ምሳሌ Chapter 25

For English

Read ምሳሌ Chapter 25 Online

Read ምሳሌ Chapter 25 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ምሳሌ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ምሳሌ 25

ምዕራፍ 25

1. እነዚህም ደግሞ የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስ ሰዎች የቀዱአቸው የሰሎሞን ምሳሌዎች ናቸው።

2. የእግዚአብሔር ክብር ነገርን መሰወር ነው፤ የነገሥታት ክብር ግን ነገርን መመርመር ነው።

3. እንደ ሰማይ ከፍታ እንደ ምድርም ጥልቀት የነገሥታት ልብ አይመረመርም።

4. ከብር ዝገትን አስወግድ፥ ፈጽሞም ይጠራል።

5. ከንጉሥ ፊት ኀጥኣንን አርቅ፥ ዙፋኑም በጽድቅ ትጸናለች።

6. በንጉሥ ፊት አትመካ፥ በታላልቆችም ስፍራ አትቁም፤

7. ዓይኖችህ ባዩት በመኰንን ፊት ከምትዋረድ። ወደዚህ ከፍ በል ብትባል ይሻልሃልና።

8. ባልንጀራህ ባሳፈረህ ጊዜ ኋላ እንዳትጸጸት ለክርክር ፈጥነህ አትውጣ፤

9. ክርክርህን ከባልንጀራህ ጋር ተከራከር፤ የሌላ ሰው ምሥጢር ግን አትግለጥ፥

10. የሚሰማ እንዳይነቅፍህ፥ አንተንም ከማነወር ዝም እንዳይል።

11. የወርቅ እንኮይ በብር ፃሕል ላይ፤ የጊዜው ቃል እንዲሁ ነው።

12. የምትሰማን ጆሮ የሚዘልፍ ጠቢብ ሰው እንደ ወርቅ ጉትቻ እንደሚያንጸባርቅም ዕንቍ እንዲሁ ነው።

13. በመከር ወራት የውርጭ ጠል ደስ እንደሚያሰኝ፥ እንዲሁ የታመነ መልእክተኛ ለላኩት ነው፤ የጌቶቹን ነፍስ ያሳርፋልና።

14. ስለ ስጦታው በሐሰት የሚመካ ሰው ዝናብ እንደማይከተለው ደመና ነፋስም ነው።

15. በትዕግሥት አለቃ ይለዝባል፥ የገራም ምላስ አጥንትን ይሰብራል።

16. አጥብቀህ እንዳትጠግብ እንዳትተፋውም ማር ባገኘህ ጊዜ የሚበቃህን ብላ።

17. እንዳይሰለችህ እንዳይጠላህም እግርህን ወደ ባልንጀራህ ቤት አታዘውትር።

18. በባልንጀራው በሐሰት የሚመሰክር እንደ መዶሻና እንደ ሰይፍ እንደ ተሳለም ፍላጻ ነው።

19. ወስላታውን ሰው በመከራ ጊዜ መተማመን እንደ ተሰበረ ጥርስና እንደ ሰለለ እግር ነው።

20. ለሚያዝን ልብ ዝማሬ የሚዘምር፥ ለብርድ ቀን መጐናጸፊያውን እንደሚያስወግድ በቍስልም ላይ እንደ መጻጻ እንዲሁ ነው።

21. ጠላትህ ቢራብ እንጀራ አብላው፥ ቢጠማም ውኃ አጠጣው፤

22. ፍም በራሱ ላይ ትሰበስባለህና፥ እግዚአብሔርም ዋጋህን ይመልስልሃልና።

23. የሰሜን ነፋስ ወጀብ ያመጣል፤ ሐሜተኛ ምላስም የሰውን ፊት ያስቈጣል።

24. ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ከመቀመጥ በሰገነት ማዕዘን መቀመጥ ይሻላል።

25. የቀዘቀዘ ውኃ ለተጠማች ነፍስ ደስ እንደሚያሰኝ፥ ከሩቅ አገር የመጣ መልካም ምስራች እንዲሁ ነው።

26. በኀጥእ ፊት የሚወድቅ ጻድቅ እንደደፈረሰ ፈሳሽና እንደ ረከሰ ምንጭ ነው።

27. ብዙ ማር መብላት መልካም አይደለም፤ እንዲሁም የራስን ክብር መፈላለግ አያስከብርም።

28. ቅጥር እንደሌላት እንደ ፈረሰች ከተማ፥ መንፈሱን የማይከለክል ሰው እንዲሁ ነው።

About ምሳሌ Chapter 25

Read ምሳሌ Chapter 25 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ምሳሌ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ምሳሌ
Chapter: 25
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ምሳሌ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ምሳሌ Chapter 25 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ምሳሌ Chapter 25?

ምሳሌ Chapter 25 is part of the Book of ምሳሌ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ምሳሌ Chapter 25 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ምሳሌ

  1. ምሳሌ Chapter 29
  2. ምሳሌ Chapter 24
  3. ምሳሌ Chapter 17
  4. ምሳሌ Chapter 4
  5. ምሳሌ Chapter 19
  6. ምሳሌ Chapter 15
  7. ምሳሌ Chapter 1

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. አስቴር Chapter 1
  2. ኢሳይያስ Chapter 36
  3. ኢያሱ Chapter 14
  4. 2 ሳሙኤል Chapter 17
  5. አስቴር Chapter 5
  6. ነህምያ Chapter 12
  7. ኤርምያስ Chapter 41

Related Chapters & Readings

  1. ኢሳይያስ Chapter 26
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 60
  3. ኢያሱ Chapter 10
  4. ነህምያ Chapter 2
  5. መክብብ Chapter 1
  6. 1 ጴጥሮስ Chapter 2
  7. ዘጸአት Chapter 2
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *