ኤርምያስ Chapter 20

For English

Read ኤርምያስ Chapter 20 Online

Read ኤርምያስ Chapter 20 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኤርምያስ in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኤርምያስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ኤርምያስ 20

ምዕራፍ 20

1. በእግዚአብሔርም ቤት የተሾመው አለቃ የካህኑ የኢሜር ልጅ ጳስኮር ኤርምያስ በዚህ ነገር ትንቢት ሲናገር ሰማ።

2. ጳስኮርም ነቢዩን ኤርምያስን መታው፥ በእግዚአብሔርም ቤት በነበረው በላይኛው በብንያም በር ባለው በእግር ግንድ ውስጥ አኖረው።

3. በነጋውም ጳስኮር ኤርምያስን ከግንድ ውስጥ አወጣው። ኤርምያስም እንዲህ አለው። እግዚአብሔር ስምህን። ማጎርሚሳቢብ እንጂ ጳስኮር ብሎ አይጠራህም።

4. እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። እነሆ፥ ለራስህና ለወዳጆችህ ሁሉ ፍርሃት አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ ዓይኖችህም ያያሉ፤ ይሁዳንም ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል በሰይፍም ይገድላቸዋል።

5. የዚህችንም ከተማ ባለጠግነት ሁሉ ጥሪትዋንም ሁሉ ክብርዋንም ሁሉ የይሁዳንም ነገሥታት መዝገብ ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እነርሱም ይበዘብዙአቸዋል ይዘውም ወደ ባቢሎን ያፈልሱአቸዋል።

6. አንተም፥ ጳስኮር ሆይ፥ በቤትህም የሚኖሩት ሁሉ ተማርካችሁ ትሄዳላችሁ፤ አንተም በሐሰትም ትንቢት የተናገርህላቸው ወዳጆችህ ሁሉ ወደ ባቢሎን ትገባላችሁ፥ በዚያም ትሞታላችሁ፥ በዚያም ትቀበራላችሁ።

7. አቤቱ፥ አታለልኸኝ እኔም ተታለልሁ፥ ከእኔም በረታህ አሸነፍህም፤ ቀኑን ሁሉ መሳቂያ ሆኛለሁ፥ ሁሉም ያላግጡብኛል።

8. በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፤ ግፍና ጥፋት ብዬ እጮኻለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ቀኑን ሁሉ ስድብና ዋዛ ሆኖብኛልና።

9. እኔም። የእግዚአብሔርን ስም አላነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህም በስሙ አልናገርም ብል፥ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፥ መሸከምም አልቻልሁም።

10. የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁ፥ ማስፈራራትም ከብቦኛል። መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ። ምናልባት ይታለል እንደ ሆነ፥ እናሸንፈውም እንደ ሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደ ሆነ፥ ክሰሱት እኛም እንከስሰዋለን ይላሉ።

11. እግዚአብሔር ግን እንደ ኃያልና እንደ ጨካኝ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም፤ አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘላለምም በማይረሳ ጕስቍልና ይጐሰቍላሉ።

12. አቤቱ፥ ጻድቅን የምትመረምር ኵላሊትንና ልብን የምትመለከት የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ ክርክሬን ገልጬልሃለሁና በቀልህን በላያቸው ለይ።

13. ለእግዚአብሔር ዘምሩ እግዚአብሔርንም አመስግኑ፤ የችግረኛውን ነፍስ ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና።

14. የተወለድሁባት ቀን የተረገመች ትሁን፤ እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን የተባረከች አትሁን።

15. ወንድ ልጅ ተወልዶልሃል ብሎ ለአባቴ የምሥራች ነግሮ ደስ ያሰኘው ሰው የተረገመ ይሁን።

16. ያም ሰው እግዚአብሔር ሳይጸጸት እንደ ገለበጣቸው ከተሞች ይሁን፥ በማለዳም ልቅሶን በቀትርም ጩኸትን ይስማ፤

17. እናቴ መቃብር ትሆነኝ ዘንድ ማኅፀንዋም ዘወትር ይዞኝ ያቆይ ዘንድ በማኅፀን ውስጥ አልገደለኝምና።

18. ድካምንና ጣርን አይ ዘንድ ዘመኔም በእፍረት ታልቅ ዘንድ ስለ ምን ከማኅፀን ወጣሁ?

About ኤርምያስ Chapter 20

Read ኤርምያስ Chapter 20 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኤርምያስ in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ኤርምያስ
Chapter: 20
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኤርምያስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ኤርምያስ Chapter 20 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ኤርምያስ Chapter 20?

ኤርምያስ Chapter 20 is part of the Book of ኤርምያስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ኤርምያስ Chapter 20 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 1
  3. አሞጽ Chapter 3
  4. አሞጽ Chapter 2
  5. አሞጽ Chapter 7
  6. አሞጽ Chapter 6
  7. አሞጽ Chapter 5

Explore More from ኤርምያስ

  1. ኤርምያስ Chapter 13
  2. ኤርምያስ Chapter 28
  3. ኤርምያስ Chapter 41
  4. ኤርምያስ Chapter 49
  5. ኤርምያስ Chapter 19
  6. ኤርምያስ Chapter 33
  7. ኤርምያስ Chapter 45

Related Chapters & Readings

  1. ኢዮብ Chapter 33
  2. ኤርምያስ Chapter 15
  3. መዝሙረ ዳዊት Chapter 32
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 33
  5. ኤርምያስ Chapter 3
  6. የሐዋርያት ሥራ Chapter 17
  7. ሕዝቅኤል Chapter 38
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *