ኤርምያስ Chapter 14

For English

Read ኤርምያስ Chapter 14 Online

Read ኤርምያስ Chapter 14 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኤርምያስ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኤርምያስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ኤርምያስ 14

ምዕራፍ 14

1. ወደ ኤርምያስ ስለ ድርቅ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።

2. ይሁዳ አለቀሰች፥ ደጆችዋም ባዶ ሆኑ በምድርም ላይ ጨለሙ፤ የኢየሩሳሌም ጩኸት ከፍ ከፍ ብሎአል።

3. ታላላቆችም ብላቴኖቻቸውን ወደ ውኃ ሰደዱ፤ ወደ ጕድጓድ መጡ ውኃም አላገኙም፥ ዕቃቸውንም ባዶውን ይዘው ተመለሱ፤ አፈሩም ተዋረዱም ራሳቸውንም ተከናነቡ።

4. በምድር ላይ አልዘነበምና መሬቱ ስንጥቅጥቅ ስለሆነ አራሾች አፈሩ ራሳቸውንም ተከናነቡ።

5. ዋላ ደግሞ በምድረ በዳ ወለደች፥ ሣርም የለምና ግልገልዋን ተወች።

6. የሜዳ አህዮችም በወና ኮረብታ ላይ ቆመዋል፥ እንደ ቀበሮም ወደ ነፋስ አለከለኩ፤ ልምላሜም የለምና ዓይኖቻቸው ጠወለጉ።

7. አቤቱ፥ ኃጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኃጢአት ሠርተናልና ኃጢአታችን ይመሰክርብናል ነገር ግን ስለ ስምህ ብለህ አድርግ።

8. አንተ የእስራኤል ተስፋ ሆይ በመከራም ጊዜ የምታድነው፥ በምድር እንደ እንግዳ፥ ወደ ማደሪያ ዘወር እንደሚል መንገደኛ ስለ ምን ትሆናለህ?

9. እንዳንቀላፋ ሰው ሰው፥ ያድንም ዘንድ እንደማይችል ኃያል ስለ ምን ትሆናለህ? አንተ ግን፥ አቤቱ፥ በመካከላችን ነህ እኛም በስምህ ተጠርተናል፤ አትተወን።

10. እግዚአብሔር ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል። መቅበዝበዝን ወድደዋል እግራቸውንም አልከለከሉም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ደስ አይለውም፥ በደላቸውንም አሁን ያስባል ኃጢአታቸውንም ይቀጣል።

11. እግዚአብሔርም። ለዚህ ሕዝብ ስለ መልካም አትጸልይላቸው።

12. በጾሙ ጊዜ ጸሎታቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ባቀረቡ ጊዜ አልቀበላቸውም፤ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ አለኝ።

13. እኔም። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! እነሆ፥ ነቢያት። በእውነት ሰላምን በዚህ ስፍራ እሰጣችኋለሁ እንጂ ሰይፍን አታዩም፥ ራብም አያገኛችሁም ይሉአቸዋል አልሁ።

14. እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ። ነቢያቱ ውሸት በስሜ ትንቢት ይናገራሉ፤ አላክኋቸውም፥ አላዘዝኋቸውም፥ አልተናገርኋቸውም፤ የውሸቱን ራእይ ምዋርትንም ከንቱንም ነገር የልባቸውንም ሽንገላ ይሰብኩላችኋል።

15. ስለዚህ እግዚአብሔር በስሜ ትንቢት ስለሚናገሩ ነቢያት። በዚህች አገር ሰይፍና ራብ አይሆንም ስለሚሉ ስላላክኋቸው ነቢያት እንዲህ ይላል። እነዚያ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ።

16. ትንቢት የሚናገሩላቸውም ሰዎች ከራብና ከሰይፍ የተነሣ በኢየሩሳሌም አደባባይ ይበተናሉ፤ ክፋታቸውንም አፈስስባቸዋለሁ እነርሱንና ሚስቶቻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም የሚቀብራቸው አይገኝም።

17. እንደዚህም ብለህ ትነግራቸዋለህ። የወገኔ ልጅ ድንግሊቱ በታላቅ ስብራትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰብራለችና ዓይኖቼ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፈሳሉ።

18. ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ፥ በሰይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተማም ብገባ፥ እነሆ፥ በራብ የከሱ አሉ፤ ነቢዩና ካህኑም ወደማያውቋት አገር ሄደዋልና።

19. በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ጠልታታለችን? ስለ ምን መታኸን? ፈውስስ ስለ ምን የለንም? ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፤ ፈውስን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ።

20. አቤቱ፥ በአንተ ላይ ኃጢአትን ሠርተናልና ክፋታችንንና የአባቶቻችንን በደል እናውቃለን።

21. ስለ ስምህ ብለህ አትናቀን፥ የክብርህንም ዙፋን አታስነውር፤ ከእኛ ጋርም ያደረግኸውን ቃል ኪዳንህን አስብ እንጂ አታፍርስ።

22. በውኑ በአሕዛብ ጣዖታት መካከል ያዘንብ ዘንድ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ዝናብ ማፍሰስ ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ፥ አንተ አይደለህምን? አንተ ይህን ነገር ሁሉ አድርገሃልና ስለዚህ አንተን በተስፋ እንጠባበቃለን።

About ኤርምያስ Chapter 14

Read ኤርምያስ Chapter 14 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኤርምያስ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ኤርምያስ
Chapter: 14
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኤርምያስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ኤርምያስ Chapter 14 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ኤርምያስ Chapter 14?

ኤርምያስ Chapter 14 is part of the Book of ኤርምያስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ኤርምያስ Chapter 14 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 1
  3. አሞጽ Chapter 3
  4. አሞጽ Chapter 6
  5. አሞጽ Chapter 2
  6. አሞጽ Chapter 7
  7. አሞጽ Chapter 5

Explore More from ኤርምያስ

  1. ኤርምያስ Chapter 38
  2. ኤርምያስ Chapter 18
  3. ኤርምያስ Chapter 24
  4. ኤርምያስ Chapter 47
  5. ኤርምያስ Chapter 15
  6. ኤርምያስ Chapter 17
  7. ኤርምያስ Chapter 43

Related Chapters & Readings

  1. ሉቃስ Chapter 15
  2. ማቴዎስ Chapter 8
  3. 2 ዜና መዋዕል Chapter 3
  4. ኢዩኤል Chapter 3
  5. ዘካርያስ Chapter 5
  6. ኢዮብ Chapter 21
  7. ዘዳግም Chapter 2
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *