter 2

Related Chapters & Readings

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 51
  2. 2 ቆሮንቶስ Chapter 5
  3. 2 ዜና መዋዕል Chapter 17
  4. ሕዝቅኤል Chapter 22
  5. ዮሐንስ Chapter 5
  6. ኢዮብ Chapter 16
  7. አስቴር Chapter 1
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *