Read ኤርምያስ Chapter 21 Online
Read ኤርምያስ Chapter 21 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኤርምያስ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኤርምያስ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
ኤርምያስ 21
ምዕራፍ 21
1. ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው።
2. ይህም የሆነው ንጉሡ ሴዴቅያስ። የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይወጋናልና ስለ እኛ፥ እባክህ፥ እግዚአብሔርን ጠይቅ፤ ከእኛም ይመለስ ዘንድ ምናልባት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደ ተአምራቱ ሁሉ ያደርግ ይሆናል ብሎ የመልክያን ልጅ ጳስኮርንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስ ወደ ኤርምያስ በላከ ጊዜ ነው።
3. ኤርምያስም እንዲህ አላቸው። ሴዴቅያስን እንዲህ በሉት።
4. የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ የባቢሎንን ንጉሥ በቅጥርም ውጭ የከበቡአችሁን ከለዳውያንን የምትወጉበትን በእጃችሁ ያለውን ዕቃ ጦራችሁን እመልሰዋለሁ፥ እነዚያንም ወደዚህች ከተማ ውስጥ እሰበስባቸዋለሁ።
5. እኔም በተዘረጋች እጅና በብርቱ ክንድ፥ በቍጣና በመዓት በታላቅም መቅሠፍት እወጋችኋለሁ።
6. በዚህችም ከተማ የሚኖሩትን ሁሉ ሰዎችንና እንስሶችን እመታለሁ፥ በጽኑም ቸነፈር ይሞታሉ።
7. ከዚህ በኋላ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ከቸነፈርና ከሰይፍ ከራብም በዚህች ከተማ የቀሩትንም ባሪዎቹንና ሕዝቡን በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውንም በሚሹት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እርሱም በሰይፍ ስለት ይመታቸዋል፤ አያዝንላቸውም፥ አይራራላቸውም፥ አይምራቸውም።
8. ለዚህም ሕዝብ እንዲህ በል። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ በፊታችሁ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ አድርጌአለሁ።
9. በዚህች ከተማ ውስጥ የሚዘገይ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ይሞታል፤ ወጥቶ ወደ ከበቡአችሁ ወደ ከለዳውያን የሚገባ ግን በሕይወት ይኖራል፥ ነፍሱም ምርኮ ትሆንለታለች።
10. ለመልካም ሳይሆን ለክፋ ፊቴን በዚህች ከተማ ላይ አድርጌአለሁና፤ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ትሰጣለች፥ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል።
11. የይሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
12. የዳዊት ቤት ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣና ማንም ሳያጠፋው እንዳይነድድ፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ የተበዘበዘውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ።
13. እነሆ፥ በሸለቆው ውስጥ በሜዳ ላይም ባለው አምባ የምትቀመጪ ሆይ፥ እኔ በአንቺ ላይ ነኝ፤ እናንተም። በእኛ ላይ የሚወርድ ወይም ወደ መኖሪያችን የሚገባ ማን ነው? የምትሉ ሆይ፥ እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፤
14. እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፤ በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፥ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።
About ኤርምያስ Chapter 21
Read ኤርምያስ Chapter 21 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኤርምያስ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: ኤርምያስ
Chapter: 21
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኤርምያስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading ኤርምያስ Chapter 21 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is ኤርምያስ Chapter 21?
ኤርምያስ Chapter 21 is part of the Book of ኤርምያስ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete ኤርምያስ Chapter 21 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from ብሉይ ኪዳን
Explore More from ኤርምያስ
- ኤርምያስ Chapter 15
- ኤርምያስ Chapter 23
- ኤርምያስ Chapter 30
- ኤርምያስ Chapter 47
- ኤርምያስ Chapter 24
- ኤርምያስ Chapter 4
- ኤርምያስ Chapter 18