ኤርምያስ Chapter 4

For English

Read ኤርምያስ Chapter 4 Online

Read ኤርምያስ Chapter 4 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኤርምያስ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኤርምያስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ኤርምያስ 4

ምዕራፍ 4

1. እስራኤል ሆይ፥ ብትመለስ፥ ወደ እኔ ተመለስ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ርkWsvትህንም ከፊቴ ብታስወግድ፥ ባትናወጥም፥

2. ሕያው እግዚአብሔርን! ብለህም በእውነትና በቅንነት በጽድቅም ብትምል፥ አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ በእርሱም ይመካሉ።

3. እግዚአብሔር ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እንዲህ ይላልና። ጥጋቱን እርሻ እረሱ በእሾህም ላይ አትዝሩ።

4. እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሆይ፥ ስለ ሥራችሁ ክፋት KWTaዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል፥ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።

5. በይሁዳ ዘንድ ተናገሩ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩና። በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ በሉ፤ ጮኻችሁም። ሁላችሁ ተሰብሰቡ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ በሉ።

6. ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና ወደ ጽዮን ዓላማን አንሡ፤ ሽሹ፥ አትዘግዩ።

7. አንበሳ ከጭፍቅ ዱር ወጥቶአል፥ አሕዛብንም የሚዘርፍ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ያደርግ ዘንድ ከስፍራው ወጥቶአል፥ ከተሞችሽም ሰው የሌለባቸው ፍርስራሾች ይሆናሉ።

8. የእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ከእኛ ዘንድ አልተመለሰምና ማቅ ልበሱ፥ አልቅሱም ዋይም በሉ።”

9. በዚያም ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የንጉሡና የመኳንንቱ ልብ ይጠፋል፥ ካህናቱም ይደነቃሉ ነቢያቱም ይደነግጣሉ።

10. እኔም። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ፥ አንተ ሰይፍ እስከ ነፍስ ድረስ በደረሰ ጊዜ። ሰላም ይሆንላችኋል ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን እጅግ አታለልህ አልሁ።

11. በዚያ ጊዜ ለዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም። ለማበጠር ወይም ለማጥራት ሳይሆን የሚያቃጥል ነፋስ በምድረ በዳ ካሉ ከወናዎች ኮረብቶች ወደ ወገኔ ሴት ልጅ ይመጣል፤

12. ስለ እኔ ጽኑ የሆነ ነፋስ ከእነዚህ ይመጣል ይባላል። አሁንም እኔ ደግሞ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።

13. እነሆ፥ እንደ ደመና ይወጣል፥ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ፤ ፈረሶቹም ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። ጠፍተናልና ወዮልን።

14. ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ትድኚ ዘንድ ልብሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። ክፉ አሳብ የሚኖርብሽ እስከ መቼ ድረስ ነው?

15. የተናጋሪ ድምፅ ከዳን ዘንድ ይናገራልና፥ ከኤፍሬምም ኮረብቶች መከራን ያወራልና።

16. ለአሕዛብ አሰሙና። እነሆ፥ ጠባቂዎች ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ በይሁዳም ከተሞች ላይ ይጮኻሉ ብላችሁ በኢየሩሳሌም ላይ አውሩ።

17. በእኔ ላይ ዓመፀኛ ሆናለችና በዙሪያዋ ከብበው እንደ እርሻ ጠባቂዎች ሆነውባታል፥ ይላል እግዚአብሔር።

18. መንገድሽና ሥራሽ ይህን አድርጎብሻል፤ ይህ ክፋትሽ መራር ነው፥ ወደ ልብሽም ደርሶአል።

19. አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፥ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፤ ነፍሴ ሆይ፥ የመለከትን ድምፅና የሰልፍን ውካታ ሰምተሻልና ዝም እል ዘንድ አልችልም።

20. መከራ በመከራ ላይ ተጠርቶአል፤ ምድርም ሁሉ ተበዝብዛለችና፤ በድንገትም ድንኳኔ በቅጽበት ዓይንም መጋረጃዎቼ ጠፉ።

21. ዓላማውን የምመለከት፥ የመለከቱንስ ድምፅ የምሰማ እስከ መቼ ነው?

22. ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤ ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።

23. ምድሪቱን አየሁ፥ እነሆም፥ ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም፤ ሰማያትንም አየሁ፥ ብርሃንም አልነበረባቸውም።

24. ተራሮችን አየሁ፥ እነሆም፥ ተንቀጠቀጡ፥ ኮረብቶችም ሁሉ ተናወጡ።

25. አየሁ፥ እነሆም፥ ሰው አልነበረም፥ የሰማይም ወፎች ሁሉ ሸሽተው ነበር።

26. አየሁ፥ እነሆም፥ ፍሬያማ እርሻ ምድረ በዳ ሆነች፥ ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ከጽኑ KWTaው የተነሣ ፈርሰው ነበር።

27. እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች፥ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋትም።

28. ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፥ በላይም ሰማይ ይጠKWraል፤ ተናግሬአለሁና፥ አስቤአለሁም፤ አልጸጸትም ከእርሱም አልመለስም።

29. ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ድምፅ የተነሣ ከተማ ሁሉ ሸሽታለች፤ ወደ ችፍግ ዱርም ይገባሉ በቋጥኝ ላይም ይወጣሉ፤ ከተማ ሁሉ ተለቅቃለች የሚቀመጥባትም ሰው የለም።

30. አንቺም የተበዘበዝሽ ሆይ፥ ምን ታደርጊአለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም ባጌጥሽ ጊዜ፥ ዓይንሽንም በkWl በተኳልሽ ጊዜ፥ በከንቱ ታጌጫለሽ፤ ውሽሞችሽ አቃለሉሽ፥ ነፍስሽን ይሹአታል።

31. እንደምታምጥ የበkWrዋንም እንደምትወልድ ሴት ድምፅ ሰምቻለሁና፤ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ይሰልላል፥ እጆችዋንም ትዘረጋለችና። ተገድለው ከሞቱት የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ! አለች።

About ኤርምያስ Chapter 4

Read ኤርምያስ Chapter 4 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኤርምያስ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ኤርምያስ
Chapter: 4
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኤርምያስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ኤርምያስ Chapter 4 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ኤርምያስ Chapter 4?

ኤርምያስ Chapter 4 is part of the Book of ኤርምያስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ኤርምያስ Chapter 4 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 2
  2. አሞጽ Chapter 7
  3. አሞጽ Chapter 4
  4. አሞጽ Chapter 3
  5. አሞጽ Chapter 1
  6. አሞጽ Chapter 9
  7. አሞጽ Chapter 6

Explore More from ኤርምያስ

  1. ኤርምያስ Chapter 17
  2. ኤርምያስ Chapter 40
  3. ኤርምያስ Chapter 45
  4. ኤርምያስ Chapter 41
  5. ኤርምያስ Chapter 34
  6. ኤርምያስ Chapter 49
  7. ኤርምያስ Chapter 16

Related Chapters & Readings

  1. ዮናስ Chapter 3
  2. ኤርምያስ Chapter 39
  3. ኤርምያስ Chapter 21
  4. ኢዮብ Chapter 19
  5. 1 ዜና መዋዕል Chapter 8
  6. ዘካርያስ Chapter 6
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 94
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *