2 ሳሙኤል Chapter 22

For English

Read 2 ሳሙኤል Chapter 22 Online

Read 2 ሳሙኤል Chapter 22 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ሳሙኤል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 2 ሳሙኤል and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

2 ሳሙኤል 22

ምዕራፍ 22

1. ዳዊትም እግዚአብሔር ከሳኦል እጅና ከጠላቶቹ እጅ ሁሉ ባዳነው ቀን የዚህን ቅኔ ቃል ለእግዚአብሔር ተናገረ።

2. ፤ እንዲህም አለ። እግዚአብሔር ዓለቴ አምባዬ መድኃኒቴ ነው፤

3. ፤ እግዚአብሔር ጠባቂዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ፤ ጋሻዬና የረድኤቴ ቀንድ፥ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ፥ መድኃኒቴ ሆይ፥ ከግፍ ሥራ ታድነኛለህ።

4. ፤ ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ።

5. ፤ የሞት ጣር ያዘኝ፤ የዓመፅ ፈሳሽም አስፈራኝ፤

6. ፤ የሲኦል ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድ ደረሰብኝ።

7. ፤ በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፤ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።

8. ፤ ምድርም ተንቀጠቀጠች፥ ተናወጠችም፥ የሰማዮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፤ እግዚአብሔርም ተቈጥቶአልና ተንቀጠቀጡ።

9. ፤ ከቍጣው ጢስ ወጣ፥ ከአፉም የሚበላ እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእርሱ በራ።

10. ፤ ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ፥ ወረደም፤ ጨለማም ከእግሩ በታች ነበረ።

11. ፤ በኪሩብም ላይ ተቀምጦ በረረ፤ በነፋስም ክንፍ ሆኖ ታየ፤

12. ፤ መሰወርያውን ጨለማ፥ በዙሪያውም የነበረውን ድንኳን፥ በደመና ውስጥ የነበረ የጨለማ ውኃ አደረገ።

13. ፤ በፊቱም ካለው ብርሃን የተነሣ ፍም ተቃጠለ።

14. ፤ እግዚአብሔርም ከሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ፤

15. ፤ ፍላጻውን ላከ፥ በተናቸውም መብረቆችን ላከ፥ አወካቸውም።

16. ፤ ከእግዚአብሔር ዘለፋ፥ ከመዓቱም መንፈስ እስትንፋስ የተነሣ፥ የባሕር ፈሳሾች ታዩ፥ የዓለም መሠረቶችም ተገለጡ።

17. ፤ ከላይ ሰደደ፥ ወሰደኝም፤ ከብዙ ውኆችም አወጣኝ።

18. ፤ ከብርቱዎች ጠላቶቼ፥ ከሚጠሉኝም አዳነኝ፤ በርትተውብኝ ነበርና።

19. ፤ በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ደገፋዬ ሆነ።

20. ፤ ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፤ ወድዶኛልና አዳነኝ።

21. ፤ እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ ይከፍለኛል፤ እንደ እጄ ንጽሕና ይመልስልኛል፤

22. ፤ የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፥ በአምላኬም አላመፅሁምና።

23. ፤ ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበረና፤ ከሥርዓቱም አልራቅሁምና።

24. ፤ በእርሱ ዘንድ ቅን ነበርሁ፥ ከኃጢአቴም ተጠበቅሁ።

25. ፤ እግዚአብሔርም እንደ ጽድቄ፥ እንደ እጄም ንጽሕና በዓይኖቹ ፊት መለሰልኝ።

26. ፤ ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤

27. ፤ ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ።

28. ፤ አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፤ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ።

29. ፤ አቤቱ፥ አንተ መብራቴ ነህና፤ እግዚአብሔርም ጨለማዬን ያበራል።

30. ፤ በአንተ ኃይል በጭፍራ ላይ እሮጣለሁና፤ በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁና።

31. ፤ የአምላክ መንገድ ፍጹም ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፤ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው።

32. ፤ ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችንስ በቀር አምባ ማን ነው?

33. ፤ ኃይልን የሚያስታጥቀኝ፥ መንገዴንም የሚያቃና፥

34. ፤ እግሮቼን እንደ ብሆር እግሮች የሚያበረታ፥ በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው።

35. ፤ እጆቼን ሰልፍ ያስተምራል፤ በክንዴም የናስ ቀስት እገትራለሁ።

36. ፤ የማዳንህንም ጋሻ ሰጠኸኝ፤ ተግሣጽህም አሳደገኝ።

37. ፤ አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፥ እግሮቼም አልተንሸራተቱም።

38. ፤ ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ፥ አጠፋቸውማለሁ፤ እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም።

39. ፤ አስጨንቃቸዋለሁ መቆምም አይችሉም፥ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ።

40. ፤ ለሰልፍም ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፤ በላዬ የቆሙትን በበታቼ ታስገዛቸዋለህ።

41. ፤ የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው።

42. ፤ ጮኹ፥ የሚረዳቸውም አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ አልሰማቸውምም።

43. ፤ እንደ ምድር ትቢያ ፈጨኋቸው፤ እንደ አደባባይም ጭቃ ረገጥኋቸው፥ ደቀደቅኋቸውም።

44. ፤ ከሕዝብ ክርክር ታድነኛለህ፤ የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፤ የማላውቀው ሕዝብም ይገዛልኛል።

45. ፤ የባዕድ ልጆች ደለሉኝ፤ በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ።

46. ፤ የባዕድ ልጆች እየጠፉ ይሄዳሉ፤ ከተዘጉ ስፍሮች እየተንቀጠቀጡ ይወጣሉ።

47. ፤ እግዚአብሔር ሕያው ነው፥ ጠባቂዬም ቡሩክ ነው፤ የመድኃኒቴ ጠባቂ አምላኬ ከፍ ከፍ ይበል፤

48. ፤ በቀሌን የሚመልስልኝ አምላክ፥ አሕዛብን በበታቼ የሚያስገዛ፥

49. ፤ ከጠላቶቼ የሚያወጣኝ እርሱ ነው፤ በእኔም ላይ ከቆሙ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፤ ከግፈኛ ሰው ታድነኛለህ።

50. ፤ አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ ለስምህም እዘምራለሁ።

51. ፤ የንጉሡን መድኃኒት ታላቅ ያደርጋል፤ ቸርነቱንም ለቀባው፥ ለዳዊትና ለዘሩ፥ ለዘላለም ይሰጣል።

About 2 ሳሙኤል Chapter 22

Read 2 ሳሙኤል Chapter 22 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ሳሙኤል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 2 ሳሙኤል
Chapter: 22
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 2 ሳሙኤል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 2 ሳሙኤል Chapter 22 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 2 ሳሙኤል Chapter 22?

2 ሳሙኤል Chapter 22 is part of the Book of 2 ሳሙኤል in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 2 ሳሙኤል Chapter 22 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 2-ሳሙኤል

  1. 2 ሳሙኤል Chapter 1
  2. 2 ሳሙኤል Chapter 13
  3. 2 ሳሙኤል Chapter 2
  4. 2 ሳሙኤል Chapter 21
  5. 2 ሳሙኤል Chapter 16
  6. 2 ሳሙኤል Chapter 3
  7. 2 ሳሙኤል Chapter 12

Explore More from ብሉይ ኪዳን

  1. ሶፎንያስ Chapter 2
  2. ዘጸአት Chapter 3
  3. ዘዳግም Chapter 20
  4. ዘካርያስ Chapter 5
  5. 1 ዜና መዋዕል Chapter 12
  6. ዘዳግም Chapter 3
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 6

Related Chapters & Readings

  1. ዘዳግም Chapter 18
  2. የሐዋርያት ሥራ Chapter 17
  3. ሕዝቅኤል Chapter 26
  4. 1 ዜና መዋዕል Chapter 6
  5. ዘፍጥረት Chapter 25
  6. 1 ዜና መዋዕል Chapter 29
  7. ሉቃስ Chapter 8
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *